>
5:31 pm - Friday November 13, 3722

“አፍሪካዊ ጄት ሲያበር ለመጀመሪያ ጊዜ በማየታችሁ ለምን ትፈራላችሁ? ለምንስ ትጠራጠራላችሁ?” (ካፒቴን አለማየሁ አበበ)

“አፍሪካዊ ጄት ሲያበር ለመጀመሪያ ጊዜ በማየታችሁ ለምን ትፈራላችሁ? ለምንስ ትጠራጠራላችሁ?” 

 
የመጀመርያዉ ጥቁር ፓይለት ኢትዮጵያዊው ካፒቴን አለማየሁ አበበ
ካፒቴኑ በራሳቸዉ በተፃፈዉ “ህይወቴ በምድርና በአየር” በተሰኘ ድንቅ መጽሐፋቸዉ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ገዥዎች ቀንበር ነጻ ለመውጣት በሚታገሉበት በዛ ወቅት ጥቁር ፓይለት በሚያበረው ዘመናዊ ጄት ለመሳፈር እንኳን ለባዕዳን ለወገኖቻችንም ቢሆን መደናገጥን ፈጥሮ እንደነበር ፅፈዋል።
የነጻነት ታጋዩም ኔልሰን ማንዴላ መጀመሪያ ጥቁር  የአውሮፕላን አብራሪ ሲገጥማቸው የተሰማቸውን ድንጋጤ በመፃፋቸው አስፍረዋል
~
” In his memoir, Long Walk To Freedom , Nelson Mandela recounts an incident that occurred early in the anti-apartheid movement on one of his trips to garner support from other African leaders. The incident caused him to experience what he called “a strange sensation” as he was boarding an Ethiopian Airways flight to Addis. He noted that the pilot was black, and because he had never seen a black pilot before, in the instant he saw this pilot, he writes that he had to suppress the panic that arose within him. “How could a black man fly an airplane?” he asked himself.
But a moment later he had caught himself and recounted: “I had fallen into the apartheid mind-set, thinking Africans were inferior and that flying was a white man’s job. I sat back in my seat and chided myself for such thoughts.” Once they were in the air, he lost all of his nervousness and began to study the geography of Ethiopia.”
~
“የአብራሪነት ኃላፊነቱን ከተረከብኩ በኋላ አንዳንድ መንገደኞች አብራሪው ነጭ ባለመሆኑ ከሚያሳዩት መደናገጥ በቀር ምንም እንከን ሳያጋጥመኝ አየር መንገዱ በሚገለገልባቸው አፍሪካና አውሮፓ መብረር ጀመርኩ፡፡ በስልሳዎቹ አሥርተ ዓመታት መጀመሪያ ላይ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ገዥዎች ቀንበር ነጻ ለመውጣት የሚታገሉበት ወቅት ስለነበር ጥቁር ፓይለት በሚያበረው ዘመናዊ ጄት ለመሳፈር እንኳን ለባዕዳን ለወገኖቻችንም ቢሆን መደናገጥን ፈጥሮ ነበር፡፡
ይኸው የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ በረራ አብቅቶ መሬት እንዳረፍን መንገደኞቹ ሲሰናበቱን ከልብ የመነጨ ምሥጋና ያቀርቡልን ነበር፡፡ አንዳንዶች ኢትዮጵያውያንማ ማመኑም እየቸገራቸው ሳይሆን አይቀርም በአድናቆት ይመለከቱንና ያነጋግሩን ነበር፡፡ በተከታታይ በረራዎች የመንገደኞቼ ሥጋትና ጥርጣሬ ወደ መተማመን ተለውጦ ባየሁትና በሰማሁት ቁጥር የሥራ ባልደረቦቼም ሆኑ እኔ ደስታ ይሰማን ነበር፡፡
በሥራ ውጤት እምነት ከማግኘት የበለጠ ምን ነገር ይኖራል እርግጥ ነው ስንት ፈተና በትዕግሥት አልፌ ለዚያ ደረጃ እንደበቃሁ መንገደኞቼ አያውቁም ነበር፡፡
ቢያውቁስ ኑሮ “አፍሪካዊ ጄት ሲያበር ለመጀመሪያ ጊዜ በማየታችሁ ለምን ትፈራላችሁ ለምንስ ትጠራጠራላችሁ?” ብሎ መጠየቅስ ይቻል ነበር? በእኔ ላይ የደረሰው ዓይነት በተከታዮቹ አብራሪዎች ላይም ደርሶ እነርሱም በትዕግሥትና በፅናት አልፈውታል፡፡ ” ሲሉ ካፒቴን አለማየሁ አበበ “ሕይወቴ በምድርና በአየር” በሚል መፅሐፋቸው ፅፈዉታል ።
Filed in: Amharic