>
5:30 pm - Saturday November 2, 0897

አቢይ አህመድ አሊ ቀርጥፎ የበላቸው አማሮች! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

አቢይ አህመድ አሊ ቀርጥፎ የበላቸው አማሮች!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 

በምታምኑት ይሁንባችሁ ጸልዩልኝ፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳልከታተል ልቤ ድፍን ይሆን ዘንድ ጽልዩልኝ፡፡ እንደኤርየል ሻሮል ሰመመን ውስጥ ገብቼ በአርምሞ እንድቆይና ብዙ የደከምኩባትን የውዲቷን ሀገሬን ነፃነት አይ ዘንድ ፈጣሪ እንዲረዳኝ ጸልዩልኝ፡፡ ዕንቅልፍ እያጣሁ እየታመምኩ ነው፡፡ በያ ላይ ያ ደደብ በሽታ ይዞኝ እየተሰቃየሁ ነው – ሌላ እንዳይመስልህ ደግሞ – ደም ግፊት ማለቴ ነው፡፡(አንተ ደግሞ “ጉረኛ” አትበለኝ፤ እመብርሃንን እውነቴን ነው! ለምን እዋሻለሁ? አታቀኝ፤ አላቅህ፡፡)

ይህን ማስታወሻ የምጽፍላችሁ በፍቅር የምከታተላቸውን የዘሀበሻውን ሄኖክ ዓለማየሁንና የጆሲን (ዮሴፍ ይጥና) ዩቲዩብ የዜና ሀተታዎች እየተከታተልኩ ሳለ ነው – አሁን፡፡ ስለሀገራቸው ጉዳይ ግድ ሳይኖራቸው በድንቁርናና ጮማና ውስኪ ባደነቆረው ብልሹ ስብዕና የሚኖሩ ነፍላሎች “ብፁኣን” ናቸው – ከሆዳቸው በስተቀር ሌላ ዘመድ የላቸውምና፤ በነገዋ የነፃነት ቀን ጸጸታቸው ወደር አይገኝለትምናም፡፡

አቢይ አህመድ እንደሚከተለው ዓይነት ሰው ነው፡፡ ዐይንህን ጨፈን አድርግና የአቢይንና የናርሲሰስን ታሪክ ማመሳሰል ነው፡፡ ከዚያ ሁሉም ነገር ይገባሃል፡፡ ደግሞም አትፍራ ወይም በይሉኝታ አትታሰር፡፡ እውነቱን ተናግሮ እመሸበት ማደርን የመሰለ ነገር የለምና በምልህ ነገር እውነተኝነት ተጠራጥረህ እኔን አትውቀስ፡፡ 

