>

ታጋይ ይለያል ትግል ግን ይቀጥላል (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

ታጋይ ይለያል ትግል ግን ይቀጥላል

መንገሻ ዘውዱ ተፈራ
… አዎ  ባንድ ወቅት በላኩዋት ፅሁፌ በአማራ ክልል አዳራሽ ስለተነገርች ሱስ የምትለዋ ቃል በተመለከተ እስኪ እንረጋጋ ሱስ እኮ በጊዜ ሂደት የሚተው በሽታ ነው ብየ ነበር። አሁን የምንሰማው ከተከስተ አዲስ ነገር አይደለም ልዩነት የነበረ ያለ የሚኖር ነው።ያልነበረ በ27 ዓመታት የተጠናወተን የእኛ የማመዛዘንና ሚዛናዊ ፍርድና ትንበያ መስጠት የተሳነው አስተሳሰብ መላበሳችን ነው።  ዶ/ርዐብይ እኮ በረጀት የተጣደ ዳቦ ነበሩ በረጀት የተጣደ ዳቦስ እሳቱ እንዳይጎዳው ከላይም ከታችም ግለቱን እየተቆጣጠረ የሚቀንስለት አለ። ዶ/ር ዐብይ ግን ያ የለላቸው የግል ሰውአዊ ብሶታቸውን እንኳን የሚያወያዩትየቅርብ ሰው የለላቸው መሆኑ ሊያሳስበን ልናዝንላቸውና ቀድመን ተረድተን በእየምንችለው ልናግዛቸው በተገባ ነበርት። ይህ ለእሳቸው ብለን ሳይሆን ለእራሳችን ብለን። ይህን አላደረጉም ብለን በወነጀልናቸው ቁጥር እስኪ ለደቂቃ ቆም ብለን ዙሪያውን ሰይፍ ተመዞባቸው ይህን በል ይህን አድርግ እየተባሉ የሚኖር ያህል ጫና ቢኖርባቸው ነው ብለን አስበነው እናውቃለን? እንዲህ ጊዜው ሲደርስና እዉነቱ ሲወጣ ከመፀፀት።እንደእኔ አሁንም ግምታዊ በሆነ ጉዳይ ጊዜ ከምናጠፋና ሐገራችንም ከምናጎሳቁል ቢያንስ ውስጡ ሳያስጨንቀን ሁልጊዜ እንዲህ ሲደርስ የምናስብበት ሆኖ አሁን ከአንደበታቸው ብቻ ለሚወጡት ቃሎች ብለን የሚቻለንን በማድረግ ኢትዮጵያን ለማዳን እንስራ።
በመሆኑም ሁላችን ሐገር ወዳድ ባለችን ትንሽ አቅም በእያለንበት በእየአካባቢያችን ያለውን ፊሽካ ሲነፋ ለኃይል እርምጃ የሚንቀሳቀስ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን ኢትዮጵያንና እኛን ኢትዮጵያዊያንን በሚጠቅመው ብቻ እየተነጋገርን እየተማማርን መናናቅን ትተን በነበረ የመደማመጥና የመከባበር ባህል በልዪነት መሀል ያለውን አንድነት እየተጠቀምን ልዩነታችን ለማጥበብ እንስራ። ለስልጣን ብቻ የተኮለኮሉ የፖለቲካ ድርጅቶችንና ስብስቦችን ከተበጠበጠች አገር ከሚገኝ ስልጣን ሰላሙዋ ከተረጋገጠ አገር ያለ የቀን ሠራተኛ የተሻለ መሆኑን በማስረዳት ሐገርንና ወገንን እንዲያስቀድሙና እንዲሰባሰቡ ይመከር ይሰራ።
ይህ ከሆነ ከስልጣን ጥመኞች በስተቀር እኛ ኢትዮጵያዊን በህሊናችን የምንስላትንና ነፍስና ስጋችን የሚመኛትን ኢትዮጵያን ለማግኘት እንደምንችል እናስብ ሳንጠራጠር እንስራ።ታጋይ ይለያል ትግል ግን ይቀጥላል። ትልቁ ቁምነገር የትግሉ ደጋፊዎች ልንከተለው የሚገባ የአጋርነት ሚና ነው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ይጠብቅ።
Filed in: Amharic