>

“ የህወሓትን ለቅሶና እየዬ በጌታቸው ረዳ በኩል ዓየሁት!!!”  (ዘመድኩን በቀለ)

“ የህወሓትን ለቅሶና እየዬ በጌታቸው ረዳ በኩል ዓየሁት!!!”

ዘመድኩን በቀለ
ህወሓት ኢትዮጵያን በዘር ፖለቲካ መርዝ የበከለች መርዘኛ ናት። ህወሓት እንደ አህያዋ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ብላ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ በኢትዮጵያ ምድር የቀበረች አረመኔ ክፉ ድርጅት ናት። አሁን ኢትዮጵያ እየሆነችው ላለው ሁሉ ተጠያቂዋ ህወሓት ናት!!!
አሄሄ የህወሓት ነገር ምንም እንኳ የመጨረሻ መቋጫ ባያገኝም ሥልጣን በኩል እህል ውኃዋ አልቋል። ተፈጥሟልም። ደግሞም ሃያ ምናምን ዓመት በተግባር ተፈትናም ወድቃለች። የአቦን ግብር ሰርቃ ስለበላች በጌታቸው ረዳ በኩል እንዲያው ፈራ ተባ እያለች ትንጫጫለች እንጂ ከዚህ በኋላ እንኳን በኢትዮጵያ ፎለቲካ ውስጥ ሥፍራ የላትም። ተዛዚሙ።
•••
ተፈራርተው ነው እንጂ ይሄ ተረኛው ሁሉ ኬኛውም ህወሓትን በድሮ ቁመናዋ ስለሚያውቃት ዶክኮና ፈርቶ ነው እንጂ አቅም ኖሮት ትንሽ ቆጣ ቢል ዳይፐሯን ጥላ መግቢያ ቀዳዳም አይኖራትም ነበር። ሁለቱም ውቃቢ ስለራቃቸው ተፈራርተው ማዶ ለማዶ ሆመኘነው ሌባ ፣ ቀጣፊ ፣ ሀገር ሻጭ ፣ የቀንጅብ እየተባባሉ ይሰዳደባሉ እንጂ የፌደራል መንግሥቱ እውነተኛና በህዝብ ይሁንታ አግኝቶ የተመረጠ የኢትዮጵያ መንግሥት ቢሆን ኖሮ ትግራይ መቀሌ ሄዶ ወንጀለኞቹን ለመያዝ ሳደክም ራሱ የትግራይ ህዝብ ነበር ከተዘፈዘፉበት የአክሱም ሆቴል በከዘራ እየዠለጠ ማንቁርታቸውን አንቆ ለሕግ የሚያቀርባቸው። የለማ መንግሥት። ሞቱማን ኢንጂሩ ካ። የለም። ሌባ ለሌባ፣ እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ ነው ነገሩ።
•••
እኔ የሚያሳዝነኝ የትግራይ ህዝብ ነው። አጅሪት ህወሓት ያን ሃይማኖተኛና ጨዋ ህዝብ እንዲህ አዋርዳው፣ ቅስሙንም ሰብራው፣ አንገቱንም አስደፍታው አጎንብሶ እንዲሄድ ማድረጓ ነው የሚያሳዝነኝ። ዓባይ ፀሐዬ ለላሰው ስኳር፣ የአድዋው ስብስብ የስብሃት ነጋው ሮያል ፋሚሊ በዘረፈው ብር ምስኪኑ የትግራይ ህዝብ እንዲሸማቀቅ መደረጉ ነው። እሱ ነገሩ ያሳዝናል። አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ ነው የሚባለው። ኢንዴዢያ ነው።
•••
አሁን አሁን የሊቢያው ጋዳፊ ስብሃት ነጋን እየመሰለኝ እቸገራለሁ። ዓባይ ፀሐዬ ሳዳም ሁሴንን፣ የየመኑንም መሪ የሚመስሉኝ አሉ። ደብረ ጽዮን የያዘ ይዞት ፈርቶ እንጂ አዲስ አበባ ሄዶ ቢቀመጥ ደስታው ነው የሚመስለኝ። ሼባዎቹ ወጥረው የያዙት ይመስላል። ብቻ እያንዳንዱ የእጁን እንደ ሥራው መጠን ሳይቀበል አይቀርም። የእጁን ያገኛታል። ህወሓትን ዲያብሎስ ከነ ሠራዊቱ ቢሰለፍ አያድናትም። ህወሓት አይደለም ጃዋር መሐመድን አባዱላን ራሱ ብትማጸን ከፍርድ አያስጥላትም። ህወሓት ወንጀለኛ ድርጅት ናት። ነፍሰ በላ። ሀገር ሻጭ ድርጅት ናት። ህወሓት ኢትዮጵያን በዘር ፖለቲካ መርዝ የበከለች መርዘኛ ናት። ህወሓት እንደ አህያዋ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ብላ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ በኢትዮጵያ ምድር የቀበረች አረመኔ ክፉ ድርጅት ናት። አሁን ኢትዮጵያ እየሆነችው ላለው ሁሉ ተጠያቂዋ ህወሓት ናት።
•••
የአቶ ጌታቸው ረዳን ቃለመጠይቅ ደጋግሜ አየሁት። በጋዜጠኛዋ ውበት ገመናውን ለመሸፈን ሲራወጥ አየሁት። እንደ ወንድ ደፈር ለማለት ይፈልግና ደግሞ ራያነቱ ትዝ ብሎት ዓደዋዎቹ ቢያስበሉኝስ ብሎ ያስብና ፍሬቻ ሳያሳይ ድንገት እጥፍ ሲል አየዋለሁ። ቆጣ ብሎ ለመሳደብ ይሞክርና ደግሞ ሲያስበው ፈራ ብሎ ራሱን እንደ ባህታዊ ሲከስ ይገኛል።
•••
ጌቾ በየዲስኩሩ ከዚህ ቀደም ተጸይፎ “ይህቺ ሀገር” ይል የነበረውን ቃል ወደ “ይሄ ሀገር” አሻሽሎ ሲናገር ተደምጧል። ኢትዮጵያ ሀገሬ ብሎ በእናት፣ በሴት አንቀፅ ባይጠራትም ኢትዮጵያ የሚባለው ሀገር ብሎ በወንድ አንቀጽ ሲጠራው አምሽቷል። ብትንትኗ ይውጣ ሲል እንዳልከረመ አሁን ደግሞ “ ቢያንስ ቢያንስ ተምሬበተላሁ፣ ኢትዮጵያ በሚባለው ሀገር አድጌያለሁ፣ ክፉ ደጉንም አይቻለሁ፣ እኔ በበኩሌ ኢትዮጵያ እንዲፈርስ አልፈልግም” ሲልም ተደምጧል ጌቾ። ህወሓት ሁሉን ነገር በወንድ ጾታ መጥራቷ ግን የጤና አይመስለኝም። እናት ሀገርን የምን ጋሼ ሀገር ብሎ መጥራት ነው። ነውር ነው። ደግሞም ሉጢነት ነው። እናት እናት ናት አከተመ።
•••
አበደን ደግሜ እላለሁ ህወሓት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ዳግም ሥፍራ የላትም። ሥልጣን ኢንጂሩ። ማኔ ቴቄል ፋሬስ።  ኢትዮጵያ ግን ጠላቶቿን ሁሉ አፈር ከደቼ እያስጋጠች አቧራዋን አራግፋ የጠላት ዐይኑ እያየ፣ ጆሮውም እየሰማ ትነሣለች። አከተመ።
•••
ሻሎም !    ሰላም !
ታህሳስ 8/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic