የመቱ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የዛሬ ውሎና አዳር
ዘመድኩን በቀለ
“ በገዛ ሀገር ስደት ”
• ደወዬ ያነጋገርኳቸው የመረጃ ምንጮቼ የነገሩኝን እንደወረደ አቅርቤላችኋለሁ።
ሀ•
የመቱ ዩኒቨርሲቲ የዐማራ ነገድ ተማሪዎችን ፊርማ አስፈርሞ፣ ፎርም አስሞልቶ ከዩኒቨርሲቲው ቅጽር ጊቢ አሰውጥቶ አሰናብቷቸዋል።
•ሁ
የዐማራ ነገድ ተማሪዎችም ዝናብና ብርድ፣ ውርጭም እየተፈራረቁባቸው ከከረሙበት ስፍራ ወጥተው ወደ የቤተሰቦቻቸው ለመሄድ ጉዞ ጀምረዋል።
ሂ•
ከዩኒቨርሲቲው የወጡት የዐማራ ነገድ ተማሪዎችም በቡድን፣ በቡድን ሆነው ዕቃዎቻቸውን ሸክፈው በስደተኛ መልክ በእግራቸውና በባጃጅ ተሳፍረው ወደ ከተማው መነሃሪያ አምርተዋል።
•ሃ
ተማሪዎቹ መነሃሪያ ከደረሱ በኋላ ግን የመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን መኪና እንዳያቀርብላቸው መታዘዙን ስለገለጸላቸው ተማሪዎቹ በመቱ አውቶቡስ መነሃሪያ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ መስለው፣ ለስደተኞች እንኳ ከሚሰጥ ክብር አንሰው በገዛ ሀገራቸው በሚያሳዝን መልኩ ሜዳ ላይ ፈስሰው ተቀምጠዋል።
ሄ•
ቄሮ ነኝ ባዩ አሸባሪ ሕግ የማይገዛው የኦህዴድ፣ የኦነግና የጃዋር ሠራዊትም መመሪያ ማስተላለፉ ተነግሯል። ምንም እንኳ ዩኒቨርሲቲው የዐማራ ተማሪዎችን ቢያሰናብትም በዐማራ ክልል የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ከዐማራ ክልል ዩኒቨርሲቲ በግድም ቢሆን ወጥተው ወደ ኦሮሚያ ካልመጡ የፈለገ ነገር ይመጣታል እንጂ በመቱ ያሉት የዐማራ ነገድ ተማሪዎች የትም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ተነግሯል።
•ህ
•••
ሆ•
በመቱ አሁን የዐማራ ተማሪዎች ጭንቅ ላይ ናቸው። የደወልኩላቸው ተማሪዎችና የመረጃ ምንጮቼ የሚነግሩኝ ነገር ደስ አይልም። አሁን ተማሪዎቹ ከመነሃሪያ ወጥተው መቱ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተጠልለዋል። የሚሆነውን እየተከታተልኩ አቀርብላችኋለሁ የፌደራል መንግሥቱ፣ የኦሮሚያና የዐማራ ክልል መንግሥታት ለችግሩ በቶሎ መፍትሄ ካልሰጡ በኋላ ለሚፈጠር መጥፎ ነገር ሁሉ በሚዲያ ቀርቦ መግለጨ መስጠት መፍትሄ አይሆንም። ከአሁኑ መፍትሄ ስጡበት።
•••
ወላጆች ምንም ማድረግ የሚችሉ አይመስለኝም። መንግሥታቸውን አምነው ነው ልጆቻቸውን ከሃገር መጨረሻ የላኩት። እነሱም ሄደው ማምጣት አይችሉም። ወደፊት የሚሆነውን አብረን የምንመለከት ቢሆንም ለአሁኑ ግን የሚመለከታችሁ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ኃላፊነታችሁን በጊዜ ብትወጡ መልካም ነው። እንደ ዘንድሮ እንዲህ ለምንም ነገር ደንታ የሌለው መንግሥት ተብዬ አሙቁልኝ የጨቅላና የፍንዳታዎች ስብስብ በታሪክ አንብቤም አላውቅ። አውርቶ አደር ሁላ ቲሽ ሲያስጠሉ በማርያም።
•••
በል ደግሞ አንተ ማነህ መቱ ዩኒቨርሲቲ ነኝ ባዩ ዛሬም ደግሞ “ ዘመድኩን በቀለ የሚባል ፀረ ሰላም፣ ፀረ ሰብል፣ ፀረ ፀራፀር ምንጥስዮ ነው፣ ቅብጥርስዮ ነው ብለህ ወብራብኝ አሉህ።” ችግርህን እዚያው ሜዳ ላይ አስጥተህ እሪሪሪሪ በልብኝ አሉህ።
•••
•••
አንተም ቄሮ ተረጋጋ። በኋላ እንዳይቆጭህ ተረጋጋ !! ምክሬ ነው።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ህዳር 23/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።