ናርሲሰስ የተባለ በራሱ ፍቅር የወደቀ ልጅ ነበር፡፡ ይህ ልጅ የእውተነኛው ዓለም ነፀብራቅ እንጂ በርግጥ በሰው መሀል ግዘፍ ነስቶ በአካል የታዬ የሰው ፍጡር አልነበረም፡፡ በግሪክ ሚቶሎጂ ናርሲሰስ አኝ ነበር፡፡ (“ዳ” ይጥበቅ፡፡) ግሪኮች ለሁሉም ነገሮች አማልክት አሏቸው ወይም ነበሯቸው – ለፍቅር፣ ለአዝመራ፣ ለባህርና ለወንዞች፣ ለጋብቻ፣ ለአርት፣ ወዘተ፣ …፡፡ ናርሲሰስ የሚባለው እንደአህመድ አቢይ መልከ ቀና የነበረ የወንዞች አማልክት ሴፊሰስ ልጅ ራሱን እጅግ ከማፍቀሩ የተነሣ ምስሉን ውኃ ላይ እያዬ ፈዝዞ ይውል ነበር፡፡ አቢይም ሥልጣኑንና በሥልጣኑ ሰበብ የሚገኘውን ክብርና ሞገስ እጅግ ከማፍቀሩ የተነሣ ልክ እንደዚያ የግሪክ አማልክት ልጅ እንደ ናርሲሰስ በራስ ፍቅር ወድቆ ሀገራችንንም እንጦርጦስ ሊከታት በቋፍ ላይ ይገኛል፤ ብልጥና አሰለጥ ሆኖ ሳለ ለአንዳች ጥቅሙ ሲል የዋህና ገራገር መስሎ በተለይ የማያውቁትን በአራዳ ቋንቋ ያገነትራል፡፡ ትንሽ ዕውቀት መጥፎ ነው ወገኖቼ፡፡ የዕውቀት ፆመኞች ቤተ መንግሥትን በጉልበትና በሻጥር እየተቆጣጠሩ ጉድ ሠሩን – ሥጋ በሉ ዐውሬ በጭቃሾህ ምላሱ ስለተቅጠፈጠፈ ዐዋቂ ከመሰለህ ተሳስተሃል – እንደውነቱ ዓለማዊ ዕውቀት ማንም ሊኖረው ይችላል፡፡ ሰይጣንም እኮ ብዙ ትላልቅ ዕውቀቶች ነበሩት – አሉትም፡፡ ችግሩ ወደ ጥበብ ያልተለወጠ ዕውቀት እርባና ቢስ መሆኑ ነው፡፡ By the way we have to understand that there is significant difference among knowledge, information, and wisdom. ይሁንና ራሱ ቀድሞ ይንደባለላል እንጂ ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን ሀገር በመሆኗ ምንም አትሆንም፡፡ እርግጥ ነው – እንደፖለቲካ ሰውና እነሰሜን ኮርያንና ሦርያን ለሚያስታውስ ወገን ይህ ነገር ላይጥም ይችላል፤ ችግራቸውም ይገባኛል፡፡ የሆኖ ሆኖ እነጃዋርንና አቢይን ሲከፋቸው ውሎ ሲከፋቸው ይደር እንጂ ይህ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እየመረራቸውም ቢሆን ሊቀበሉት ይገባል፡፡ ከበቡሽም(ጃዋር) ናርሲሰስም(አቢይ) ትንሽ ይውረግረጉና አባታቸው ዲያቢሎስ ክንፉን ሲመታ እነሱም ተያይዘው ወደአባታቸው የጨለማው ግዛት ይወርዳሉ – ቤታቸው ታጥቦና ታጥኖ እየጠበቃቸው እንደሆነ ይህን መጣጥፍ ያነበባችሁ ወዳጆቻቸው ንገሯቸው፡፡ ለኢትዮጵያ ነፃነት ማንም ሳይታገል እጁን አጣጥፎ ቢቀመጥ ይህ አውነት አይቀለበስም፡፡ ለምን ቢባል – ቃል ነበር፤ ቃሉም ሥጋ ሆኖ በቅርብ በገሃድ የምናየው ይሆናል፡፡

አቢይ የቀረጠፋቸው ወገኖቼ፤

አቢይ ሥጋ በል ነው፡፡ ሥጋ ካልበላ እስትንፋሱ አትጸናም፡፡ እንደብዙዎቹ ፖለቲከኞች ፍጥረቱ ከአማራ ይሁን እንጂ የተጣባው ናርሲሳዊ እርኩስ መንፈስ ቀላል አይደለምና ኅሊናውን አስቶታል፡፡ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ እንደምንል አቢይም “ለሥልጣኔ ያልሆነ ሁሉ አፈር ደቼ ይብላ!” ብሎ ቆርጦ ተነስቷል፡፡ የአቢይ ዐቢይ ችግር የሥልጣንና የዝና ሱስ ነው፡፡ የብዙዎች አምባገነኖች ችግርም ይሄው ነው – አፈ ቅቤው አቢይ ግን የማኪያቬሊን “The Prince” ጨምሮ ብዙ በማንበቡ በምላሱ በርካታ ጅሎችን አነሁልሏል – እርሱም እንዳቅሚቲ ሌላ “The Prince” (እርካብና መንበር?) በመጻፍ “ተቀናቃኝህን በጥቅሙ ግባበትና ጨው እያላስክ ገደል ክተተው! ከዚያም ሥልጣንህን አደላድል፡፡” የሚል ማዕከላዊ ጭብጥ ያለው ሂትለር ወሙሶሌኒያዊ ፍልስፍና እየተገበረ ይገኛል፤ የአማራ ሆዳምና ጅላጅል ባለሥልጣኖች በአቢይ የእጅ አዙር ጥይት የተረፈረፉት ለዚህ ነው – ይሄ ራሱ እንኳን ሰውን አልገባውም – አዙሮብናላ! የነአዩ ጩፋና የነእስራኤል ዳንሣ ወንድም ሆኖ እንዴት አያዞርብንና አይዞርብን! የምዕራብ አፍሪካና የህንድ ጠንቋዮችና ሰይጣን ጎታቾች ምን ሠርተው ይብሉ? ሀገሪቱ እኮ በፊንታ ሠሪ የአፍዝ አደንግዝ ትብታባሞች የፊጥኝ ታስራለች – ከላይ እስከታች፤ በሃይማኖቱም በፖለቲካውም፡፡ ቄሱም ቃልቻውም፣ ጳጳሱም ኢማሙም …ለሥጋቸው አደሩና ምዕመኑ ካለእረኛ ቀርቶ ተኩላና ቀበሮ ይቦተርፈው ገባ፡፡ በዚህ የጨረባ ተዝካር ወቅት በሽተኛው ጤነኛ ነው፤ ጤነኛውም በሽተኛ፡፡ ኧሯ! ኧረ ግዴላቸሁም እንጸልይ! ለዘር የሚተርፍ ሰው እኮ እየጠፋ ነው፡፡ ነፃነትስ ቢገኝ ካለሰው ምን ፋይዳ ይኖረዋል?  

ሥጋ በሉ አቢይ ከመነሻው ኢንጂኔር ስመኘውን ቅርጥፍ አድርጎ በላ፡፡ እርሱን ለመደገፍ ሰኔ 16/2010 አደባባይ የወጡ የዋሃን ሰልፈኞችንም በርሱ ጦስ ቀርጥፎ በላ፤ ጥቂቶችንም አካለ ጎደሎ አደረገ፡፡ ቀጠለ፡፡ ባህር ዳርና አዲስ አበባ ላይ በተቀናጀ መልኩ እነሠዓረንና አሣምነውን ቀረጠፈ፡፡ ያም ግድያ የቫምፓየርነቱን ጫፍ የረገጠ ፍላጎት አላረካምና እነክርስቲያን ታደለን በማያውቁት ነገር ከያሉበት ሰብስቦ አሠረ፡፡ ከመግደል ባልተናነሰም እያሰቃያቸው ይገኛል፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርገውም ለስሙ በአማራነታቸው ይሁን እንጂ ዋና መነሻው ግን የአቢይ ናርሲሳዊ የእፉኝት ጠባይ ነው፡፡ በመሠረቱ አምባገነኖች ጨካኝ ከመሆናቸውም በላይ በሃሳብና በጥበብ የሚበልጣቸውን እያሳደዱ ማጥፋት ዋና ተግባራቸው ነው፡፡ መንግሥቱ ለምሣሌ አይደለም በሃሳብ፣ በመልክና በቁመት ሳይቀር የሚበልጠውን ወይም ይበልጠኛል ብሎ የሚያስበውን ሰው ደብዛውን ያጠፋው ነበር፡፡ አምባገነኖች እንደዚህ ናቸው፡፡ በጣም ቀሽም ናቸው፡፡ ከነሱ በላይ ማንም የለም፡፡ ሀገርና ሕዝብ በነሱ ዘንድ ቦታ የላቸውም፡፡ የሀገራችን ትልቁ የሥልጣን ወንበር ደግሞ እጅግ የተለዬ ነው፡፡ ሰዎች እዚያ ሲወጡ ጠባያቸው ዐውሬ ይሆናል፡፡ ሞትን ይረሳሉ፤እርጅናን ይረሳሉ፤ ህመምን ይረሳሉ፤ መውጣት እንዳለ ሁሉ መውረድን ይረሳሉ፤ በጥቅሉ ሰው መሆናቸውን ዘንግተው የአምላክነትን ባሕርይ ይላበሱና ተጃጅለው ያጃጅላሉ፡፡ ሲያሳዝኑ!

