>

ጥብቅ ምስጢር.... (ዘመድኩን በቀለ)

ጥብቅ ምስጢር ነው!!!
ክብር ለሞጣ ከተማ እስልምና ምክር ቤት አባቶች!!!
ዘመድኩን በቀለ 
* “ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን ተከትሎ 
    መስጊዶች እየተቃጠሉ ነው? ” 
      [ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ]
•••
በሞጣው ጉዳይ የሞጣ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ከፍተኛ ምስጋና ይገባዋል። መንግሥት በአስቸኳይ እርምጃ ካልወሰደ ይህ አሁን ትናንት ያየነው አስጸያፊና የሚወገዝ ድርጊት በሞጣ እንደሚፈጸም አስቀድሞ አውቆ ከሳምንት በፊት አክራሪው የእነ አህመዲን ጀበል የወሃቢይ ቡድን ሊያደርስ ስላሰበው ጥቃትና ውድመት መንግሥት በአስቸኳይና በፍጥነት የሽብር ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት በቶሎ እርምጃ እንዲወስድ ስጋቱን ገልጦ ደብዳቤ ጽፎ ነበር። ደብዳቤው እነሆ እንዲህ ነው የሚለው።
•••
በምስ/ጎጃም ዞን እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት
የሞጣ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት
[ከደብዳቤው በግራ በኩል በአረብኛ በቀኝ በኩል በእንግሊዘኛ የተጻፈ header]
ቁጥር:- ም/ጎ/እስ/ጉ/ም/ቤት-174
ቀን :- 05-01-12
—ለሞጣ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ጽ/ቤት
                 ሞጣ
 ጉዳዩ:- እውቅና እንዲኖራችሁና ክትትል    እንድታደርጉ ስለማሳወቅ
ከላይ በጉዳዩ ለመግለጽ እንደተሞከረው በከተማችን በሚገኘው ማርዘነብ ሆቴል ውስጥ ከእኛ እውቅና ውጭ በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ስም ተደጋጋሚ ስብሰባዎች እየተደረጉ እንደሆነ ለማወቅ የቻልን ሲሆን ይህንንም ለከተማ አስተዳደሩ ጸጥታ ጽ/ቤት ከዚህ በፊት በቃል ያሳወቅን ቢሆንም ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንጻር በጽሑፍ ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ይህ ስብሰባ ከቀድሞ ጀምሮ አራት በአራት አካባቢ በሚገኘው ሼህ አሊ እስማኤል ሱቅ ውስጥ ይሰበሰቡ እንደነበር እና አሁን ላይ ግን በአቶ ሀብታም ጸጋዬ እና ደሴ ወርቁ ሰብሳቢነት ማርዘነብ ሆቴል ውስጥ እየተሰበሰቡ ይገኛል። በዚህም ስብሰባ የት ነው እኔ ከፈለኩ እስልምና ጉዳይን እና የመስጂድ ኮሚቴን ማፈራረስ እችላለሁ። ሼህ ሙስጦፋም ነባሩን ሰው እያባረሩ ነው በማለት ግጭት የሚፈጥሩ ንግግሮችን እንደሚያደርጉ በስብሰባው ከተገኙ ሰዎች አረጋግጠናል።
የዚህ ስብሰባ ዓላማ ሙስሊሙን የሚጠቅም ከሆነ ከእኛ ጋር በመነጋገር ስብሰባቸውን በእስልምና ጉዳይ ቢሮ ውስጥ ወይም መስጂዶች ውስጥ ማድረግ እየተቻለ ሆቴል ውስጥ ማድረጋቸው ሌላ ድብቅ አጀንዳ እንዳላቸው እና ይህም የከተማችንን ሙስሊም ሕብረተሰብ ከመከፋፈል አልፎ ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር ሊያጋጭ የሚችል እንደሆነ የከተማችን እስልምና ጉዳይ ም/ቤት ስራ አስፈጻሚ ባደረገው ስብሰባ ገምግሟል። በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ጸጥታ ጽ/ቤት እና የሚመለከታቸው አካላት ክትትል በማድረግ ወደሌላ ነገር ከመሄዱ በፊት መደረግ ያለበት ነገር እንዲደረግና ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከሰተው ነገር ም/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል።
