>

ዶ/ር አብይ የእርስዎ ነገር እኮ ግራ አጋባን?!? (ያሬድ ሀይለማርያም)

ዶ/ር አብይ የእርስዎ ነገር እኮ ግራ አጋባን?!?

ያሬድ ሀይለማርያም
• የሉም እንዳሉ አሉ ከመንበርዎ፤ አሉም እንዳንል የሉም ከምግባርዎ።
 
• የሉም እንዳንል ችግኝ ዛፍ እያጠጡ ያስደምሙናል፤ አሉም እንዳንል በአገሪቱ ሥርዓት አልበኝነት ሲነግስ ሕግ ማስከበር ተስኖዎታል።
• የሉም እንዳንል በያዳራሹ ስለ መደመር እና ስለ ብልጽግና ሲሰብኩ እናዮታለን፤ አሉም እንዳንል ዜጎች ሲገደሉ እና ንብረታቸው በመንጋዎች ሲወድም እያዩ ድምጽዎትን ሳያሰሙ ሳምንታት ይሞላ፤
• የሉም እንዳንል የሾሟቸውን ሴት ሚኒስትሮች አስከትለው በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሴቶች መብት ሲደሰኩሩ አይተናል፤ አሉም እንዳንል ለ52 ቀናት ሴት ተማሪዎች ከደንቢዶሎ ዩንቨሪሲቲ በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ያሉበት በማይታወቅበት፣ ቤተሰብ የመንግስት ያለህ ልጆቻችንን አሙ እያሉ ሲያነቡ እና ሕዝብም ድንጋጤና ግራ በተጋባበር ሁኔታ ድምጽዎትን አጥፍተዋል፤
አሉ እንዳንልም፤ የሉም እንዳንልም ግራ አጋቡን። እርሶም ይች ጉደኛ አገር ግራ አጋብታዎት ከሆነ፤ ግራ የገባው መሪና ግራ የገባው ሕዝብ መጨረሻው ስለማያምር በጊዜ የጋራ መፍትሔ መፈለግ ይሻላል።
Filed in: Amharic