>

አህመዲን የጃዋር ስኮርት ነው! (ሃሊማ ከመከንዝባ) 

አህመዲን የጃዋር ስኮርት ነው!

በአህመዲን ጀበል ህግ መሰረት ኦሮሞ ሙስሊም እንጂ አማራ ሙስሊም ጀነት አይገባም!” –

 ሃሊማ ከመከንዝባ 
ጠያቂ ፦ አህመዲን ማጥቃት የፈለገው አማራነትን እንጂ እስልምናን ማዳን አይደለም ብለሽ ታስቢያለሽ ?
እኔ ፦ ይሄንን በቀጥታ አዎ ወይም አይደለም ብየ ከምመልስልህ አንድ በአንድ ተራራዎችን ባፈራርስ እና ፍርዱን ላንተ ብተውልህ ነው የሚሻለው ፤
1.አህመዲንና ኦነጋዊ ጓደኞቹ በኦሮሚያ ለተቃጠሉ መስጊዶችም ሆነ በኦሮምያ ለተፈናቀሉ ሙስሊሞች ምንም ነገር ትንፍሽ ሲሉ አይደመጡም ። ለምን ይመስልሀል? የኦሮሞን አንድነት ይሸረሽራል ብለው ስለሚያስቡ ነው!
ከሀይማኖታቸው ይልቅ ለብሄራቸው ይሳሳሉ ለዛ ነው እንጂ ሀይማኖቴን ብቻ ላለማ እንኳን ኦሮሚያ ውስጥ ለተቃጠለ መስጂድ ፣ አሮሚያ ውስጥ ለተፈናቀለ ምስኪን ሙስሊም ቀርቶ ሳውዲ ውስጥ ለተበደለ አንድ ሙስሊምም ሆነ መስጂድ ተመሳሳይ ስሜት ማሳየት ይጠበቅበታል ።
የኢራኑ ቃሲም ሶሌይማኒም ቢሆን ሰጋጅና ሀይማኖቱን የሚወድ ግለሰብ ነበር አህመዲን ይሄንን ሙስሊም ግለሰብ አሜሪካ ገደለችብኝ ብሎ ሰልፍ መጥራቱ ቢቀርበት እንኳን አሜሪካን አውግዞ መጻፍ ነበረበት ። ግን እሱ ምን በወጣው እቴ ተራራ
ከተራራ ጋር እንዲላተም የሱ ህግ አያዝም! በባሌም በቦሌም ብሎ ኦሮሞነት አማራነትን ያሸንፍለት እንጂ ሀይማኖት ለሱ ቆይቶ የሚመጣ ነገር ነው ።በተግባር ያየሁት ይሄን ነው! !
2.የአህመዲን ተቆርቋሪነት እውነት ለሀይማኖቱ ብቻ ታስቦ ቢሆን ልክ እንደ ኦነግ አጼዎቹን በመርገም ላይ ብቻ የተንጠለጠለ መጸሀፍም አይጽፍም ነበር የየእለት ተግባሩም አጼ ሀይለስላሴን በመርገም አይሆንም ነበር ከዛ ይልቅ በየቀኑ የእስልምናን
አስተምህሮ በደንብ ያስተምረንና ይሰብከን ነበር! ሲጀመር በሀይማኖታችን ቂም በቀልን መስበክ ሀራም ነው አይፈቀድም እሱ ግን ይሄን ጥሶ ያለፈ ታሪክን እያነሳ በየቀኑ ጥላቻን ሲዘራ ይውላል ። እሱን ለመጠራጠር ይሄ ብቻ በቂ ነው ። እንጂ የሞጣ
መስጊድ ሲቃጠል አጼ ሀይለስላሴ አይወገዙም ነበር! ሲቀጥል አጼዎቹንና የኋላ ታሪክን እያነሳ ከከሰሰ ደግሞ የአማራ አጼዎችን ብቻ እያነሳ አይከስም ነበር ።
አጼ ዮሀንስ ለራሳቸው ሀይማኖት ባላቸው አስተሳሰብ ምክንያት ሙስሊሞችን ጨፍጭፈዋል ፣ ግራኝ አህመድ ለራሳቸው ሀይማኖት ባላቸው ቀናኢነትና ሀይማኖታቸውን ለማስፋፋት ባደረጉት ጥረት ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አውድመዋል ። እነዚህ ሁሉ በታሪካችን ሁሉ በጎና መጥፎ ቅልቅል ታሪኮቻችን ናቸው ።
አህመዲን ግን አጼ ዮሀንስም ሆነ  ግራኝ አህመድ አማራ ስላልሆኑ  ሲያቃጥሉና ሲጨፈጭፉ ከኖሩት አጼ ዮሀንስና ግራኝ አህመድ ይልቅ በንግግር አስቀይመውናል የሚላቸውን በአንጻሩ ግን ቁርአንን ወደ አማርኛ የያስተረጎሙትን መስጂዶች እንዲሰሩ የመሰረት ዲንጋይ የሚጥሉትን አጼ ሀይለ ስላሴን ሲደበድብ ይውላል! ለምን ይመስልሀል?
እሳቸው አማራ ስለሆኑ ነዋ! !!!!! ያሾፋል እንዴ!!!
3.በእስልምና ሀይማኖት ሰውን እንደውሻ በሰንሰለት አስሮ ባርያ እያለ መሸጥ ጸያፍ ብቻም ሳይሆን በአላህ ዘንድ ያስቀጣል ።  አባ ጅፋር ይሄን አስነዋሪ ተግባር ሙስሊምም ሆነ ክርስቲያኖች ላይ ሲያደርጉ ነበር! እሳቸውን ግን አህመዲን ምንም ሲላቸው ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ! ለምን ይመስልሀል? እሳቸው ያገሩ የጅማ ልጅ ናቸዋ! እንዴ እሳቸውማ ኦሮሞ እንጂ አማራ አይደሉማ!
በደልና ሀጢያት ለሁሉም የሰው ልጅ እኩል ጽዩፍ የሚሆነው እውነተኛው አንድ አሏህ ጋር እንጂ አህመዲንና ጓደኞቹ ጋርማ የአማራ አጼዎች የተሳሳተ ንግግር አሰቃቂ ሀራም ሲሆን የነ ግራኝ አህመድና የነ አጼ ዮሀንስ ከንግግርም ያለፈ አሰቃቂ ጭፍጨፋ
ሀላል ባይሆን እንኳ ለትችት የሚነሳ ግን አልሆነም አረ እንደውም ጽድቅ ሳይሆን አይቀርም ! ለምን ይመስልሀል? አማራ አይደሉማ! !!!
ጠያቂ ፦ቆይ ግን ከዚህ ሁሉ በፊት የመስጂዶቹን ቃጠሎ ለምን አላወገዝሽም!?
እኔ ፦ ያምሀል እንዴ! ! መስጂዶቹ በመቃጠላቸው እንደኔ ያረረ አለ እንዴ? ያውም የኔ ማረር ሁለቴ ነው ከሌላው ሁሉ ይለያል! በዚህ የምሰግድባቸው መስጂዶቸን አቃጠሉና በዛ በኩል ደግሞ ማንነቴን
ለማቃጠል እየተሯሯጡ እያየሁ እንዴት አልበሽቅም! ማውገዝማ ምን አላት? ማውገዝ እኮ ወግ ነው ዝም ብሎ ንግግር? እኔ ራሴ ተቃጥያለሁ እያልኩህ ነው ከገባህ! ይሄንን ያደረጉ ለሆዳቸው የተገዙ ተላላኪዎችም ሆነ የሀሳቡ አመንጪዎች በህግ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ፈራጅ እኔ ብሆን ፍርዱ ሌላ ነበር ።
ሀይማኖትና ማንነትን ባንዴ ለማቃጠል ነው የተሞከረው ። የዋሁን የአማራ ሙስሊም ከየዋሁ የአማራ ክርስቲያን ነው ለማጫረስ ነው የተሞከረው ። ደጉና የዋሁ የአማራ ህዝበ ሙስሊም ግን
ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ጠይቋል!በዚህም ኮርቻለሁ!!
