>

"የአዲሱ ውሁድ ፓርቲ ምስረታ ህጋዊ መሰረት የለውም!!!" (አቶ በቀለ ገርባ)

“የአዲሱ ውሁድ ፓርቲ ምስረታ ህጋዊ መሰረት የለውም!!!”
 
የኦፌኮ ም/ሊቀ መንበር ፌደራሊስቱ አቶ በቀለ ገርባ 
ግዛቸው ናታን.
 በ ኦ.ኤም.ኤን ቲቪ ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት የኦፌኮ ም/ሊቀ መንበር ፌደራሊስቱ አቶ በቀለ ገርባ”ይህ ፓርቲ አዲስ ፓርቲ እንጂ ከኢህአዴግ የወጣ ፓለቲካዊ ፓርቲ ነው ማለት አይቻልም። ስለዚህ በፊት የሌለ አዲስ ፓርቲ ነው የተመሰረተው ማለት ነው ።ይህ ከሆነ ደግሞ እንደ አዲስ ፓርቲ ተመዝግቦ ህዝብ ፊት ቀርቦ ድምፅ አግኝቶ ነው መንግስት መሆን የሚችለው እንጂ በህዝብ የተሰጠው አደራ ትቶ በሌላ መንገድ ሂዶ እንደ ቀድሞ በህዝብ እንደ ተመረጠ መንግስት መንግስት ነኝ ማለት አይችልም ።
የሚገርመው ነገር ግን ቀድሞ የኦሮሞ ህዝብ ይወክል የነበረው ፓርቲ መጥፋቱ ነው ። ያ ፓርቲ ከአሁን ብኋላ የለም ማለት ነው ። መጀመርያ የኦሮሞ ህዝብ ለፓርቲው ድጋፍ ሲሰጠው እና ሲመርጠው አንደኛ አላማው ፣ የሚከተለው ርዕየተ አለምና የፓለቲካ ፕሮግራም አይቶ ነው ። በዚህ ስምምነት ነው ህዝቡ ለፓርቲው ድምፅ የሰጠው:: ነገር ግን ፓርቲው ህዝቡ አምኖ የሰጠው ሁሉ ትክክል አይደለም የሰጣችሁኝም ድምፅ ትክክል አይደለም በማለት ህዝቡን መሪ አልባ አድርገው መንገድ ላይ ጥለው መሄዳቸው በጣም የሚያሳዝን ነው።
በእውነቱ በዚህ መልኩ የሚቀጥል ከሆነና ሌላ ፓርቲ የሚመሰረቱ ከሆነ ያ በህዝብ ስልጣን የተሰጠው ፓርቲ የሚጠፋ ከሆነ አገር የሚያስተዳደር የለም ማለት ነው። በብሄር ፣ በማንነት መሰረት አድርገው የተመሰረቱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ሊጠፉም ሆነ ወደሌላ ሊቀየሩ የሚችሉት የማንነትም ሆነ የብሔር ጥያቄ ምላሽ ሲያገኝ ነው ። የአዲሱ ውሁድ ፓርቲ መስረታ ህጋዊ መሰረት የለውም ።
በመጨረሻም በህዝብ ሃብት የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎች በመጠቀም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የአዲሱ ፓርቲ ፕሮግራም ማስተዋወቅም ሆነ ህዝቡ ፓርቲው እንዲቀበለው ማስገደድ ሊቆም ይገባል በማለት ህዝቡም በሃቡቱ ሊቀለድበት ስለማይገባ በመንግስት ባለስልጣናት እየተደረገ ያለው ድርጊት ሊያስቆም ይገባል በለዋል ።
የመንግስት ባለስልጣናት ዛሬም ሆነ ነገ በመንግስት ሚዲያ ወጥተው መናገር ማቆም አለባቸው :: ከፈለጉ የራሳቸው ሚዲያ አቋቁመው እንደ ፓርቲ ተመዝግበው መወዳደር ይችላሉ::  ነገር ግን በዚህ ህዝብ ሃብት ተጠቅመው ጥዋትና ማታ ህዝቡ አዲሱ ፓርቲ እንዲቀበል መጮህ እና ማስገደድ መቆም አለበት። ህዝብም ይህንን መስማት የለበትም ። እኛ በግድ የምንቀበለው ፓርቲ ሊኖር አይገባም :: ህዝቡም እንደ መድሃኒት በግድ ትውጠዋለህ መባል የለበትም። በንብረታችን ሊቀልዱቡን አይገባም ። ስለዚህ ገንዘባችን መጠበቅ አለብን ።”
Filed in: Amharic