አላህ አክበር
ጀማል ጌታው
የሞጣ ከተማአስ/እስ/ጉ/ሰብሳቢ
ግልባጭ:-
-ለሞጣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
-ለሞጣ ከተማ አስተዳደር አዴፓ ጽ/ቤት
-ለሞጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት
-ለምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ም/ቤት
-ለአማራ ክልል አስተዳደር ም/ቤት
•••
ለዚህ ነው ለዐማራ ሙስሊም ከፍተኛ አክብሮት ያለኝ። የዐማራ ሙስሊም ሃይማኖቱን አክባሪ ነው የምለውም ለዚሁ ነው። የዐማራ ሙስሊም ኢትዮጵያ ገደል ትግባ፣ ፍርስርሷ ይውጣ አይልም። የዐማራ ሙስሊም ብልህ ነው። የዐማራ ሙስሊም ሃይማኖቱን አክብሮ የሚያስከብር ነው። ቤተ ክርስቲያን በገንዘቡ የሚያንጽ፣ ቤተ ክርስቲያን ሲመረቅ ሰንጋ ሙክት እንኳን ደስ አላችሁ ብሎ ለክርስቲያን ወንድሞቹ የሚያቀርብ  አማኝ ነው። ይሄ የዐማራ ሙስሊም በእነ አህመዲን ጀበሉ ጽንፈኛ ቡድን እንደ “ ሙናፍቂ፣ ሸሪክ፣ መቃብር አምላኪ” ወዘተ የሚል ቅጽል ስም የሚሰጠውም ነው። አይወዱትም። አሁን በወሎ መስገድ አስረክቡን አናስረክብም ያለውን ጦርነት ብታዩ ትገረማላችሁ።
•••
ለማንኛውም ከላይ እንደተመለከትነው በሞጣው ጉዳይ ይሄ እንደሚከሰት የሞጣ የእስልምና ምክር ቤት አስቀድመው ስጋታቸውን በዝርዝር ጽፈው የችግሩን ምንጮች በስም ጠቅሰው ለመንግሥት ያቀረበው የከተማው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምስጋና ይገባዋል።
•••
የእኔ ጥያቄ  ?  
ሀ፥ የክልሉ መንግሥት ከግለሰቦች እንኳ ሳይሆን ከተቋም የደረሰውን የደኅንት መረጃ ለምን ንቆ ችላ አለው?
ሁ፥ በዛው በሞጣ አካባቢ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቃጠሎ ሙከራ በፊት ሌላ ቤተ ክርስቲያን የማቃጣል ሙከራ ሲደረግ እንኳ ለምን ቀደም ሲል የደረሰውን ስጋት ተንተርሶ እርምጃ ለመውሰድና ቅድመ ጥንቃቄ ለመውሰድ አልሞከረም።
ሂ፥ መልካም እንቀጥል ፥ መስጊዱ ከመቃጠሉ በፊት ልክ ቤተ ክርስቲያኑ እሳት እንደተነሳ ለምን ወዲያው በአስቸኳይ የጸጥታ ኃይሉን አሰማርቶ ቤተ እምነቶቹ እንዲጠበቁ አላደረገም። በጅጅጋ በአብዲ ኢሌ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ መንግሥት መስጊዶችን በወታደር ከብቦ ይጠብቅ የነበረው ለምን ይመስልሃል? ክርስቲያኖች ቢቃጠልባቸውም ለፈጣሪ ነግረው መልሰው ለማሠራት ይንቀሳቀሳሉ እንጂ ሌላ ምንም እንደማያመጡ ስለሚያውቅ አይደለምን? አሁን በሞጣ መስጊዱ በደንብ እስኪቃጠል መንግሥት ወታደሮቹን ለምን ደበቀ?
ሃ፥ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች የአራተኛና የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች “ ከኦሮሚያ ዩኒቨርስቲዎች ወንድም እህቶቻቸው መፈናቀል፣ መገደል፣ መባረሩ ይብቃቸው ብለው እስራስና ደብተር ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ ህጻናቱ ላይ ተኩስ ከፍቶ የረፈረፋቸው የክልሉ ፖሊስ ይሄን የመሰለ ከባድ ወንጀል የያዘ መረጃ ደርሶት ለምን ዝም አለ?
