>
5:13 pm - Friday April 20, 3218

ሕወሓት በኢህአዴግነት ዘመን ካፈሩት ሀብት ድርሻውን እንደሚጠይቅ አስታወቀ!! (ሪፖርተር)

ሕወሓት በኢህአዴግነት ዘመን ካፈሩት ሀብት ድርሻውን እንደሚጠይቅ አስታወቀ!!

ሪፖርተር

ከቅዳሜ ታኅሳስ 25 ቀን እስከ እሑድ ታኅሳስ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ አስቸኳይ ጉባዔ የተቀመጠው ሕወሓት ባወጣው የአቋም መግለጫ፣ አራቱ የኢሕአዴግ ድርጅቶች በጋራ ካፈሩት ሀብት ድርሻውን በሕግ አግባብ እንደሚጠይቅ አስታወቀ። ከአዲሱ የብልፅግና ፓርቲ ጋር እንደማይዋሀድ በድጋሚ አስታውቆ፣ ከፌዴራሊስት ኃይሎች ጋር በጥምረት፣ በግንባርና በትብብር አብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ከዚህ በኋላ ከመንግሥትም ሆነ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር የሚኖረው ግንኙነት በሕግና በሕገ መንግሥት መሠረት ብቻ እንደሚሆን፣ ከዚህ ውጪ ያለው ግንኙነት ተቀባይነት እንደማይኖረው ሕወሓት በአቋም መግለጫው አስታውቋል። ሕወሓት ከኢሕአዴግ አራት ድርጅቶች መካከል አንዱና ዋነኛው የነበረ ሲሆን፣ የዛሬ 45 ዓመታት ገደማ በወርኃ የካቲት መመሥረቱ ይታወሳል።

Filed in: Amharic