>

ሙሉ ጦርነት  ዝግጅት [ Conventional War ]!!!  (ሙሉአለም ገብረመድህን

ሙሉ ጦርነት  ዝግጅት [ Conventional War ]!!!

 ሙሉአለም ገብረመድህን
 
ትህነግ/ታሊባን ከነፃ አውጭነት ባህሪው ሳይወጣ ሃያ ሰባት ዓመታትን በቤተመንግሥት ቆይቷል። “አጋር” ብሎ ያቀረባቸው ሁሉ በገቢር ገባር ከማድረግ ባሻገር ስለፍትሃዊ ተጠቃሚነት አሳስቦት አያውቅም። ከዐድዋ ፊውዳል የሚመነጨው የጠባብ ቡድንተኝነት መቆሚያ የሌለው የፖለቲካ ፍላጎት  በፌዴራሊዝም ስም ሲነገድበት ኑሯል።
ዛሬ 1983 አይደለምና የትላንት ብልጠቱንና ሃሳዊነቱን የተረዱ “አጋሮች” ሰልፋችን አንተ ዘንድ አይደለም ብለውታል። ቀዳሚነትን እና የበላይነት መለያው ያደረገው ይሄ ኀይል እንደገና ከተቻለ በተለመደው የፖለቲካ ብልጠት [ ‘የፌዴራሊስቶች ኀይል’ በሚል] ካልተቻለ በአዲስ ጦረኝነት ወደመሀል ፖለቲካው የመመለስ ፍላጎት አለው።
በተለይ ወታደራዊ ዝግጅቱ ሙሉ ጦርነት ለማካሄድ በሚያስችል ቁመና ላይ  ይገኛል። በሁሉም ዞኖች ስር ባሉ ወረዳዎች የሚሊሻ ስልጠናዎች ከአራት ዙር በላይ ተሰጥተዋል። ‘ፀለምት’: ‘አግበ’ እና ‘አዲ ጎሹ’ የኮማንዶ ስልጠናዎችን ጨምሮ የልዩ ኀይል ማሰልጠኛ ካምፖች አሉ። ዛሬ የታሊባን ጦር በኮማንዶ ደረጃ የተዋቀረ ሆኗል። ሁለተናዊ ቁመናው የልዖላዊት ሀገር እንዲሆን ተሰርቶበታል።
 አፈር ገፊው የትግራይ አርሶ አደር ምንም በማያውቀው ሁኔታ ‘ጠላት ከሸዋ ሊመጣብህ ነው’ በሚል trauma ውስጥ ከቶታል።
የልዩ ኀይል አደረጃጀቱ በይዘት ደረጃ በክፍለ ጦርና በሬጅመንት ደረጃ የተደራጀ ነው። የሻምበል አመራሮች ቢኖሩትም በጋንታ ደረጃ ያለው ትጥቅ ሲገለፅ :-
 አንድ ጋንታ አስራ ስድስት የሚደርሱ አባላት ሲኖሩት÷  አስሩ ክላሽ : አራቱ የእጅ መትረየስ: ሁለቱ ስናይፐር እንዲታጠቁ ተደርጓል። ይሄ የታችኛው አደረጃጀት ሲሆን ÷ ከጋንታ እስከ ሬጅመንትና  ክፍለ ጦር  እያደገ የሚሄድ አደረጃጀት አለው። የጸጥታ ኀይል ስምሪቱ የተደራጀና ማዕከላዊ [ command and control ] ያለው አደረጃጀት ነው። ከመከላከያም ሆነ ከፌዴራል ፖሊስ አኩርፈውም ይሁን በጡረታ የወጡ (የትህነግ/ታሊባን) መኮንኖችን በጦር አውርድ ዝግጅት ተጠምደዋል።
ዋና አዛዦቹ ጌታቸው አሰፋ እና ሜጀር ጀኔራል ታደሠ ወረደ ናቸው (ታዴ ነብሴ ከባህር ዳር ሳይቀር መረጃ ያገኛል)
በነገራችን ላይ ታደሰ ወረደ የድምፃዊት ሃይማኖት ግርማ ባል ነው። ሰውየው በከባድ ህመም እየተሰቃየ “ከመሞቴ በፊት የአማራን ትምክህት ካልሰበርኩ” ሲል የነበረውን  ጀኔራል አብርሃ ወ/ማርያምን ተክቶ ሙሉ “ኢታማዡር” ከሆነ ስድስት ወር ሊሆነው ነው። ሳሞራ የኑስ በቀን አልኮል ጨብጦ ‘ባር’ ላይ የሚሰየም የጡረታ ሰው ሆኗል። ሱዳን ‘አላምያ’ የተባለ ቦታ ላይ ከሰጠው ስልጠና በኀላ የረባ ግዳጅ አልተወጣም። ከጌታቸው አሰፋ ጋር ባለበት የግል ቅራኔ ገለል ተደርጓል። ዋና ዋና ቀጣናዎቹ የሚመሩት በሌሎች ነው።
