>
6:52 am - Tuesday December 6, 2022

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የታወጀ ግልጽ ጦርነት!!! (ትርጉም - ዮሀንስ መኮንን)

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የታወጀ ግልጽ ጦርነት!!!

ትርጉምዮሀንስ መኮንን
በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ግልጽ ጦርነት
ታውጆባታል። አገልጋይ ካህኖቿን ለማሸማቀቅ።፣ አስተዳደራዊ መዋቅሯን ለማፍረስ እና ሀብቷን ለመውረስ ታውጆባታል። ሰምቶ መፍረዱን ለአንባቢ ትቼዋለሁ!
 
ይህ ሰው “ዲያቆን” ኃይለሚካኤል ይባላል። የኦፌኮ ሰዎች ገብረጉራቻ ላይ በጠሩት ስብሰባ ላይ ከአቶ ጀዋር ጎን በመሆን በኦሮምኛ ያደረገውን ንግግር በ OMN ተላልፎ አድምጬው እንደወረደ ተርጉሜዋለሁ።
 
ቄሮ! ቀሬ! እንደምን ዋላችሁ?
ይኸውላችሁ ይህ መሬት ሲገለጽ በነበረው መሠረት የታደሠ ብሩ መሬት ነው። ጀነራል ታደሠ ብሩ ለእምነቱ የሚቆረቆር ሰው ነበር።
ኦርቶዶክሳዊነቱ ለራሱ ብሔር እንዳይቆረቆር አላደረገውም።
እንዲያውም ኦርቶዶክስ መሆኑ ለህዝቡ በቁርጠኝነት እንዲታገል አድርጎታል። የኩዩ ቄሮ ኦርቶዶክስ መሆናችሁ ለህዝባችሁ እንዳትቆሙ ሊያደርጋችሁ አይገባም። ከበደ ብዙነሸን ልትጠይቁ ትችላላችሁ።
ምዕራብ ሸዋ ሜታ ላይ ቤተክርስቲያን ኩሩጴ ማርያምን ሠርተዋል። ከበደ በርጋን መጠየቅ ትችላላችሁ። ቤተክርስቲያን የሠሩ ሰዎች ናቸው። ነገር ግን ለህዝባቸው መብት ለመታገል ወደኋላ አላሉም።
* ስለዚህ እንደ ኦሮሚያ ቤተክህነት እኛ የምንፈልገው የኦሮሚያ ቤተክህነት ወይንም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን መስቀል አሳልማ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን የምትተው ቤተክርስቲያን አንፈልግም ። (ጩኸት)
የሌላው ሥነሥርዓት ላይ ተገኝታ የጃዋር ሥነሥርዓት
ላይ የምትቀር ቤተክርስቲያን አንፈልግም። (ጩኸት) በእምነት የምትነጣጥለን ቤተክርስቲያን አንፈልግም። (ጩኸት)
ኦሮሞን በጎሳ የምትነጣጥል ቤተክርስቲያን አንፈልግም። (ጩኸት)
ለምን መሠላችሁ?
ምን ሲሉ ከረሙ መሰላችሁ?
“የቱለማ መሬት የሰሜን ሰዎች መሬት ነው። የአማራ መሬት ነው” ብለው የሚፎክሩ ብዙዎች ናቸው እኮ! “የቱለማ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ ስለሆነ ኦሮሞነቱን ለውጧል። ከዚህ በኋላ ከወንድሞቹ ከእስልምና
ሰዎች ጋር ከፕሮቴስታንት ሰዎች ጋር በአንድነት አይኖርም” የሚሉ ሰዎች ብዙዎች ናቸው። ይህ ይከሽፋል። ይ ከ ሽ ፋ ል!
ዐያችሁ ሰዎች፤ መሬቱ የመገርሣ በዳሳ ነው። የአቡነ ጴጥሮስ መሬት ነው። ይኽ መሬት የአቡነ አኖሬዎስ መሬት ነው። ይኽ መሬት የአቡነ ፊሊጶስ መሬት ነው።
ቄሮ! ቀሬ!
ቤተክርስቲያን ውስጥ እንግዶች አልሆናችሁም? በቋንቋችሁ እያመለካችሁ ነው? እየቀደሳችሁ ነው? የኦሮሞ ቄስ አልጓጓችሁም? የኦሮሞ ዲያቆን አልጓጓችሁም? የኦሮሞ ጳጳስ አልጓጓችሁም? የኦሮምኛ አገልግሎት አልጓጓችሁም? በመሬታችሁ
ላይ የኦሮምኛ ቋንቋን አልጓጓችሁም? ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ባዳ እንደ ሽፍታ አልታያችሁም?
*
– ይህ ከአሁን በኋላ ሙሉ በሙሉ ይቆማል አይቆምም? (ይቆማል)
– ይቆማል አይቆምም? (ይቆማል)
– ከዚህ በኋላ በኦሮምኛ ቋንቋ ይቀደሳል በሉ (ይቀደሳል)
– ይመሠገናል!… (መፈክር ነው)
– ይዘመራል!…
– ይሰበካል!…
– ኦሮሞ አንድ ነው!
– ኦሮሞ አይነጣጠልም!
– ኦሮሞነትን የማይቀበል ኦርቶዶክሳዊነት የለም!
– የኦሮሞን ባህል የማይቀበል ኦርቶዶክሳዊነት የለም!
የኦሮሚያ ቤተክህነት መቋቋም አለበት” በሉ እና እስኪ ለኦሮሚያ ቤተክህነት ሁላችሁም በጭብጨባ ሞራል ሰጡት! (ረጅም ጭብጨባ)
*
ሰላሌዎች!  እናንተ አኮ ሊቃውንት ናችሁ። ለምንድነው ታዲያ እንግዶች የሆናችሁት? በቤተክርስቲያን ውስጥ ለምን እንግዶች ትሆናላችሁ? 
*
እናንተ እኮ የታሪክ ባለቤቶች ናቸሁ። ደብረ ሊባኖስ የእናንተ ነው። … በ11ኛው መቶ ክፍለዘመን ደብረሊባኖስን የመሠረቱት አባ ሊባኖስ ናቸው። ከዚያም አስቀድሞ ጎሐጽዮን ላይ በአብርሃ እና አጽብሃ ዘመን የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጎሐጽዮን ተራራ ላይ ተተክላለች።
*
ግቡ (ወደ ቤተክርስቲያን) ። ስበሩ እና ግቡ። ከእጃቸው ተቀበሏቸው። እጃችሁ አስገቡ። 
እንደ አጠቃላይ፦ ኦፌኮ (ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ) ፓርቲን አስመልክቶ ላስተላልፈው የምፈልገው የሰው ልጅ ሲፈጠር Theologicaly speaking (በትምህርተ መለኮት አነጋገር) የሰው ልጅ ጠባያት ውስጥ የፈለጉትን መምረጥ የሚለው ሀሳብ አንደኛው ነው። ሰው የፈለገውን ይመርጣል።
*
ኦፌኮ ለኦሮሞ ህዝብ እንደምርጫ ሆኖ በመቅረቡ የተሰማኝን ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ። (ረጅም ጭብጨባ)
*
ኦፌኮ ለኦሮሞ ህዝብ አማራጭ ሆኖ በመቅረቡ እንኳን ደስ ያላችሁ! ሁላችንንም እንኳን ደስ ያለን!!!
*
ስለዚህ የሃይማኖት አባቶችም ይሁኑ የፖለቲካ ሰዎችም ይሁኑ ለህዝባቸው፣ ለመሬታቸው፣ ለአፈራቸው እስከመጨረሻው ተቆርቁረው አሳይተውናል።
ከአሁን በኋላ ደብረሊባኖስ ላይ የምታዝዙት እናንተ ናችሁ። (ጩኸት)
ከአሁን በኋላ ቤተክርስቲያን ዎስጥ የምታዝዙት እናንተ ናችሁ። (ጩኸት)
ከአሁን በኋላ ቤተክርስቲያን የምትተዳደረው
ከደብረሊባኖስ ተምረው በሚወጡ የኦሮሞ ምሁራን ባለሥልጣናት ነው እንጂ ቤተክርስቲያን በእንግዶች መተዳደር የለባትም።
 
