>

በጅማ ዞን ዛሬም 7 ተማሪዎች በአድማ በታኝ ተደብድበው ታሰሩ!!! (ነጋሲ ራድዮ)

በጅማ ዞን ዛሬም 7 ተማሪዎች በአድማ በታኝ ተደብድበው ታሰሩ!!!

ነጋሲ ራድዮ
 ★ ትናንት የታሰሩትም ፍ/ቤት ቀረቡ!!!
ከትናንቱ የሊሙ ገነት በተጨማሪ በጅማ ዞን በአሰንዳቦ ከተማ በአሰንዳቦ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች  ጅልባብ ለብሰው እንዳይማሩ ሲከለከሉ  ለምን ብለው የተቃወሙ ተማሪዎችም በአድማ በታኝ ፖሊስ ተደብድበው 7 ተማሪዎች ታስረዋል። ከታሰሩት ተማሪዎች መካከል የሚከተሉት በአሁኑ ሰዓት በኦሞ ናዳ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ።
1) አህመዲን ሀጂ ሙሀመድ
2) ሳቢት ሲራጅ
3) ሙዓዝ አባተማም
4) ሙባረክ
5)ሙሀመድ
6) ሪያድ ሀፊዝ
7) ያልታወቀ
በአድማ በታኝ ፖሊስ ድብደባ የተፈጸመባቸው ተማሪዎች ከፊሎቹ  አካላዊ ቁስለትና መቀጥቀጥ ደርሶባቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በአሰንዳቦ ከተማ ዉስጥ አድማ በታኝ ፖሊስ ተበትኖ ሌሎች ተማሪዎችን ለማሰር እንደተሰማራ ተማሪዎች እና የአከባቢው ኢማሞች ይገልጸሉ።
 በተመሳሰይ መልኩ በትናንትናው እለት በጂልባብ/ሂጃብ ምክንያት የታሰሩት ተማሪዎችን ለመጠየቅ የሄዱ ጠያቂዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ታስረዋል። ትናንት የታሰሩት ተማሪዎች ሌሊት ሲደበደቡና ሲገረፉ እንዳደሩ ዛሬ ጠዋት ሲጠይቋቸው እንደነገሯቸው የሚጠቅሱ አሉ። ከአካቢው በደረሰኝ መረጃ የጅማ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቢሮ ሀላፊ አቶ አሸናፊ ትዕዛዝ አማካኝነት በሊሙ ከተማ ጂልባብ ለብሰው በትምህርት ቤቱ አቅራቢ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሴቶች ጭምር ታስረዋል። ከነዚህ በተጨማሪም ከታሰሩት መካከል አንዋር ሙስጠፋ የተሰኘ መምህር ዛሬ የሚገኝ  ሲሆን ከትናንት ጀምሮ እስከ አሁን በሊሙ ገነት ከተማ የታሰሩት 17 የደረሱ ሲሆን ዛሬ ከሰዓት ፍ/ቤት ቀርበው የሰባት ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።
በተመሳሳይ መልኩ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በጅማ ዞን በጢሮ አፈታ ወረዳ በዲምቱ ከተማ ጥቂት የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑና ከሌላ አከባቢ የመጡ መምህራን በተደራጀ መልኩ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ጅልባብ ለብሰው እንዲማሩ ከተፈቀደላቸው እነርሱ ማስተማር እንደሚያቆሙ ማሳሰባቸው ታውቋል። በተጨማሪም የጅማ ዞን አስተዳደር አቶ አብዱልሀኪም ሙሉ እንደሚሉት ከሌላ አከባቢ የመጡ መምህራን የሌላ እምነት ተከታይ ተማሪዎችን ለሙስሊም ሴት ተማሪዎች  ጅልባብ እንዲለብሱ ከተፈቀደ እናንተም ነጠላና መስቀል ያለባቸው አልባሳት ለብሳችሁ ወደ ት/ቤት ኑ በሚል እየቀሰቀሱ እንዳሉ ሪፖርት እንደደረሳቸውና በዞኑ የፀጥታ መዋቅር ዉስጥም ችግር እንዳለ እንደተገነዘቡ ጠቅሰው በቅርብ ቀናት ዉስጥ አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በኦሞናዳ ከተማ ማምሻዉን ጂልባብ የሚለብሱና ሙስሊም ተማሪዎችን ያስተባብራሉ በሚል በዛሬው እለት ቤት ለቤት ተማሪዎችን ፖሊስ እየለቀመ ለማሰር ባደረገው ሙከራ ወላጆች በመቃወመቸው በከተማ የተሰበሰቡ ወላጆችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተተኩሷል።
ከጅማ ዞን የትምህርት ቢሮና የጸጥታ ዘርፍ በተገኘው መረጃ መሰረት ጫናውን በተማሪዎች ላይ በማጠናከርና ወላጆችን በማግባበት የጂልባብ ክልከላዉን ተግባራዊ እናደርጋለን የሚል አቅጣጫ እንዳለ ታውቋል። ከአከባቢው የደወሉልኝ አንድ የመጅሊስ አመራርና የአንዱ ወረደ አስተዳደር እንደሚገልጹት ችግሩ በአከባቢው ባለው የመንግስት የፀጥታና የትምህርት ቢሮዎች መዋቅር ዉስጥ እንደሆነና አመራሮቹ መካከል በሚል የነበረ ልዩነትና ሽኩቻ ምክንያት በአቋም ተለያይተው ችግሩ በተማሪዎች ላይ እየተፈጠረ እንደሆነ ይገልፃሉ።
Filed in: Amharic