>
10:03 am - Wednesday December 7, 2022

ከወላይታ የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በአካባቢው ውጥረት ሰፍኗል!!! (DW)

ከወላይታ የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በአካባቢው ውጥረት ሰፍኗል!!!

DW Amharic 

ከወላይታ የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ ዛሬ በአካባቢው ውጥረት የነገሰ መሆኑን ከስፍራው የደረሰኝ ማስረጃ ያሳያል። ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ በወጡና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል መፋጠጥ መኖሩንም ማወቅ ተችሏል። መንግስት ከሲዳማው ክስተት ትምህርት በመውሰድ ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲይዘው እና ነገሮች ወደ ግጭት ሳያመሩ በፊት ከሕዝብ ተወካዮች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ እንዲወያይ ለማሳሰብ ያህል ነው።

በአሁኑ ወቅት በደቡብ ከልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የማህበራዊ አግልግሎት መስጫዎች እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸው ተሰምቷል!
ከአካባቢው እየወጡ የሚገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ዛሬ በከተማው መደበኛ አንቅስቃሴዎች አይስተዋሉም፣ አብዛኞቹ የንግድና የመንግስት አግልግሎት ሰጪ ተቋማትም ተዘግተዋል።
የአግልግሎት መስጫዎች እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሊቋረጥ ያቻለው የወላይታ ዞን ራሱን በቻለ የራስ ገዝ አስተዳደር (ክልል) ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ ካለማግኘቱ ጋር በተያያዘ ሁከት „ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ ነው“ ተብሏል።
ይች አገር ከአንድ ግጭት ወደ ሌላ ደም አፋሳሽ ግጭት እንዳትሄድ ቅድመ ዝግጅት እና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የመንግስት ተቀዳሚ ሃላፊነት ነው። መወያየት ከቻልን እዳው ገብስ ነው።
Filed in: Amharic