>

“ከዚህ ቦኋላ መታገስ አንችልም!!!" ( ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል)

“ከዚህ ቦኋላ መታገስ አንችልም!!!” 

 

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል 
* “እኛ የትግራይ ህዝብ ተላላኪዎች ነን! ከትግራይ ህዝብ ውጪ ሌላ የሚያዝዘን ምድራዊ ኃይል የለም!!!”
 
… ይሄ ያለንበት መድረክ በጣም ከባድ መድረክ ነው። የትላንት ቂም የቋጠሩና አዳዲስ ተስፈኞች በጋራ ተሰልፈው በትግራይ ህዝብ ላይ ዘመቻ ከፍተው ይገኛሉ። የትግራይ ህዝብን በጣጥሰን ካላዳከምነውና ቀጥቅጠን ራሱን ካላስደፋነው በአገሪቱ እንደፈለግነው መሆን አንችልም ነው እያሉ ያሉት።
የትግራይ ህዝብ ታሪክ ስለሚያውቁ ነው እንደዛ እያሉ ያሉት። ስለሆነም ወደዚህ ኮንፈረንስ ስንጠራቹህ ያልናቹህ እንድትሰሙና የወሰንነው ልትወስኑ ሳይሆን ልንመካከር፣ የጋራ ውሳኔ እንድንወስን፣ በወሰነው ላይም አብረን በአንድ ተሰልፈን እንድንታገል የሚያስችል ውሳኔ ለመወሰን ነው የመጣችሁት።
የትግራይ ህዝብ ከእያንዳንዷ ቀበሌ ጀምሮ ለእያንዳንዱ አደረጃጀቶች ለሁሉም በሚያሳትፍ መልኩ ተወክሏል። ስለዚ የዚህ ምክክር ውሳኔ የትግራይ ህዝብ ውሳኔ ነው። በአገሪቱ እየተደረገ ያለው ሁሉም ሥራ ከህግ ውጪ ነው እየተፈፀመ ያለው። ለዛም ነው እየተፋጠነ ያለው። ይሄ አገር ማፍረስ፣ ህገመንግስት ማፍረስ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እኩል ነው። ለኛ ግን ከዛ የሚያልፍ ነው። ሊቀጠቅጡን፣ ሊያሸማቅቁን፣ በዚህ አገር ጨካኞች፣ ሌቦችና ኮንትሮባንዲስት እየተባልን ልንኖር ካላቸው ፍላጎት ተነስተው እየሰሩ መጥቷል።
 ይሄ ሁሉ ሲያደርጉ እኛ በትዕግስት ሁሉንም እያየነው መጥተናል። እንደዛ ስለሚጠቅም እንጂ እኛ ምንም ማድረግ ስለማንችል አይደለም ዝም ብለን እያየን የመጣነው። እኛ ማድረግ እንችላለን። አሁን ግን እየተባሰ ሄዷል። ከዚህ ቦኋላ መታገስ አንችልም። ለምጣዱ ሲባል የሚል ነገርም የለም። የት ያለ ምጣድ?
አንድነታችን ካጠነከርን ያለው ሁኔታ በፍጥነት የሚያልፍ ነው። እኛ ሁሉም ነገር ማድረግ እንችላለን። ነገር ግን አሁንም ማስተዋል ይጠይቀናል። አንድነት ያስፈልገናል! አንድነታችን ለመበጥበጥ የተላኩ ተላላኪዎች አሉ። ለነዚህ እናባርራቸው። አንዱን ይያዙ። ይሄ ዘመን ፈታኝ ነው። ትግራዋይ ነኝ ያለ ከትግራይ ህዝብ ጎን ይሰለፍ።
ትግራይን እበጠብጣለሁ ያለ ግን ራሱን ያቃጥላል። ትግሉም በውስጣችን ነው የምንጀምረው። ተስፈኞች አሉ፣ እውነቴን ነው መቅለብለብ የሚያበዙ አሉ። እነዚህ ስርዓት ይያዙ። ስርዓት ካልያዙ በነሱ እንጀምራለን። ተባብሶ ስላለ ነው የምደግመው። እነዚህ ተላላኪ እነዚህ ተስፈኞች ስርዓት ካልያዙ በነሱ እንጀምራለን።
 በትግራይ ላይ ደግሞ ለውጥ እናመጣለን። የግድ ለውጥ እናመጣለን። ጀምረነው ነው ያለነው። በዚህ መድረክ ያልገባ ምሁር፣ ነጋዴ፣ ወጣቶች፣ በውስጥ ይሁን በውጪ ያለው ሁሉ ሁኔታውን እያየ ስለሆነ ለትግራይ ምን ላግዝ እያለ ያለው። ሌላ ቀርቶ ከውጭ እንምጣ ወይ ልታሰልፉን የሚሉን አሉ። አትምጡ፣ አንፈልግም ራሳችን እንበቃለን ነው እያልናቸው ያለነው። አእኛ ደግሞ የማንም ተላላኪዎች አይደለንም። እኛ የትግራይ ህዝብ ተላላኪዎች ነን። የናንተ ተላላኪዎች ነን። ዝለሉ ካላቹሁን ምንያህል ብቻ ነው የምንላቹህ። ከትግራይ ህዝብ ውጪ የሚያዝዘን ምድራዊ ኃይል የለም። “
ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
በመቐለ ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ኮንፈረንስ ከተናገሩት የተወሰደ።
Filed in: Amharic