ሄ፥ ቃጠሎው እየተፈጸመ በፕሮፌሽናል ካሜራ አመቺ ስፍራ ይዞ ለኦኤምኤን ይቀርጽ የነበረው ማነው? በዚያ ቀውጢ ሰዓት አንግሉን የጠበቀ ፕሮፌሽናል ቀረጻ በማን ነው የተካሄደው? በሐረርጌ አብያተ ክርስቲያናት ወድመው ሳለ በቴሌቭዥናቸው ቀርበው አንድም ቤተ ክርስቲያን አልተቃጠለም ብለው የለፈፉት ኦኤም ኤኖች የሞጣውን እንዴት በፕሮፌሽናል ካሜራ ሊቀርጹት ቻሉ?
ህ፥ እስከ አሁን ድረስ የክልሉ መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ?
ሆ፥ አደጋው ከተፈጸመ በኋላ የአክራሪዎቹ ኡስታዞችና ጭፍሮቻቸው ለምን ቀውጢ ለመፍጠር መራወጥ ፈለጉ? ጉዳዩ የማይመለከተውን ማኅበረ ቅዱሳንን፣ ዲን ዳንኤል ክብረትን፣ እኔንና ልጅ ቢኒን፣ ምህረተ አብን ጭምር ለምን መክሰስ ፈለጉ? እኛስ እሺ ልጅ ቢኒ ምን አድርጎ ነው የሚከሱት? አስቀድመው ስለተዘጋጁበት ነው።
•••
መስጊድ ማቃጠል የኦርቶዶክሳውያን በህሪ አይደለም። ሞራሉም የለውም። ያውም የኢትዮጵያ ክርስቲያን ይሄን መቼም መቼም አይፈጽመውም። በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በይፋ እንኳ መቃጠል የጀመረው ግራኝ አህመድን ተከትለው በመጡ የቱርክ ኃይሎች ነው። አሁንም አብያተ ክርስቲያናት የሚቃጠሉት በሐረር፣ በባሌ፣ በአሩሲ በተደራጁ ጽንፈኛ ቡድኖች ነው። የጽንፈኛው ቡድን መሪ ደግሞ አህመዲን ጀበል ነው።
•••
“ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን ተከትሎ 
    መስጊዶች እየተቃጠሉ ነው? ” 
      [ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ]
* ለመስጊድ መቃጠል የቤተ ክርስቲያንን መቃጠል በምክንያትነት ማቅረብ አደገኛ ወንጀልን ወደ ሕዝብ የመጎተት ክፉ ሴራ ስለኾነ ነቃ እንበል፡፡ [ ዲን አባይነህ ካሴ ]
•••
ክርስቲያንነት ሥልጡንነት ነው፡፡ እንኳን ዛሬ ያኔ ጥንት ያኔ በቁጥር ገና ጥቂት ሳሉ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ሳይተናኮል አቅፎ ደግፎ ያኖረ ነባር የኢትዮጵያ ሕይወት ነው፡፡ ሞጣ ላይ እየደረሰ ያለውን የመስጊዶች መቃጠል ከክርስቲያኑ ጋር ለማያያዝ መሞከር ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚባለው ዓይነት ነው፡፡
•••
ስመ ጥር ከሆኑት ኡስታዞች አንዱ አቡበከር አህመድ የመስጊዶችን መቃጠል ሲዘግብ እንዲህ የሚል አደገኛ ቃል አስፍሯል፡፡ “ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በጥንታዊው የጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ቃጠሎ መድረሱን ተከትሎ እየደረሰ ያለው ይህ መስጅዶችን የማቃጠል አጥፊ አካሔድ እጅግ በጣም አስደንጋጭ አሳዛኝም ነው፡፡”
• አንደኛ፡- ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ብሎ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ለመጻፍ ተናጋሪው ማን ነው? ስለ ጉዳዩ ምን ያኸል በዝርዝር የሚያውቀው ነገር ቢኖር ነው?
• ኹለተኛ፡- በመስጊዶች ላይ እየደረሰ ያለው ቃጠሎ ከሞጣ ጊዮርጊስ ቃጠሎ ጋር እንዴት ሊያይዘው ቻለ?  በመስጊዶች ላይ እየደረሰ ያለው ቃጠሎ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ቃጠሎ የተከተለ ነው ሲል ምን ማለት ፈልጎ ነው?
