እነ መንግሥቱ ንዋይ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸሙት የአገር ክህደት!
አቻምየለህ ታምሩ
መንግሥቱ ንዋይና ግርማሜ ንዋይ የኢትዮጵያ አርበኞችን በግፍ ከመረሸናቸው ባሻገር በኢትዮጵያም ላይ የአገር ክህደትም የፈጸሙ ባንዶች ነበሩ። እነ መንግሥቱ ንዋይን ሲያሞካሹ የኖሩ የ ያ ትውልድ ፖለቲከኞች ስለፈጸሙ የአገር ክህደት ወንጀል ሊነግሩን አይፈልጉም።
ከታች የታተመው ታሪካዊ ሰነድ መንግሥቱና ግርማሜ ንዋይ ስዒረ መንግሥት ባደረጉበት ወቅት እርዳታ እንዲያደርጉላቸው ወደ አዲስ አበባ ስለጋበዟቸው በግብጽ መከላከካ ሚኒስቴር ወታደራዊ ስለላ ምክትል ሚኒስቴር የተመራ 15 አባላት ያሉት የግብጽ ወታደራዊና የስለላ ቡድን ማምነት የሚያወሳ ነው።
ስዒረ መንግሥቱ ከከሸፈ በኋላ በቁጥጥር ስር ውለው በእስር ላይ የቆዩት እነዚህ እነ በነግርማሜ ግብዣ በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ከካይሮ የመጡት በግብጹ ወታደራዊ ስለላ ምክትል ሚኒስቴር የተመሩት የግብጽ ወታደሮችና እያበረሩ ይዘዋት የመጧት የጦር አውሮፕላን ለፈጸሙት ወንጀል ተገቢውን ወታደራዊ ቅጣት ከተቀጡ በኋላ ተዋርደው፣ ጸጉራቸውንና ጺማቸውን እንዳንጨፈረሩ ከኢትዮጵያ ምድር እንዲባረሩ ተደርገዋል።
በነገራችን ላይ እነዚህን በግብጹ ምክትል ሚኒስቴር እየተመሩ እነ ግርማሜ ንዋይን ለማገዝ ከካይሮ እየበረሩ የመጡ የግብጽ ወታደሮች ከነ አውሮፕላናቸው የማረከው የፈጥሮ ደራሽ ፖሊስ አዛዥ የነበረው ኮሎኔል [ኋላ ጀኔራል] ታደሰ ብሩ ነበር። ይህንን እውነት ጀኔራል ታደሰ ብሩ ራሱ ለጀኔራል መርዕድ መንገሻ በወቅቱ በጻፈው ሪፖርት ላይ አረጋግጧል። ጀኔራል ታደሰ ብሩ መፈንቅለ መንግሥቱን እንዴት እንዳከሸፈና እነ ግርማሜን ለመርዳት የመጡትን ግብጾቹን ከነ አውሮፕላናቸው ማርኮ ለምድር ጦር አዛዡ ለጀኔራል ከበደ ገብሬ እንዴት እንዳስረከበ በማተት የጻፈውን በእጃችን የሚገኘውን ይህንን ሪፖርት ትውልድ ይማርበት ዘንድ ወደፊት እናትመዋለን!