>

አጣፍቶ ጠፊ (መስፍን አረጋ)

አጣፍቶ ጠፊ

 

መስፍን አረጋ

 

ጥላቻ ሲያሰክር አናት ላይ ሲወጣ

ራስን ያስጠላል ይበልጥ ከባላንጣ፡፡

ከባላንጣው ይበልጥ ራሱን የጠላ ኅሊናውን ያጣ

ደስታውን አይችልም ባላንጣው ተቀጥቶ እሱ እጥፍ ቢቀጣ፡፡

 

የደደቢት ጉዶች ባማራ ጥላቻ ደድበው ያበዱ

እየመሰላቸው አማራን የጎዱ፣ የሐበሻን ጠላት ኦነግን ረዱ፡፡ 

ተነስተዋል ምለው ላይሰንፉ ላያርፉ

አማራን አጣፍተው በቄሮ እስኪጠፉ፡፡

 

አፍቃሪ ወያኔ የትግራይ ልሂቃን ትግራዋይነታቸውን የሚገልጹት ባማራ ጥላቻቸው ስለሆነ፣ ማናቸውም ድርጊት አማራ የሚሉትን ሕዝብ ኢምንት የሚጎዳ እስከሆነ ድረስ እነሱን ጃምንት ቢጎዳም ከበሮ ያነሱለታል፡፡  ማናቸውም እሳት አማራን በወላፈኑ እስከገረፈ ድረስ ትግሬን የሚያንጨረጭር ቢሆንም እሳቱን ለመለኮስ፣ ለኩሰው ለማቀጣጠል፣ አቀጣጥለው ለማንቦግቦግ አያንገራግሩም፡፡  ያማራ ደሳሳ ጎጆ እስከፈረሰ ድረስ የትግሬ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ቢደረመስ፣ ያማራ ሐብት እስከተዘገነ ድረስ የትግሬ ሐብት ቢታፈስ፣ ያማራ ስም እስከጠለሸ ድረስ የትግሬ ሐበሻዊ ስም ቢጠቀርሽ፣ የ 50% አማራ ሐይማኖት እስከጠፋ ድረስ የ 96ትግሬ ሐይማኖት ቢጠፋ፣ ባጠቃላይ ደግሞ ያማራ አንድ ዓይን እስከጠፋ ድረስ የትግሬ ሁለቱም ቢደረገም ዴንታ የላቸውም፡፡

የኦነጋውያን እሳት አማራን ቢበላ፣ ቀጥሎ የሚበላው ትግሬን እንደሆነ በርግጠኝነት እያወቁ፣ እሳቱን ለማንቀልቀል ይንቀለቀላሉ፡፡  ጃዋር ሙሐመድና በቀለ ገርባ በመድረክ፣ ኦዴፓ ደግሞ በመግለጫ ሸገር የኦሮሞ ናት ሲሉ፣ የወያኔ ጎጠኞች ምንትሳቸው ቄጠማ ይቆርጣል፡፡ 

አስራ ሰባት ዓመት በሌት ጅብነት፣ ሃያ ሰባት ዓመት ደግሞ በዝብ ቀትርነት ልክ የሌለው ሐብት ዘረፉ፡፡  ከዚህ የዝርፊያ ሐብት ጥቂቱን በመቆንጠር ደግሞ ባንድ ቀን ባጸደቁት አፓርታዊዳዊ የሊዝ አዋጅ አማካኝነት ካማራና ከጉራጌ በነጠቁት ርስት ላይ አብዛኞቹን ያዲሳባ ሕንፃወች አነጹ፡፡  ስለዚህም የኦነጋውያን እቅድ ቢሳካ ከማንምና ከምንም በላይ የሚጎዱት እነሱ መሆናቸውን ነጋሪ አያስፈልጋቸውም፡፡ እንዲህም ሆኖ የኦነግን እቅድ ለማሳካት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡  የታከለ ኡማ ዓላማ ያማራንና የጉራጌን ቆሎ ይዞ ወደ ትግሬ አሻሮ መጠጋት እንደሆነ ይበልጥና ይበልጥ ግልጽ እየሆነላቸው፣ በኦቦ ታከለ የመጣ ባይናችን መጣ ይላሉ፡፡   

እነዚህ ዓይነቶቹን ምን እንበላቸውአጥፍቶ ጠፊ እንዳንላቸው፣ የሚመኙት አማራን አጥፍተው ራሳቸውን ማጥፋት ሳይሆን፣ አማራን አጣፍተው በኦነግ ኢንትራሐምዌ መጥፋት ነው፡፡  አጣፍቶ ጠፊ ይገልጻቸው ይሆን?

ኦነጋውያን በማያሻማ ቋንቋ እንደገለጹት፣ መሠረታዊ ዓላማቸው በመግደል፣ በማፈናቀል፣ አሰፋፈርን በመቀየርና በመሳሰሉት ዘዴወች ሐበሻ የሚሉትን ትግሬወችን የሚያካትተውን ሰፊ ሕዝብ፣ አብናቶቹ (አባቶቹና እናቶቹ) በደም ባጥንታቸው ባስከበሩለት በገዛ አገሩ በጦቢያ ላይ የበይ ተመልካች ማድረግ ነው፡፡  

ስለዚህም አፍቃሪ ወያኔ የትግራይ ልሂቃን ባማራ ጥላቻ ባይታወሩ ኖሮ፣ ማወገዝ የሚገባቸው የማንነታቸው መግለጫ የሆነውን ጦቢያዊነትን አለቅጥ አዳክሞ ከሞት አፋፍ ያደረሰውን ወያኔን ነበር፡፡  ትናንት ያስመራ መንገድ ጠራጊ የነበረው ኦነግ፣ ዛሬ በጦቢያዊነት መቃብር ላይ የኦሮሞን አጼጌ (empire) እገነባለሁ እያለ እስከመታበይ የደረሰው ዋናውን ሥራ ወያኔ ስለሠራለት ብቻ ነው፡፡   

የትግራይ ልሂቃን ቅሬታ ሊኖራቸው ይችላል፣ ቢኖራቸውም አያስገርምም፡፡  ጊዜው ግን የመወቃቀሻ ሳይሆን በዋናው ጠላት በኦነግ ላይ የሚተኮርበት ጊዜ ነው፡፡  እባብ ባለበት ጉንዳን አይፈራም፡፡ አብናቶቻችን በጣልያን ላይ፣ ቻይኖችም በጃፓኖች ላይ ያደረጉት ይህንኑ ነው፡፡  ጦቢያውያን አንድ ከሆኑ ደግሞ ፀረጦቢያውያን አንድ ቀን አያድሩም፡፡ ታከለ ኡማ ያማራንና የጉራጌን ቆሎ ዘግኘ ወደ ትግሬ አሻሮ እጠጋለሁ ሲል፣ አንድ ጥሬ ሳያነሳ እጁን ይሰበስብ፣ ካልሰበሰበም ይቆረጥ ነበር፡፡

  

 EMAIL:  mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic