>
12:09 am - Monday May 23, 2022

ከዶምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ከታገቱ ወር ስላለፋቸው 17 ተማሪዎች አብዝተን እንጩህ!!! (ታደለ ጥበቡ)

ከዶምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ከታገቱ ወር ስላለፋቸው 17 ተማሪዎች አብዝተን እንጩህ!!!

ታደለ ጥበቡ
*ስማኝ’ማ ሴት ልጅ ጫካ ውስጥ ተይዛ እየተደፈረች ነው፤  እህትህ ጫካ ውስጥ በኦነግ ሸኔ አሸባሪዎች እየተደፈረች ነው፤ እየደማች ነው፤ እያለቀሰች ነው። ስለእናትህ ስለ እህትህ ስትል ድምጽህን አሰማ።ህንድ ውስጥ አንዲት ሴት በ17 ወንድ ተደፍራ መሬት አንቀጥቅጥ ተቃውሞ እንደነበረ አስታውሳለሁ።
*በአማራ ክልል ትንሽ ነገር ስትፈጠር የዓለም ዜናዎች ያሰራጩታል።የኦሮሞ አመራሮችና አክቲቪስቶች አጥንት እንደያዘ ውሻ “እኝኝ” እያሉ ይከርሙበታል።ኦሮሚያ ክልል  ግን 86 ንጽሃን እንደ አብርሃም በግ ሲታረዱ ሚዲያው ሁሉ ፀጥ-ረጭ ይላል።ቤተ ክርስቲያን ስትወድም ባልሰማ ያልፉታል።ሬሳ ሲጎተት ሃፍረት አይሰማቸውም።አራስ ሴት በድንጋይ ተቀጥቅጣ ስትገደል “ነውር ነው” አይሉም።
*17 ተማሪዎች ከታገቱ ወር አልፏቸዋል።ነገርግን ትምህርት ሚኒስተር፣የፌዴራል ፖሊስ፣መከላከያ ኃይል፣የኦሮሚያ መንግሥት “የምናውቀው ነገር የለም” በማለት በተማሪዎች ህይወት ላይ አላግጠዋል።
*ይኼ ለምን ሆነ ብለን ስንጠይቅ መልሱ አጭር ነው።ተረኝነቱን ለመረዳት፦
1.የጦር ጠቅላይ አዛዥ-ጠሚ አብይ አህመድ
2.የመከላከያ ሚኒስትር  – ለማ መገርሳ
3.የአየር ኃይል አዛዥ —ጀነራል ኃይሉ መርዳሳ
4.ብሔራዊ ደህንነት አዛዥ- አቶ ደመላሽ ወ/ሚካኤል
5.የሪፐብሊኩ ጋርድ አዛዥ—-ኮለኔል ብርሃኑ በቀለ
6.የመከላከያ ም/ኢታ እና ዘመቻ መምሪያ-ጀ/ብርሃኑ ጁላ
7.የኢንሳ አዛዥ- አቶ  ወርቁ
8.ፌደራል ፖሊስ -ኮሚሽነር መላኩ ( ኮሚሽነር መላኩ በፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል እና ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ)
9.ፌደራል አቃቤ ህግ– ብርሃኑ ፀጋዬ
10.የፌደራል ማረሚያ ቤት ኃላፊ–አቶ ጀማል አብሶ
11.የመከላከያ 4 እዞች እያንዳንዳቸው አራት አዛዦች እንዳላቸው ይታወቃል  4×4 =16 ይሆናል።ከዚህ ውስጥ 6ቱ ኦሮሞ ናቸው።አማራ አንድ ብቻ ነው።
*ስለዚህ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሴት ጡት ቢቆረጥ ፣የወንድ ብልት ቢቆረጥ፣ሰው ዘቅዝቀው ቢገሉ፣ሬሳ ቢጎተት፣ሴት ልጅ ብትደፈር፣ሰው ቢታገት ደንታቸው አይደሉም።ምክንያቱም ሁሉም አመራሮች ኦሮሞዎች ናቸው።ሲጠየቁ እንኳን “የምናውቀው የለም” ሲሉ ነው የመለሱት።
*አሁንም ደንቢ ዶሎ ይማሩ የነበሩ 17 የአማራ ተማሪዎች በምዕራብ ወለጋ ጥቅጥቅ ደን እንደታገቱ ናቸው።ከ17ቱ ደግሞ 13ቱ ሴት እህቶቻችን ናቸው።
የስም ዝርዝራቸው፦
1.በላይነሽ መኮንን ደምለዉ
(Auto Economics 1st year)
2.ሳምራዊት ቀሬ አስረስ-Journalist 2nd year
3.ዘዉዴ ግርማዉ ፈጠነ-Auto Economics 3rd
4.ሙሉ ዘዉዴ አዳነ-Sociology 2nd year
5.ግርማቸዉ የኔነህ አዱኛ-Biotechnology 3rd year
6.ስርጉት ጌቴ ጥበቡ-Natural Science 1st year
7.ትግስት መሳይ መዝገቡ-የ12 ክፍል የፕሪፓራቶሪ ተማሪ
8.መሰረት ከፍያለዉ ሞላ- Natural science 3rd year
9.ዘመድ ብርሃን ደሴ-Natural science 3rd year
10.ሞነምን በላይ አበበ-journalist 2nd year
11.ጤናለም ሙላቴ ከበደ-Agro Economics 2nd year
12.እስካለሁ ቸኮል ተገኝ-Chemistry 3rd year
13.አሳቤ አየለ አለም-Plant Science 3rd year
14.ቢተዉልኝ አጥናፉ አለሙ-C/ Science 3rd year
15.ግርማው ሀብቴ እመኘዉ-M/Engineering 3rd year
16.አታለለኝ ጌትነት ደረሰ-Natural Science 1st year
17.ክንድዬ ሞላ ገበየሁ-Natural Science 1st year
መንግስት ተብዬው በተማሪዎች ህይወት እየቀለደ ነው!!!
የኦነግ ሸኔ አሸባሪዎች ተማሪዎችንን አግተው ጫካ ውስጥ እንደተያዙ ናቸው።ለእነዚህ ሴት እህቶችህ ነው ጩህ እያልኩህ ያለሁት።እነዚህ ተማሪዎች እስካልተለቀቁ ድረስ ጭሆታችንን አናቆምም።ዛሬ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ አንድ የወልድያ ልጅ በጩቤ ተወግቶ ህይወቱ አልፏል።ከኦሮሚያ ዩኒቨርስቲ በጠቅላላ የአማራ ተማሪዎች ተፈናቅለዋል።በኦሮሞ ሰዎች የተያዘው የመከላከያ ኃይል፣ፌዴራል ፖሊስ፣ኢንሳ የምናውቀው ነገር የለም በማለት በተማሪዎች ህይወት ላይ ቀልደዋል።ለእነዚህ ተማሪዎች ድምፅ ሁን።ጩሁላቸው።አስፈላጊም ከሆነ የአደባባይ ተቃውሞ መጠራት አለበት።በተማሪዎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለዓለም ህዝብ ማሳወቅ ይኖርብናል።
Filed in: Amharic