>
9:54 am - Saturday November 26, 2022

ታሪክን መሰረዝና መንቀሉ በምትኩ ጥላቻን መዝራቱ ከህወሀት ወደተረኛው ኦዴፓ ተላልፏል! (ኪሩቤል አሳምን)

ታሪክን መሰረዝና መንቀሉ በምትኩ ጥላቻን መዝራቱ ከህወሀት ወደተረኛው ኦዴፓ ተላልፏል!!!

 

ተረኝነት ይዘገንናል፣!

ኪሩቤል አሳምን
ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሊሰጥ የተዘጋጀውን የ”የታሪክ” ኮመን ኮርስ ከአንድ እህቴ  አግኝቼ ሳልተኛ አነበብኩት …ግራም ተጋባሁ…ለምን ታሪክን ማፋለስ እንደተፈለገ እና የሌለ ታሪክ ሊጨመር እንደተፈለገም ግራ ገብቶኛል።
በሰባት ክፍሎች (ዩኒቶች) ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ጥራዝ….እኔ በዋነኝነት ያተኮርኩበት ከክፍል አራት እስከ ስድስት ያለውን ሲሆን የተቀሩት ሶስቱም ቢሆኑ ከስህተት ያልፀዱ  አስቂኝ የሆነ ወሬ የታጨቀባቸው አይነት ናቸው (ለምሳሌ ሉሲ ኦሮሞ ናት የሚል አለ።)
 unit 4
politics ,economy and socio -cultural process from the late 13n to the beginning of 16n c
በሚለው ርእስ ስር ሌሎች ንኡሳን ክፍሎች ይገኛሉ…በኔ እይታ የዚህ ቀልደኛ ፅሁፍ ስህተት የሚጀምረው በዋነኝነት እዚህ ምእራፍ ላይ ነው። ይህ  ክፍል በዋነኝነት በሰለሞናዊ ስርወ መንግስት እና በሙስሊም ሱልጣኔቶች መካከል የነበረው ግጭት ለመዳሰስ የሞከረበት መንገድ.. ቀጥሎ ባለው ክፍል 5 ላይ ከሜዳ አንስቶ ለሚደነጉረው “የኦሮሞ ታሪክ” ማሳመኛ እንዲሆንለት አንዳንድ የታሪክ ተፋልሶዎችን ደንቅሮ አልፏል።
እንደ ሚታወቀው የሁለቱ ከባድ ሚዛን ጦርነቶች ዋና ምክንያት ሀይማኖታዊ ሳይሆን አለም ላይ ቀድመው እንደ ተደረጉ መሠል ጦርነቶች የንግድ መስመርን በሞኖፖል የመቆጣጠር ፍላጎት ነበር…ነገር ግን የዚህ ኮርስ አዘጋጆች ታሪክ ሲያጣርሱ እናያለን።
unit 5 
politics ,economy and socio_ cultural process from the late early 16th to the end of 18th century የሚል ነው። ይህ ክፍል ስድስት ንኡሳን ክፍሎች ሲኖሩት ከክፍል 4 የተገነጠለ መዝጊያ ተጅቶለታል
እዚህ ክፍል ላይ….”population movement ” በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ድሮ በታሪክ የምናውቀውም oromo expansion እና oromo migration ከሀገሪቱ “ኢንዲጂነስ” ህዝቦች ከሆኑት ከነ አፋር እና አዳል ወይም አርጎባ ጋር ነባር የሆነ እና የውስጥ የቦታ ቦታ እንቅስቃሴ ሊያስመስል ይጥራል (ይሄ ደግሞ ፍፁም ቅጥፈት ነው)
በነገራችን ላይ የዚህ ፅሁፍ ደራሲዎች መጤውን የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ አምጥተው የሚደረግሙት እና ወደ ጥንት ሊወስዱት የሚሞክሩበት መነሻ ቦታ ይሄ የሁለቱ ሀይማኖታዊ መሠል ጦርነቶች ወቅትን ነው(እኛ ደግሞ ታሪክ የሚነግረን ይህንን ሰአት ኦሮሞ ከደቡብ ቅጣጫ ለመስፋፋት እንደ ተጠቀመበት ነው)