በወልቃይት እና በሁመራ [ምዕራባዊ ዞን ይሉታል] በኩል ያለውን ቀጣና (ግንባር) መቀመጫውን ሽሬ አድርጎ ብርጋዴየር ጀኔራል ምግብ ኃይሌ ይመራዋል።
በአላማጣ እና ራያ በኩል [ደቡባዊ ዞን] ያለውን ቀጣና ብርጋዲየር ኃይለሥላሴ ይመራዋል። ከማይጨው የሚነሳ ቢሆንም የአካባቢው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በኃይለሥላሴ ዕዝ ስር ነው። የኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ያለው አሰላለፍም መሰል አደረጃጀት አለው። በተለይ በተከዜ በኩል እና ከሱዳን ሐምዳይት ጫፍ አንስቶ ያለው  መስመር threat zone ተብሎ ተለይቷል።
ትህነግ/ታሊባን ከጊዜ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ የገባ ቡድን በመሆኑ ÷ ከፖለቲካ እንቅስቃሴው ጎን ለጎን ወታደራዊ አማራጭ ሌላኛው የሙከራ በሩ ነው። ጦረኛ የአፈጣጠር ባህሪው ከብዕር ይልቅ ለብረት እንዲታመን አድርጎታል።
ዝግጅቱ የሙሉ ጦርነት ቢሆንም ራሱ ደፍሮ አይጀመረውም። ሊመጡ ይችላሉ የሚላቸውን ስጋቶች በመለየት ቀድሞ ማምከን ቀዳሚ ግቡ ነው። በመሠረታዊነት ሦስት ጠላት ለይቷል። የፌዴራሉ መንግሥት: የአማራ መንግሥትና የኤርትራን መንግሥት። ሦስቱም ኀይል ባሉበት ተዳክመው እንዲወድቁ ማድረግ ግቡ ነው። ለዚህ ደግሞ የውጭ ግንኙነቶችን ማበላሸት ጨምሮ በአገር ውስጥ  Deep state, Insurgency, Proxy war, Economic sabotage, etc ግራንድ ስትራቴጂዎችን በመለየት አውዳሚ ተልዕኮ ላይ ተጠምዷል። የዚህ ተልዕኮ ዋነኛ ዓላማ በተቻለ መጠን ጦርነቱ ወደ እርሱ እንዳይመጣ ሦስቱ ወደረኞቹ ባሉበት ተዳክመው እንዲወድቁ ማድረግ ነው።
 በዚህ ሁሉ ሂደት በአንድ ነገር እርግጠኛ መሆን ይቻላል።
ትህነግ/ታሊባን የውክልና እንጅ የግንባር ጦርነት አይገጥምም። የጦርነትን ዋጋ ያውቀዋል። በዚህ ሰዓት ጦርነት ውስጥ መግባት ትግራይን ወደ ቅድመ 1983 ድኀነቷ መመለስ እንደሆነ ከሱ በላይ ማንም አያውቅም። ጦርነት መሸከም የሚችል የምርትም ሆነ የምጣኔ ሃብት አቅም የለም። ኢፈርት እንደሆነ የስብሃት ነጋና ቤተሰቦቹ ኃ/የተ/የግ ኩባንያ ነው።
ይሄ በገዛ ፍላጎቱ ላይ ማመፅ ያልቻለ የቁስ ሰቀቀን ውስጥ የወደቀ ቡድን የአፍሪቃ ቀንድ የሠላምና ደኀንነት ስጋት ነው።
ታታሪውና ስራ ወደዱ የትግራይ ሕዝብ ሆይ ዕጣ ፈንታህ በእጅህ ነው። ይሄ ሕግና ፍርድን በእጁ ጨብጦ የኖረ ጦረኛ ኀይል በራስህ ትግል ሊሸነፍ የሚገባበት አስገዳጅ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንዳለህ አስታውሰህ ÷ ሽፍቶቹን በቃ በላቸው!
Filed in: Amharic