አቢይ በቅርቡ በከበቡሽ አማካይነት በተጫረ ሁከት ከ100 የሚበልጡ አማሮች ከያሉበት እንዲጨፈጨፉ አስደረገ፡፡ብዙ አብያተ ክርስቲያንና መስጊዶችም በጀሌዎቹ እንዲቃጠሉ አደረገ፡፡ እርሱ ወደ ውጭ በወጣ ቁጥር በምክክርና በስምምነት የሚፈጸም እስኪመስለን ድረስ የማይከሰት የሞትና የሀገር ውስጥ መፈናቀል የለም – ከዕድለ ቢስ የሀገር መሪዎች ውስጥ ቁጥር አንድ አቢይ ስለመሆኑ ማንም የሚከራከር አይመስለኝም፡፡ ሥጋ በሉ አቢይ የዓላማ አጋሩን ጃዋርን እንደልቡ እንዲፏልል ሲተወው ስለኢትዮጵያ የሚጨነቁና የሚጠበቡ በባዶ እጃቸው በድህነት የሚንቀሳቀሱ ወገኖችን ግን በውሾቹ ያሳድዳቸዋል – ዕንቆቅልሽ ምናውቅልሸ፡፡ በቄሮዎቹ አማካይነት እንደፈለገው ሕዝብን በተለይም አማራውን የሚያስጨፈጭፈው ጃዋር በቪ8 እየተንደላቀቀና በመንግሥት እየተጠበቀ – ባልተገራ ልፍዳዳ አንደበቱም ጎሣን ከጎሣ ለማጫረስ ከደናቁርት ቢጤዎቹ ጋር ያሻውን እየዘላበደ ሳለ የአማራ አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች ግን አፈናና እንግልት የየዕለት ዕጣ ፋንታቸው ነው፡፡ አማራውን አማራ ባልሆኑና ድምጻቸው በማይሰማ ደንገጡሮቹ አፍኖ መያዙም እንዳይዘነጋ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡

አቢይ ቢፈልግ በደቂቃዎች ውስጥ መፍትሔ ሊገኝ የሚችለው የወለጋው የአማራ ተማሪዎች እገታ እስካሁን ዕንቆቅልሽ እንደሆነ አለ – የዜጎችን ሕይወት አሲይዞ ቁማር መጫወት የገብጋባና የኅሊናቢስ ፖለቲከኞች ጠባይ ነው፡፡ እነዚያ ተማሪዎች እርግጠኛ ነኝ የበዛብህ ጴጥሮስን ዕድል እንዳልተጋሩ ማንም እርግጠኛ ሊሆን አይችልም፡፡ ተማሪዎቹ በሕይወት ለመኖራቸው ምንም ዋስትና የለም፡፡ በነዚህ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ግፍ ሁሉ ከ45 ሚሊዮን በሚልቀው የአማራ ሕዝብ እንደደረሰ ይቆጠራልና እነዚህ ግፈኞች ነገ ወዮላቸው!!

