የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በወቅታዊ ሁኔታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በወቅታዊ ሁኔታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መግለጫ

.
በመላው ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በደረሰው ወቅታዊ እና ያልታሰበ ጉዳት በሐዘን ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና ምዕመናት: የኢትዮጵያ እስልምና  ጠቅላይ ምክር ቤት እና የመጅሊስ  አባላት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ወገኖቻችን፦
•
በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ወረዳ  በቤተ እምነቶች  ላይ የቃጠሎ ጉዳት መድረሱን ከተለያዩ  የመረጃ ምንጮች  ሰምተናል። በጉዳቱም  የተሰማንን ልባዊ ሐዘን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እንገልጻለን።
•
የተፈጸመው ድርጊት የሀገራችን ሰላም እና እድገት የማይጠቅም ለዘመናት የቆየ አብሮነት የመኖር ዕሴቶቻችን የሚንድ  መሆኑን መላው ሕዝባችን  ተረድቶ  በተረጋጋ እና በሰከነ መንፈስ ጉዳዩ እስከሚጣራ  በትእግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።
•
ከዚሁም  ጋር  የሚመለከታችሁ የመንግሥት አካላት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት  አስፈላጊው ክትትል እንድታደርጉ  እናሳስባለን።
•
ይኽንኑ ድርጊት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሚመለከተው የመንግሥት  የአስተዳደር :የሕግ እና የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን አጣርተን ይፋ የምናደርግ መሆኑን በአጽንዖት እንገልጻለን።
•
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!!
መ/ር ኃይሉ በላይ
EOTC TV

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.