በተረፈ እዚሁ ክፍል ላይ “የኦሮሞ ህዝብን” መነሻ ሲጠቅስ ከሚያነሳቸው የአፈታሪክ ንግርቶች ውስጥ ኦሮሞ ከሰሜናዊ የሀገሪቷ አቅጣጫ እንደ መጣ ይነግሩናል (በሚያሳዝን ሁኔታ ኑብያን አክሱምን እናም የኤርትራን አንዳንድ አከባቢዎች አካሎ እስከ ናይሎ ሰሀራ አዋሳኝ አከባቢዎች እና እስከ ደቡብ ምስራቅ አፍሪካ እንደ ተንሰራፉ ይነግሩናል) (ይሄ የሚጠቅሱት በሬ ወለደ ምንም ታሪካዊ ማስረጃ የማይቀርብለት ውሃ የሆነ ታሪክ ነው)
እዚሁ ክፍል ላይ በዋላ ለሚፅፉት ድሪቶ (ክፍል 6) እንዲረዳቸው people and state in the region ባሉት ክፍል ውስጥ …ጭራሽ ለአቅመ መንግስት ያልደረሱ (መንግስት የመባል ዩኒቨርሳል ክራይቴሪያን ያላሟሉ) መንደሮችን በመንግስት ስም የሌለ ትልቅ ስምና ግርማ ሰጥተው ፅፈዋል (ይህን ያደረጉት ደግሞ በዋላ ለሚፅፉት የሚኒሊክ “ጭቆና” ተማሪው ቀድሞ አይምሮ ውስጥ “የጠፉ” ብሎ እንዲይዝላቸው ስለ ፈለጉ ነው)
*የገዳን ታሪክ የገለፁበት መንገድ ምክንያታዊ ያልሆነና ከክርስቶስ ልደት በፊት ሺህ አመታትን ያስቆጠረ እንደሆነ ነው (ነገር ግን አንድም ዋቢ ማስረጃ አላቀረቡብ…..ለነገሩ በፃፉት የኦሮሞ ታሪክ ዙሪያ ሁሉ በቂ ማስረጃ አላቀረቡም)
ለማሳየት ያክል እኔ ይህችን ካልኩኝ እናንተ ጠልቃችሁ አንብቡት
unit 6
Internal interaction and external relation in Ethiopia and the horn 1800- 1941
በሚለው ሌላኛው ክፍል ውስጥ ለመስማት የማንፈልጋቸውን ውሸቶች አጭቀውበታል።  ለምሳሌ….ለአመታት አኖሌ ይፍረስልኝ እያለ ሲጮህ የከረመ የአማራ ተማሪ በዚህ ክፍለ ግዜ በግልፅ “ምኒሊክ ጡት እና እጅ እንደ ቆረጡ” የወላይታ ህዝብ ላይም ጄኖሳይድ እንደ ፈፀሙ ይናገራል።
ሌላው የጎንደር አማራን  ስልጣኔ የኦሮሞ ስልጣኔ ለማድረግ ያለ ቅጥ ተሞክሯል።
የነገስታቶቻችን ስራ እና ታሪክ በሚችሉት ሁሉ አሳጥረው በሁለት መስመር እየጨረሱ የኦሮሞን ገፅ በአሰልቺ መልኩ ሲገነቡ ይታያል። የኢትዮጵያን የሺህ ዘመናት ታሪክ በህወሓት እና ኦነጋዊ የመቶ አመት ትርክት ላይ ሊያንጠለጥሉት ተግተዋል።
በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተዘጋጀውን ይህን ሞጁል ያዘጋጁት የአንድ አከባቢ ሰወች ብቻ ሲሆን በፅሁፋቸውም ውስጥ የታሪክ ስርቆታቸውን በአፋን ኦሮሞ ለማለማመድ ሲጥሩ ይታያል..ለምሳሌ
ፅሁፉ የተዘጋጀው በእንግሊዘኛ ሆኖ እያለ
ወሎን… wolloo፣ አፄ በካፋን….baakaaffaa፣ራስ ተሰማ ናደውን….tassama nado፣ ጎጃምን…..gojjaamm፣ ሸዋን…..showa እና የመሳሰሉትን ሌሎች እልፍ ቋንቋን እያወረሙ የማላመድ መንገድ ሲሞክሩ ይታያል።
ሌሎች እውቀቱ እና ግዜው ያላቸው ሰወች ቢያነቡት እልፍ አሳፋሪ ነገር ያገኙበታል። ስለዚህ የተበላሸ እና የሌላ ታሪክ ይዞ የሌላውን በማጥፋት የታሪክ ባለቤት መሆን ስለ ማይቻል ይህ ሞጁል ከመፅደቁ በፊት ሁሉም ሰው ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው እላለሁ።
Filed in: Amharic