ጠያቂ ፦ በአንዳንድ ሰልፎች ላይ ደግሞ “አብን ይሰቀል” “የአማራ መጅሊስ ይፍረስ” ሲባል ነበር ይሄ ነገር እንዴት ነው?
እኔ ፦ አይገባህም እንዴ ?  እየነገርኩህ ያለሁት
እሱን እኮ ነው! አላማው ምን ሆነና አብን ይውደም የተባለው ሙሉ ለሙሉ ከጅምሩ አላማው የኦነግ ጃዋር አላማ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ። የአማራ መጅሊስ ይፍረስ የሚሉትንማ እነማን እንደሆኑ ግባቸው ምን እንደሆነ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል!
ጠያቂ ፦ እና አህመዲን ጀበል በሀይማኖት ተከልሎ የጀዋርን አላማ እና ተግባር ለማስቀጠል ነው የመጣው ባይ ነሽ?
እኔ ፦ አሁን በደንብ እየተረዳህኝ ነው! አዎ እንደምታውቀው ጃዋር አክቲቪስትነቱን ተጠቅሞ የመንግስትን መዋቅር ተጠቅሞ የመንግስትን እጅ እየጠመዘዘ አላማውን የሚያሳካበት ጊዜ ተጠናቆ ወደ ፖለቲካ ፖርቲዎች ተቀላቅሏል ። ስለዚህ ይሄንን
የጃዋርን ሚና በአግባቡ የሚወጣ ሌላ ጎረምሳ ተፈለገ እና ተመረጠ ይሄንን የሚያሟላው አህመዲን ሆነ ተገኘ ስለዚህ አህመዲን የጃዋር ስኮርት ነው ። ከዛ በፊትም አህመዲን ለጃዋር የገንፎ ወዳጁ እንደሆነ ማስታወስ አለብህ! በቃ የሆነው ይሄ
ነው!
ጠያቂ ፦ የአማራ አክቲቪስቶችና ፖለቲከኞች የሞጣውን ድርጊት አላወገዙም የሚሉ አንዳንድ ሰዎችን ምን ትያቸዋለሽ? እውነት ነው?
እኔ ፦ ወንድሞቸ የአማራ አክቲቪስቶችማ ከማውገዝም በላይ በጣም ነው ያዘኑት!
 በዚህ እኛ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻቸው የደረሰብንን ድርብ በደል እያሰቡ፣ በዚህ ከየአቅጣጨው ጠላት የሚወረውርባቸውን አጀንዳ እኛን በማይነካ መልኩ ለመመለስ ሲሉ ብርቱ ትግል ላይ ነው የከረሙት!
ጠያቂ ፦ ማንነትሽ አማራ ነው ሀይማኖትሽ ደግሞ ሙስሊም ነው ሁለቱ ይጋጫሉ?
እኔ ፦ በአህመዲን ጀበል ህግ ከሆነ አዎ! በአህመዲን ህግ ኦሮሞ ሙስሊም እንጂ አማራ ሙስሊም ጀነት አይገባም!ዳሩ አማራነትንም ሙስሊምነትንም አዋህዶ ፣ መርጦና መርቆ የሰጠኝ አሏህ ስለሆነ ፣ ልክ እንደ አህመዲን አንዱን ምረጭ ብሎ ሆዴ ላይ የቆመ ፈጣሪ ስለሌለኝ ለኔ አንዱን አጉድሎ መሄድ
ክህደት ነው ። አሏህ ሁለቱንም አንድ አድርጎ ሸልሞኛል ሰጥቶኛል ። ይሄንን ደግሞ የትኛውም አካል በኡስታዝ ስምም መጣ በአሊም ስም ሊነጥቀኝ አይችልም ። አሏህ ብቻ በቂየ ነው !!!!!
ጠያቂ ፦በመጨረሻም ማስተላለፍ የምትፈልጊው ነገር አለ?
እኔ ፦ በደለኞች ለፍርድ ይቅርቡ ! ይሄንን አስታኮ አማራን ለማባላት የሚመጣውን ሁሉ
ጩህትህ ከፍየሏ በላይ ነው ግን የሚሰማህ የለም በልልኝ !!
አመሰግናለሁ !!!
Filed in: Amharic