እኔ የምለው !
– ከዚህ በላይ “የጥላቻ ንግግር” አለ?
– የምርጫ ህጉ ይህን “ቅስቀሳ” ይፈቅዳል? 
– ከዚህ በላይ የሕግ ጥሰት አለ?
 
አሁን የጽንፈኞቹ ጭምብል ሙሉ በሙሉ ወልቋል። 
ኦርቶዶክስን የመሰሉ ነባር ሀገራዊ ተቋማትን በማፍረስ እና ማኅበራዊ ሥሪታችንን በመበጣጠስ ሀገር እናፈርስ ይሆናል እንጂ “ዙፋን” አንወርስም።
 
በግሌ እንደ አንድ ግብር ከፋይ ዜጋ ለምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ይህንን የመሠለ የምርጫ ቅስቀሳ ደም አፋሳሽ ስለሚሆን በጊዜ መላ እንዲያበጁለት ትናነት በደብዳቤ በአደባባይ ጠይቄ ነበር። በዚሁ ምክንያት  ከጽንፈኛ ብሔርተኞች የስድብ እና የማስፈራሪያ ውርጅብኝ በገፍ ደርሶኛል።
 
ነገሩ “ዘጠኝ ሞት ከበር ላይ ቆመዋል” ቢሉት “አንዱን ግባ በለው” እንደሚባለው ዓይነት ነው። ቀድሞ ወይንም ዘግይቶ መሞት ቁም ነገር አይደለም! ቁምነገሩ በሕይወት በቆየንባት እድሜ ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቦቿ የሚጠቅም አንዳች በጎ ነገር ሠርተን ማለፋችን ነው !
 
Cc;
– Office of The Prime Minister
– The Federal Supreme Court
– Federal Attorney General
– Ethiopian Human Rights Commission
– የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
Filed in: Amharic