•••
ወዳጄ ከኢሉአባቦራ በሻሻ እስከ ሶማሌ ጎዴ ሰዎቿን በሜንጫ፣ አብያተ ክርስቲያናቷን በእሳት እያጣች ያለችውም ቤተ ክርስቲያን ጽንፈኞችን ታወግዛለች እንጅ እንዲህ እንደ አንተ ወደ ሕዝብ ጠቁማ አታውቅም፡፡ በምንም ዓይነት ሁኔታ የመስጊዶችን መቃጠል ከሙስሊሙ እኩል ክርስቲያኑም እያወገዘ እንደኾነ ጠፍቶህ አይደለም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ለብጥብጥ የሚጋብዝ መልእክት ማስተላለፍ ለማንም አይበጅም፡፡ ስለዚህ ቃልህን አርመው፡፡ ለሞጣ ክርስቲያን ለሞጣ ሙስሊምም ይህንን አንተ አትነግረውም፡፡
•••
ሌላው የአቡበከር ወዳጅ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ደግሞ “ተደራጅተን ራሳችንን እንጠብቅ እንጅ የምን ወደ መንግሥት አቤቱታ ነው” በማለት ጉዳዩን እያግለበለበው ይገኛል፡፡
እናንተ መብት አስከባሪ ነን ባዮች ሳትኖሩ ያለምንም ኮሽታ ስንት ዘመን በኀዘንም በደስታም አብሮ የዘለቀ ልዩ የሕይወት መስተጋብር ባለው ሕዝብ መካከል ጥርጥር በመንዛት ሰላሙን አታውኩት፡፡ በሰላም ይኑርበት! ከጸጥታው ባሕር አታነዋውጹት፡፡ እዚያ ላለው ሙስሊም ከእናንተ ይልቅ ኦርቶዶክሱ ይቀርበዋል፡፡ በማለት ዲያቆን አባይነህ ጦማሩን ያጠቃልላል።
•••
#ማስታወሻ | ~ ይሄን የጽንፈኞች ጩኸቴን ቀሙኝ ሴራ የሁለቱም እምነት ተከታዮች በጥንቃቄ ሊከታተሉት ይገባል። የኦሮሚያን ኬዝ ወደ አማራ ክልልና ወደ ሌሎች ክልሎች ስበው ለማስገባት የሚደረጉ ጥረቶችን ህዝቡ በንቃት በቤተ መቅደሱም፣ በመስጊዶች ጭምር በማደር ሴራውን ሊያከሽፍ ይገባል። መንግሥትም ጥፋተኞችን በፍጥነት ለፍርድ በማቅረብ አጥፊዎችን አስተማሪ ሕጋዊ ቅጣት ሊጥልባቸው ይገባል። የቀረውን ነገ እንነጋገራለን።
—-
በዝርዝር እመጣበታለሁ  !! አቋሜንም እገልጻለሁ። አሁን ቸልተኛው የክልሉ መንግሥት ለምን ይሄ ትርምስ እንዲፈጠር እንደፈለገና ዝም ማለትን እንደመረጠ መልስ እስኪሰጠን እንጠብቃለን። በሁለቱም ቤተ እምነቶች ላይ ጥቃት ያደረሱትን አካላትም ለይቶ በመያዝ በአስቸኳይ ለፍርድ ያቅርብ።
••.
በፅንፈኛው የአህመዲን ጀበል ሠራዊት የሚከመረውን የውሸት ተራራ በጽሑፍ፣ በማስረጃ መልስ እየሠጠን ከመናድ በቀር ሌላ ወላ ሃንቲ ነገር አታገኙብንም። ሰማእትነት አያምልጥህ ብለው ለሞት የሚዘጋጁ አባቶቻችን ልጆች ነን። እናም አንፈራም። በነፃነት ለሀሰት ዶሴ ምላሽ በመስጠት ትርክቶቹን ገለባ ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት ግን እንቀጥላለን።   የውሸት ትርክቱን ከመናድ ወደ ኋላ እንደማልል በድጋሚ አረጋግጥላችኋለሁ።
•••
ሻሎም !   ሰላም  !
ታህሳስ 10/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic