አሳዛኝም፣ አሳፋሪም፣ አስገራሚም ዜና ከወደ ሆሣዕና
ዘመድኩን በቀለ
* በሻሸመኔ ሃገረ ስብከቱ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይልቅ ምእመናን የባህርዳር ከነማንና የእስራኤልን ሰማያዊ በነጭ ባንዲራ እንዲያውለበልቡ መክሯል!!!
• ቆሞ ማለቃቀስ የለም። ወደፊት ብቻ !! ዳይ ወደ ዝማሬ፥ ወደ ሥራ፥ ወደ ሽብሸባ !! “ ዛሬም ነገም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!!”
•••
ዐቢይ አህመድ የተባለ በእምነቱ ፕሮቴስታንት የሆነ 7ተኛ ንጉሥ በኢትዮጵያ በነገሠበት ዘመን በከምባታና ጠምባሮ በሀዲያ ዞን በሆሣዕና ከተማ በፕሮቴስታንት ባለሥልጣናት ትእዛዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዩኔስኮ እውቅና የተሰጠውንና ከመላው ዓለም ይሄንኑ በዓል ለማክበረር በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ በሚጎርፉበት ዓመት ታይቶና ተሰምቶ በማያቅ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር በሆሣዕና ከተማ የጥምቀት በዓል አይከበርም።
•••
የጥምቀት ማክበሪያ ሥፍራውን ነጥቀው የቆሻሻ መጣያ፣ የሰገራ ማከማቻ፣ የጉሊት ገበያና ለአውቶቡስ መነሃሪያነት አውለውታል። ወታደሩም፣ ዳኛና ፖሊሱም፣ የመዘጋጃ ሹማምንቱም በሙሉ ዘመኑ የእኛ ነው። ምን አባታችሁ ታመጣላችሁ እንዳሉ ነው የሚነገረው። ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ልጆቿን ሰብስባ መርዶውን አርድታቸዋለች። “ልጆቼ ሆይ ዘንድሮ ጥምቀትን በአደባባይ አናከብርም ማለቷ ነው የተሰማው።
•••
በኦሮሚያ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ መያዝ ባልተጻፈ ዐዋጅ ተከልክሏል። በሻሸመኔ ሃገረ ስብከቱ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይልቅ ምእመናን የባህርዳር ከነማንና የእስራኤልን ሰማያዊ በነጭ ባንዲራ እንዲያውለበልቡ መምከሩ ተሰምቷል። የመከረበት ደብዳቤም በእጄ ገብቷል። በአዲስ አበባም ከኦነግ በቀጥታ ወደ ኦሮሚያ ፖሊስነት የተቀየሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ የለበሱ ፎሊሶች እንዴት የጠላት ሀገር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በእስላማዊቷ ሀገር በኦሮሚያ ይውለበለባል ብለው ሁከት እየፈጠሩ መሆናቸው ታይቷል።
•••
ወዳጄ በግብፅና በሶርያም የመስቀልና የጥምቀት በዓል የአደባባይ በዓላት ነበሩ። እናም ምንአልባትም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ኦርቶዶክሳውያኑ አይደለም በሆሣዕና ከተማ ከአጠቃላይዋ ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ ለማድረግ ሳይሞከር አይቀርም። ማዕተብ በጥስ፣ ነጠላ አትልበስ፣ ጥምቀትና መስቀል አታክብር፣ ሰንደቅ ዓላማ አታውለብልብ ካሉ ነገ ምን ሊሉ እንደሚችሉ መገመት ነው።
•••
ለማንኛውም ፕሮቴስታንት የጌታ ልጆች እንኳን ደስ ያላችሁ። አህመዲን ጀበል ሁለት ዙርባ ጫት በዳንሳ ስም ይጋብዛችሁ። አሜን !!
•••
እንዲህም ሆኖ፥ “ ኢትዮጵያ ግን ታሸንፋለች”
ሻሎም ! ሰላም !
ጥር 8/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