>
5:13 pm - Thursday April 19, 4942

ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር:- በየመንና ስዑዲ ዓረብያ ድንበር በከባድ መሳርያ ድብደባ እየደረሰባቸው ስላሉ ዜጎች ኣስቸኳይ የሂወት ኣድን ጥሪ!!!

ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር:- በየመንና ስዑዲ ዓረብያ ድንበር በከባድ መሳርያ ድብደባ እየደረሰባቸው ስላሉ ዜጎች ኣስቸኳይ የሂወት ኣድን ጥሪ!!!

አምዶም ገብረስላሴ
በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን “በየመንና ስዑድ ዓረብያ ድንበር ኣከባቢ ራጎ በተባለ ሰፈር በከባድ መሳርያ ድብደባ እያለቅን ነው ድረሱልን” እያሉ ይገኛሉ።
ወጣቶቹ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ በረሃና ባህር ኣቋርጠው በየመንና ስዑድዓረብያ የምትገኝ ራጎ የምትባል ኣዋሳኝ የሚገኝ ግዝያዊ መጠልያ ካምፕ ድንኳን ሰርተው ወደ ስዑዲ ዓረብያ ለመሻገር በመጠባበቅ ላይ ነበሩ።
 ይሁን እንጂ ሌሊት ህዳር 11 እና 17/12 ዓ/ም በዚህ መጣ የማይባል ከባድ መሳርያ ድብደባ በላያቸው ላይ ወድቆ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ምውትና ቁስለኛ ሆነዋል።
ለሁለት ቀናት የተካሄደው ድብደባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው ሂወታቸው ያጡ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩም ከፍተኛ የመቁሰል ኣደጋ ደርሶባቸዋል።
በድብደባው ሂወታቸው ካጡና ለቤተሰቦቻቸው መርዶ ከተነገራቸው ወገኖች የተወሰኑት ለመግለፅ ያህል
፩)  እያሱ ከበደ ገ/ድንግል     ሕንጣሎ ወጀራት
፪) ኣባዲ ተሻገር ሓዱሽ         ሕንጣሎ ወጀራት
፫) ዓወት ብርሃኑ በርሀ           ሕንጣሎ ወጀራት
፬) ኣሸናፊ ሓዱሽ ረዳኢ          ሕንጣሎ ወጀራት
፭) እምባይ ሓጎስ በላይ          ሕንጣሎ ወጀራት
፮) ሰሰን ኣታኽልቲ                  ሕንጣሎ ወጀራት ወረዳ ተወላጆች ሲሆኑ በኣፅቢ ወንበርታም ወረዳም ከ46 እስከ 60 ሰዎች መሞታቸው ታውቆ ለቤተሰቦቻቸው መርዶ እየተነገራቸው ይገኛል።
የሞቱት፣ የቆሰሉትና ኣሁንም ከፍተኛ ስጋት ላይ የሚገኙ ወጣቶቹ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የመጡ ሲሆኑ ጉዳት የደረሰባቸው ዝርዝር እየተገለፀ ያለው የሚያውቃቸው ሰዎች ከሰጡት መረጃ ብቻ ነው።
መሞታቸው መርዶ የተነገራቸው ወገኖቻችን የሃዘን(ብፅሖ/ኣገዎር) ለእሁድ 21/03/12 ዓም በሕንጣሎ ወጀራት፣ መሳኑ ቀበሌ ይደረጋል።
በከባድ  ቆስለው ሂወታቸው በኣደጋ ላይ የሚገኙና ኣስቸኳይ የህክምና እርዳታ የሚፈልጉ ዝርዝራቸው ከታወቁት የተወሰኑት ደግሞ
1) ሰለሞን ፀጋይ    ሕንጣሎ ወጀራት
2) ገብሩ ኣሸብር    ሕንጣሎ ወጀራት
3) ለውጡ ንጉስ    ሕንጣሎ ወጀራት
4) ማኣርጉ ጠዓመ  ሕንጣሎ ወጀራት
5) ንጉስ ጠዓመ     ሕንጣሎ ወጀራት
6) መዓዛ ገ/ሄር      ሕንጣሎ ወጀራት
7) ሙሉ ክፍላይ      ሕንጣሎ ወጀራት
8) ምሕረት ካሕሱ    ሕንጣሎ ወጀራት
9) ኣኸዛ በላይ         ሕንጣሎ ወጀራት
10)ሰለሞን ካሕሳይ  ሕንጣሎ ወጀራት
11) ዮሴፍ ነገሰ       ሕንጣሎ ወጀራት
12) ገ/ሄር ገራሰ      ሕንጣሎ ወጀራት
13) መብራህቱ ደስታ  ሕንጣሎ ወጀራት
14) ብርሃነ በርሀ        ሕንጣሎ ወጀራት
15) ህንፃ ገብረ          ሕንጣሎ ወጀራት
16) ከበዶም ብርሃኑ    ሕንጣሎ ወጀራት
17) ፍረ ኣባይ             ሕንጣሎ ወጀራት
18) ኣብራሃ ታደሰ        ሕንጣሎ ወጀራት
19) ሃፍታሙ ተስፋይ   ሕንጣሎ ወጀራት
20) ገ/መድህን ፅጋቡ ሕንጣሎ ወጀራት ስማቸው ለማወቅ የተቸለው ክፉኛ ቆስለው ኣፋጣኝ እርዳታ የሚሹ ናቸው።
በኣሁኑ ወቅትም ተመሳሳይ የሆነ ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችልና የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ስጋት ያደረባቸው በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወጣት ዜጎች ራጎ በተባለች ስፍራ እንደሚገኝ ታውቀዋል።
መዚህ መሰረት
* የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር፣
* የኢትዮጵያ ኤምባሲ በስዑዲ ዓረብያ
* ኢትዮጵያውያንና ዓለማቀፍ ገባሬ ሰናይ ድርጅቶች
* ኣለማቀፉ ቀይመስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበር
*የሃገራችንና ዓለማቀፍ ሚድያዎች በጥቃቱ ትኩረት ኣድርገው የሂወት ማዳን ስራ እንዲሰሩ ጥሪያችን እናቀርባለን ሲሉ በቦታው የሚገኙ ተጎጂዎችና ሃገር ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተማፅነዋል።
መረጃ ማግኘት ለምትፈልጉ ወገኖች
*  ንጉሰ ጠዓመ  +96 77 11 51 83 33 የመን
* ሃይለ ወልደዲዳን 0914564326 ኢትዮጵያ
እንድረስላቸው !
Filed in: Amharic