>
11:04 pm - Sunday August 7, 2022

አገራችን ወዴት እያመራች ነው? (ሰለሞን ወልዳዬ)

አገራችን ወዴት እያመራች ነው?

 

ሰለሞን ወልዳዬ
 
ይህ መልእክት ስለ አገራችን ህልውና ስለመኖርና አለመኖር  ቀጥታ የተመለከተ ይሆናል::
ስለኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በቅዱስ ቁራን እንዲሁም በታሪክ ብዙ ተብሉዋል ::በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜ ማባከንና መድገሙ አላስፈላጊ ይመስለኛል:: ስለሆነም የዚህ መልእክት ዋናው ቁምነገር 1ኛ) አገሪቱ ብሁኑ ወቅት ወዴት እያመራች ነው ያለችው? 2ኛ) ቀጥሎስ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ተረድተናል ወይ? 3ኛ) ሊድርስ ለሚችለው አደጋ መፍትሄ አስበናል ወይ?
አገራችን ወዴት እያመራች ነው?
በአለም ላይ የግፍ ውንጀል ታሪክ በትክክል መዝገብ ላይ መስፈር ቢገባው ላለፉት ሶስት አስር አመታት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተፈጸመው ግፍና ወንጀል  በአለማችን የግፍ ሰነድ ውስጥ የመጀመሪያው ይሆን ነበ:: ሆኖም እውነት በተዛባባት ይህች ግፈኛ አለም ክፋትና ጥፋት በስተቀር ምንም መጠበቅ እንደማይቻል ሁሉንም በገሃድ እየታዘብን እንገኛለን:: ወደ ዋናው ጉዳይ ልመለስና ለመሆኑ አገራችን ወዴት እያመራች ነው? ከዚያ ሁሉ በእሥር መንገላታት: ከዚያ ሁሉ መፈናቀል: ከዚያ ሁሉ ስደት: ከዚያ ሁሉ መሳደድና እንደ እንሰሳ መታረድ: ከዚያ ሁሉ የሰው ልጅ እንደ እንሰሳ ከመሽጥ: ከዚያ ሁሉ ዘር ለይቶ ማምከን ነገሮች ተሻሽለው ሰላምና መረጋጋት ይኖራል መፍትሄም ይገኛል ስንል ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ አሁን አገራችን የደረሰችበት ደረጃ እጅግ በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነው:: የዘርና የሃይማኖት ነገር ጦዞጦዞ ወደ መጨረሻው መተላለቅ ደረጃ ላይ የደረሰበት ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው:: ይህ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ አገሪቱን እንመራለን ብለው በሥልጣን ላይ የተቀመጡት አውቀው ይሁን ከጥበብ ማነስ መፍትሄ አምጭዎች ሳይሆኑ ችግር አባባሾች የጥፋት መልክተኞች ሆነው ተገኝተዋል:: በሃገሪቱ ሕግና ሥርአት ፈጽሞ ባለመኖሩ ዜጎች በሌሊት ሆነበጠራራ ፀሐይ ይደበደባሉ እንደ ከብት ይታረዳሉ:: ክዚህ በኃላ የቀረው በሩዋንዳ: በሶሪያ: የርስበርስ: በኢራቅ እንዳየነው የእርስበርስ መጠፋፋት ብቻ ነው::
ቀጥሎስ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ተረድተናል ወይ?