ሁኔታዎች ሁሉ እያመሩ ያሉት ወደሚጠበቀው አርማጌዴዎን ነው፡፡ አማራን ነካክተው ነካክተው ከተኛበት ካስነሱት የ21 ተማሪዎች አይደለም እስካሁን የተፈጸሙት የወያኔና የአክራሪ ኦሮሞዎች የግፍ ድርጊቶች ሁሉ አጸፋቸውን ያገኛሉ፡፡ ግፍ በዝቷልና ጽዋውም ሞልቷልና ብድራትን ለመቀበል ሁሉም መዘጋጀት አለበት፡፡

ሥጋ በሉ አቢይ አህመድም አማራውን የሚወጋበት ብአዴን ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደሚከሽፍበት መረዳት ይኖርበታል፡፡ አለበል መላኩን ወደ አዲስ አበባ ያመጣበት ምክንያት ለኔ ግልጽ ነው፤ ሃታኡ መሌ አልናገርም፡፡ አሁን ካለው ብአዴን ማንም ምንም ስለማይጠብቅ አለበል መጣ ዮሐንስ ቀረ ምንም ማለት አይደለም፡፡ በሠርጎ ገብ ወያኔና ኦነግ የተሞላው ብአዴን ዱሮውንም ለአማራና ለኢትዮጵያ ነፃነት አንዳችም ፋይዳ እንደሌለው የታወቀ ነው – የአህያ ባል ቤተሰቡንም ሆነ ራሱን ከጅብ አስጥሎ አያውቅም፡፡ ከቤት ውልድ መልካም ነገር እንደማይገኝ “አማራ ልጋጋም ነው” ካለው አለምነው መኮንን ተገንዝበናል፡፡ ልጋጋሙ ማን እንደሆነ ደግሞ ጊዜ ባለውሉ በቅርብ፣ እጅግ በጣም በቅርብ ያሳየናል፡፡ መፍትሔው ከሌላ አቅጣጫ ነው፤ ይህንንም አልናገርም፡፡

ይልቁናስ ዛሬ አንድ የዳዋሮ የሀገር ሽማግሌ፣ ሥጋ በሉ አቢይ ፊት ደቡብ ውስጥ የተናገረው ነገር አንጀቴን አራሰው፡፡ ይህ ነው ኢትዮጵያ እንዳልሞተችና መቼም ቢሆን እንደማትሞት በግልጽ የሚያስረዳን እውነት፡፡ ያ ሰው ከአማሮችም በበለጠ አማርኛን ከነቅኔውና ከነዘይቤው አቀላጥፎ እየተናገረ ሥጋ በሉን ሰውዬ አስደመመው፡፡ ለዚህ ነው ለሽዎች ዓመታት የተሠራን የኢትዮጵያዊነት ድርና ማግ በ30 እና በ40 ዓመታት የድውያን ዕኩይ ተግባር መበጣጠስ እንደማይቻል ስንመሰክር የባጀነው፡፡ ይሁን ግዴለም፡፡ ተማሪዎችም ይሙቱብን፤ ወልቃይቶችም እየተገደሉ በሸለቆዎች ይጣሉብን፤ ሌሎች አማሮችም ይጨፍጨፉ፤ ሞት እንደሁ መቼም አይቀርም፡፡ አይዞን ግዴለም፡፡ ራያም ይወሰድ፤ የጎንደርና የጎጃም መሬትም ለሱዳን ይሸጥ፡፡ ግዴለም -ሚሊዮኖች አማሮች ከየመኖሪያቸው፣ ከየኃላፊነታቸው፣ ከየሥራ ቦታቸው፣ ከየቀያቸው … ይፈናቀሉ፤ ይገደሉም፡፡ የነሱ መስዋዕትነት ግን የአቤል ደም ሆኖ እኛንና መጪውን ትውልድ ከገባንበት የሥጋ በሎች ሦስተኛው አብዮት ነጻ ያወጣናል፡፡ በዚህን ዘመን ባልመለስ ደስ ባለኝ፤ ግን መች ያስችለኝና! ብቻ ጠልዩልኝማ፡፡

