>

እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ በነፃ ተሰናበቱ!!! (ዶይቼቬሌ)

እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ በነፃ ተሰናበቱ!!!

ዶይቼቬሌ
ባለፈዉ ሰኔ 15 የተገደሉትን የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትን በመግደል ወይም ከገዳዮች ጋር በአባሪ ተባባሪነት ጥርጣሬ ተከሰዉ የነበሩ የክልሉ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ዛሬ በነፃ ተለቀቁ።የቀድሞዎቹ የአማራ ክልል የፀጥታ ከፍተኛ ባለስልጣናት ብርጌድየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ኮሎኔል አለበል አማረ፤ኮሎኔል በአምላክ ተስፋና ኮማንደር ጌትነት ሺፈራዉ በተጠረጠሩበት የወንጀል ጭብጥ ታስረዉ በገንዘብ ዋስትና የተለቀቁት ባለፈዉ ጥቅምት ነበር።
ተከሳሾች በዋስ ከተፈቱ በኋላም ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን ዛሬ ባሕርዳር ያስቻለዉ  የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን በአራቱ ተከሳሾች ላይ የተመሰረተዉን ክስ የሚያጠናክር የሰዉም ሆነ የቴክኒክ ማስረጃ ባለመገኘቱ አራቱም በነፃ አሰናብቷል። በነፃ ተሰናባቾቹ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብም እንዲመለስ ፍርድ ቤቱ በይኖላቸዋል።
Filed in: Amharic