ቀጥሎም የዚህ ሁሉ መጠፋፋት ፕላን ተጠቃሚዎቹ ኢትዮጵያውያን ሳንሆን ከኃላ ሆነው ይህንን ፕላን አስፈጻሚዎቹ ናቸው:: ለነገሩ በከፍተኛ ደረጃ ተጎጂው ተራው ህዝብ ነው:: ባንዳ ምጊዜም ባንዳ ነው ነጭ መጣ አረብ ከርሳቸውን እስከሞሉ ድረስ  እየተረገጠ ችግር የለባቸውም:: እነዚህ የዘመኑ ዐይነ ጭፍን ደነዝ የባንዳ ጥርቅሞች ካለፈው ታሪክ እንደምንረዳው ትልቅ የሚኮሩቡት ነገር ቢኖር ለጌቶቻቸው ታማኝ መሆን እንጂ ለህዝብና ለሃገ ቅንጣት ስሜት አይሰጣቸውም:: እነዚህ ጎጠኛ ባንዳዎች ስለሃገር የወደፊት እጣፈንታ ስለትውልድ ከዚህ በኃላ ሊመጣ ስለሚሆነው የማሰብም ሆነ መፍትሄ የማቅረብ ምንም ችሎትውም ሆነ ፍላጎቱም የላቸውም እንዲሁ በደመነፍስ በስሜት የሚመሩ ግብዞች ናቸው:: ለዚህም ነው ምንም የማያውቀውን የህብረተሰቡን ክፍል በዘርና በሃይማኖት በፕሮፖጋንዳ ዘመቻ እያጦዙ አገሪቱን እያተራመሱት ያሉት:: ያላወቀ አለቀ ብሎም ተላለቀ ሆነና ስላለፈውም ሆነ ስለነገው የማያውቀው ወንድም እህቱን ተነስቶ ያለምንም ምክንያት ይግድላል መስሎት ነው እንጂ እሱም ነገ በዚያው መንገድ ይጠፋል::
ሊደርስ ክታቀደው አደጋ መፍትሄ አስበናል ወይ?
የጥፋት መባቻ ላይ እንዳለን ለሁላችንም ግልጽ የሆነ ይመስለኛል:: አዋቂና ጠንካራ ህዝብ ምንጊዜም መፍትሄ አያጣም:: ትልቁ ነገር የአጥፊዎችን አመጣጥና አሰላለፍ ጠንቅቆ መረዳትና በተቃራኒው ጥፋትን ለማክሸፍ በዚህ በመጨረሻው ሰአት ጠንክሮ መሥራት ነው:: ይህም ለህዝብና ለሃገር ተቆርቁዋሪ ይሆነ ሁሉ በሃገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ሁሉም በሙያው ተደራጅቶ እነዚህምሙያተኞች ሁሉንም የሚያገናኝ አንድ ማእከል ፈጥረው ባለማቁዋረጥ ጊዜው በፈጠረው የመገናኛ ቴክኖሎጂ በመጠቀም እንዲህ ፊታችን ለተጋረጠብን ችግር መፍትሄ ማምጣት ይቻላል ብዬ ሙሉ እምነት አለኝ::
የአገር አጥፊው ካምፕ በግልጽ የታወቀ ነው!
 ኢሳያስ አፈወርቅና የወያኔ መሪዎች እንዲሁም የነርሱ ቡችሎች ኦነግ/ ኦህዴድ እንድሆነ እስካሁን እየታየ ባለው ያደባባይ ድራማ በግልጽ እንድንረዳ አድርጎናል:: ግን ከሁሉም ለኢትዮጵያ ጥፋት ትልቁን አስተዋጽኦ ያበረከትውና እያበረከት ያለው በአማራ መስተዳደር ስም ህዝብን ያስጨረሰውና አንገት ያስደፋው የወያኔ/ ኦነግ ተላላኪ የሆነው ብአዴን ነው:: ስለዚህ ድርጅት አደገኛነት በተከታታይ ለብዙ አመታት ጽፊአለሁ:: ከዚህ ቀጥሎ ከእንግዲህ ብዙም የምጽፈው ከቶ ይኖረኛል ብዬም አላስብም:: በአዴን በጣም አደገኛ ድርጅት ነው:: ለአማራው ህዝብ ብስቁልናና ለኢትዮጵያ ጥፋት ከማናቸውም የጥፋት መልክተኞች የበለጠ እየሠራ ያለው ይሄው ቡድንነው:: በኔ በኩል የማቀርበው የመረረ ኑዛዜዬ ይህ ነው ወገኖቼ እንድታውቁልኝ እወዳለሁ::
በታሪክ ኢትዮጵያ ወድቃ ተነስታለች ግን ይህ አሁን ያለንበት ጊዜ በጣም አደገኛ ነው:: እግዚአብሔር በቸርነቱ ካሰበን ይህንንም እናልፈው ይሆናል በእርሱ ተስፋ አንቆርጥምና:
Filed in: Amharic