>

በጥምቀት በዓል በደረሰ አደጋ 14 ምእመናን ሞቱ!!! (አደባባይ ሚዲያ)

በጥምቀት በዓል በደረሰ አደጋ 14 ምእመናን ሞቱ!!!

 

አደባባይ ሚዲያ
 ጥር 11/2012 ዓ.ም፤ Jan 20/2020) በዘንድሮው የ2012 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም በድምቀት ተከብሮ አልፏል።
በበዓሉ ላይ ብዙም የጎላ የፀጥታ ችግር አልተስተዋለም ቢባልም በአንዳንድ አካባቢዎች በደረሰ ጥቃት እና በሰው ሰራሽ አደጋ ጭምር ከ12 በላይ የሁኑ( ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል የሚለው ስጋት እንዳለ ሁኖ) ምእመናን ህይወታቸውን አጥተዋል::
በጎንደር የነበረው የበዓሉ ድምቀት እጅግ ልዩ የነበረ ቢሆንም ይህን ስሜት የሚያደበዝዝ ክስተት በማጋጠሙ ለ10 ሰዎች ሕይወት መጥፋት እና ከ150 በላይ ለሆኑ ወገኖች ደግሞ መቁሰል ምክንያት ሁኗል።
ከአካባቢው የወጡት መረጃዎች እንዳመለከቱት አደጋው የደረሰው ለእንግዶች መተላለፊያ ተብሎ የተሠራው የእንጨት ድልድይ ከአቅሙ በላይ ስለያዘ በመደርመሱ ነው ተብሏል። ከሟቾቹ ውስጥም ስምንት ያህሉ የበዓሉ ታዳሚዎች ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ የፀጥታ አካላት ናቸው ተብሏል። ከቆሰሉት መካከልም ሁለት የውጭ ሀገር ዜጎች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል በአርሲ፣ በሐረር እና በድሬዳዋ ከፍተኛ ረብሻ የፈጠሩ ሰዎች የነበሩ ሲሆን ለበዓሉ የተሰቀሉ ሰንደቆችን በማውረድ እና መንገድ በመዝጋት የተጀመረው ጥቃት ወደ ጥምቀት አክባሪ ምእመናን በመዛወሩ  በአርሲ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።  በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።
ይህን ተከትሎ በሐረር እና ድሬዳዋ በውጥረት ውስጥ ሆኖም ቢሆን ጥምቀት ተከብሮ የዋለ  ሲሆን በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ግን ሳይከበር ውሏል።
በኦሮሚያ ክልል ለተፈጠሩት አለመረጋጋቶች ምክንያቱ በቅርቡ ክሕግ ውጭ  ቅስቀሳ እያደረገ የሚገኘው የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ጃዋር መሐመድ ፓርቲ ( ኦፌኮ) ነው ሲሉ አንዳንድ ወገኖች አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ጥቃቱ በተፈፀመባቸው  በሁሉም ከተሞች  ፖርቲው ከሁለት ቀናት በፊት  ቅስቀሳ ማድረጉን ተከትሎ ነው።
በአርሲ አቦምሳ የከተራ ዕለት የታቦት ማለፊያ መንገዶችን ለማስዋብ ደፋ ቀና ይሉ ከነበሩ ኦርቶዶክሳውያን መካከል በርካቶች በደረሰባቸው ዘግናኝ ድብደባ የአካል ጉዳት ሲገጥማቸው ፪ቱ ግን ለሃይማኖታቸው መሥዋዕት ኾነው አልፈዋል። ከባድ አደጋ የደረሰባቸው ሌሎች ፪ ክርስቲያኖች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
የጠቡ ጀማሪ ፖሊስ ሲኾን እርሱን ለማገዝ የተጠራው የተደራጀ ጽንፈኛ ኃይል ያደረሰው ጥቃት መኾኑ ታውቋል።  የአንድ ክርስቲያን ነዳጅ ማደያ ሙሉ በሙሉ የተቃጠለ ሲኾን እየመረጡ የክርስቲያኖች የኾኑ ፲ ሱቆችንም አቃጥለዋል። በዚህም የተነሣ በአርሲ ዞን ባለችው አቦምሳ በዓለ ጥምቀት በአደባባይ አልተከበረም።
ኦርቶዶክሳውያን ቁጥራቸው አነስተኛ በኾኑባቸው ቦታዎች ሁሉ ከጽንፈኛ ሙስሊሞች ወይም ጽንፈኛ ዋቄ ፈታዎች ወይም በጽንፈኛ ፕሮቴስታንቶች የጥቃት ሰለባ ይኾኑ ዘንድ ተፈርዶባቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጥምቀት በዓል በውጭ ሀገራት ያለ ምንም የፀጥታ ስጋት እና መሰናክል በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
Filed in: Amharic