ለማንኛውም እንግሊዝኛ የምትሞካክሩ ከድረገጽ ጨልፌ ቀጥሎ ያስቀመጥኩትን የአቢይን ማነው የናርሲሰስን ታሪክ በንባብ ውጡት፡፡ 

 

Narcissism is the pursuit of gratification from vanity or egotistic admiration of one’s idealized self image and attributes. This includes self-flattery, perfectionism, and arrogance. The term originated from Greek mythology, where the young Narcissus fell in love with his own image reflected in a pool of water.

 

Narcissistic personality disorder

Narcissistic personality disorder — one of several types of personality disorders — is a mental condition in which people have an inflated sense of their own importance, a deep need for excessive attention and admiration, troubled relationships, and a lack of empathy for others. But behind this mask of extreme confidence lies a fragile self-esteem that’s vulnerable to the slightest criticism.[ለአቢይ ተለክቶ የተሰፋ ገለጻ!]

A narcissistic personality disorder causes problems in many areas of life, such as relationships, work, school or financial affairs. People with narcissistic personality disorder may be generally unhappy and disappointed when they’re not given the special favors or admiration they believe they deserve. They may find their relationships unfulfilling, and others may not enjoy being around them.

Treatment for narcissistic personality disorder centers on talk therapy (psychotherapy).

Symptoms

Signs and symptoms of narcissistic personality disorder and the severity of symptoms vary. People with the disorder can:

  • Have an exaggerated sense of self-importance
  • Have a sense of entitlement and require constant, excessive admiration
  • Expect to be recognized as superior even without achievements that warrant it
  • Exaggerate achievements and talents
  • Be preoccupied with fantasies about success, power, brilliance, beauty or the perfect mate
  • Believe they are superior and can only associate with equally special people
  • Monopolize conversations and belittle or look down on people they perceive as inferior
  • Expect special favors and unquestioning compliance with their expectations
  • Take advantage of others to get what they want
  • Have an inability or unwillingness to recognize the needs and feelings of others
  • Be envious of others and believe others envy them
  • Behave in an arrogant or haughty manner, coming across as conceited, boastful and pretentious
  • Insist on having the best of everything — for instance, the best car or office

At the same time, people with narcissistic personality disorder have trouble handling anything they perceive as criticism, and they can:

  • Become impatient or angry when they don’t receive special treatment
  • Have significant interpersonal problems and easily feel slighted
  • React with rage or contempt and try to belittle the other person to make themselves appear superior
  • Have difficulty regulating emotions and behavior
  • Experience major problems dealing with stress and adapting to change
  • Feel depressed and moody because they fall short of perfection
  • Have secret feelings of insecurity, shame, vulnerability and humiliation

When to see a doctor

People with narcissistic personality disorder may not want to think that anything could be wrong, so they may be unlikely to seek treatment. If they do seek treatment, it’s more likely to be for symptoms of depression, drug or alcohol use, or another mental health problem. But perceived insults to self-esteem may make it difficult to accept and follow through with treatment.

If you recognize aspects of your personality that are common to narcissistic personality disorder or you’re feeling overwhelmed by sadness, consider reaching out to a trusted doctor or mental health provider. Getting the right treatment can help make your life more rewarding and enjoyable.

Signs and symptoms of narcissistic personality disorder

  • Grandiose sense of self-importance. … 
  • Lives in a fantasy world that supports their delusions of grandeur. … 
  • Needs constant praise and admiration. … 
  • Sense of entitlement. … 
  • Exploits others without guilt or shame. … 
  • Frequently demeans, intimidates, bullies, or belittles others.

እንዴት አገኘኸው? ከአቢይ ጠባይ ጋር አንድ አልሆነብህም? ይገርማል!

 

EMAIL: ma74085@gmail.com

Filed in: Amharic