>

የማንቂያ ደውል !! (ሀብታሙ አያሌው)

የማንቂያ ደውል !!

ሀብታሙ አያሌው

ለመሆነ  ወደ ደሴ በማቅናት የአማራ ክልል አመራሮችን “በጀታችሁን  ለፖሊስ፣ ለልዩ ኃይል እና ለሚልሻ  ደሞዝ አድርጋችኋል”  ብሎ የወቀሰው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዴት ነው ? ሰላም ነው ? 
የኦሮሚያ ክልል  ፖሊስ ኮሚሽን በግልፅ “ጃዋር የኦሮሞ ህዝብ አይን ነው” በማለት በመግለጫው ማሳወቁ የቅርብ ሳምንታት ዜና እንደነበረ እናስታውሳለን።  ታዲያ በኦሮሚያ የፖሊስ ኃይል መጠናከር ሰላም ወዳዱን ህዝብ ቢያሰጋው እንዴት ለምን ይባላል ?   የጃዋር ሰይጣናዊ ተግባር የሚያሰጋው ሁሉ  በኦሮሚያ የልዩ ኃይል  ፖሊስ መበራከት በስጋት ብቻ ሳይሆን በጥንቃቄም ሊያየው ይገባል።  የኦነግ ሰራዊት  ተሰብስቦ በይፋ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል መሆኑስ እንዴት ሊዘነጋ ይችላሎ ?
“ነፍጠኛን በሰበረን ቦታ ሰብረን አዲስ አበባን የኢሬቻ ማክበሪያ አደረግን …”  የሚል ጥላቻ የተጠናወተው ሰው በሚመራው ክልል፤  የኢትዮጵያን ሰንደቀ ዓላማ አቃጥሎ የኦነግን ባንዲራ የሚሸከም ፖሊስ ሲበራከት በስጋት ማየት ምክንያታዊ ስጋት መሆኑን ልናሰምርበት ይገባል።
በቅርቡ መንገድ ከሚዘጋ ቄሮ ጋር በጋራ ተሰልፎ ከጎጃም አዲስ አበባ የሚያስገባውን መንገድን ሲዘጋ የነበረው የኦሮሚያ ፖሊስ ሲጠናከር  የልዩ ኃይል ክንድ ሲፈረጥም መስጋት ከምክንያታዊነትም በላይ ነው።
                                 ***
በአንድ ዙር በትንሹ 5000 ልዩ ፖሊስ ይሰለጥናል ቢባል በ29 ዙር የሰለጠነ 145 ሺህ ልዩ ሐይል ኦሮሚያ አላት ማለት ነው።
የዛሬን አያድርገውና ዶክተር አቢይ ጠ/ሚ/ር እያለ በነበረበት ጊዜ ቢሆን ኖሮ «በጀቱን ለልዩ ፖሊስ ስልጠናና ለመሳርያ ግዢ እየጨረሱት…!» ብሎ መስተዳድሩን ኩም ያድርግልን ነበረ!
Oh ….! ለካ ዶክተር አቢይ አሁንም ጠ/ሚ/ር ነው… ጀነራል አሳምነው ፅጌ ነፍስ ይማር !!
Filed in: Amharic