>
5:13 pm - Sunday April 18, 6117

መንግሥት በአማራ ተማሪዎች ላይ ለሚደረገው ጥቃት የሚያሳየውን ቸልተኝነት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያወግዛል!

መንግሥት በአማራ ተማሪዎች ላይ ለሚደረገው ጥቃት የሚያሳየውን ቸልተኝነት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያወግዛል!

***
በተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርስቲዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ሁሉን አቀፍ ጥቃቶች በጊዜ እንዲታረሙ ንቅናቄያችን በተለያየ ጊዜ መንግሥትን ሲያሳስብና ስለችግሩ ግዝፈትም በተለያዩ መንገዶች ለሕዝብ ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይሄ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ከእለት ወደ እለት ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሱ በመምጣታቸው አብዛኞቹ ተማሪዎች ነፍሳቸውን ለማዳን ሲሉ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ቤተሰብ ተመልሰዋል፡፡ ለጊዜው ቁጥራቸው በውል በማይታወቁ ተማሪዎች ላይ የሞትና የአካል መጉደል አጋጥሟል፡፡
መንግሥት ለጥቃቱ ባሳየው ቸልተኝነት የልብ ልብ የተሰማቸው እነዚህ ጥቃት አድራሾች በደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ 17 (13 ሴትና 4 ወንድ) የአማራ ተማሪዎችን ካገቱ ከአንድ ወር በላይ አልፏቸዋል፡፡ የታጋቱ ተማሪዎች ቤተሰቦች ለአብን እንደገለፁት አጋቾች “መንግሥት አማራ ክልል ያሉ የኦሮሞ ተማሪዎችን ወደ ክልላቸው መልሶ በኦሮምያ ክልል እስኪመድባቸው ድረስ ታጋቾች አይለቀቁም” ተብሎ ተነግሯቸዋል። ለጉዳዩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ንቅናቄያችን በተደጋጋሚ የሚመለከታቸውን አካላት በር ቢያንኳኳም ሰሚ ጀሮ አላገኘም፡፡
ስለሆነም አብን፡-
1. የክልሉ እና የፌደራል መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት በመሥጠት የታገቱ የአማራ ተማሪዎችን በፍጥነት እንዲያስለቅቁና ጥቃት አድራሾችን ለሕግ እንዲያቀርቡ ይጠይቃል፡፡ ሥለጉዳዩም አፋጣኝ ማብራሪያ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡
2. አሁንም በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ሕይወታቸው አደጋ ላይ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች አማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ወይም የተሻለ መረጋጋትና ህግ ማስከበር ስራ ባለባቸው ሌሎች ክልሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው እንዲማሩ እንዲያደርግ ይጠይቃል፡፡
3. በአማራ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወማቸው ብቻ በአማራ “ክልል” ያሉ ዩኒቨርስቲዎች በአማራ ተማሪዎች ላይ የወሰዱትን ጅምላ እርምጃ በፅኑ ያወግዛል፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመልሷቸውም ይጠይቃል፡፡
4. መንግሥት አሁንም ጉዳዩን በቸልታ የሚያልፍ ከሆነና ለጉዳዩ አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ በአማራ ተማሪዎች ላይ ለሚከሰተው ነገር ሁሉ ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን በአጽንኦት ማሳሰብ ይወዳል፡፡
****
የታገቱ የአማራ ተማሪዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
1. በላይነሽ መኮንን ደምለዉ (የ1ኛ ዓመት የእርሻ ምጣኔ ሀብት ተማሪ)
2. ሳምራዊት ቀሬ አስረስ (የ2ኛ ዓመት የጋዜጠኝነት ተማሪ)
3. ዘዉዴ ግርማዉ ፈጠነ (የ3ኛ ዓመት የእርሻ ምጣኔ ሀብት ተመራቂ ተማሪ)
4. ሙሉ ዘዉዴ አዳነ (2ኛ ዓመት የማህበረሰብ ሳይንስ ጥናት ተማሪ)
5. ግርማቸዉ የኔነህ አዱኛ (3ኛ ዓመት የባዮቴክኖሎጂ ተመራቂ ተማሪ)
6. ስርጉት ጌቴ ጥበቡ (የ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ)
7. ትግስት መሳይ መዝገቡ (የ12 ክፍል የመሰናዶ ተማሪ)
8. መሰረት ከፍያለዉ ሞላ (የ3ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራቂ ተማሪ)
9. ዘመድ ብርሃን ደሴ (የሶስተኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራቂ ተማሪ)
10. ሞነምን በላይ አበበ (የ2ኛ ዓመት የጋዜጠኝነት ተማሪ)
11. ጤናለም ሙላቴ ከበደ (የ2ኛ ዓመት የእርሻ ምጣኔ ሀብት ተማሪ)
12. እስካለሁ ቸኮል ተገኝ (የኬሚስትሪ 3ኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪ)
13. አሳቤ አየለ አለም (የ3ኛ ዓመት የእጽዋት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪ)
14. ቢተዉልኝ አጥናፉ አለሙ (የ3ኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራቂ ተማሪ)
15. ግርማው ሀብቴ እመኘዉ (የ3ኛ ዓመት የመካኒካል ምህንድስና ተማሪ)
16. አታለለኝ ጌትነት ደረሰ  (የ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ)
17. ክንድዬ ሞላ ገበየሁ (የ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ) ናቸው።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!
Filed in: Amharic