>
4:05 am - Friday July 1, 2022

እሜቴ አብዮት ውድ ልጆቿን ምን ልታደርግ ይሆን ? (ዘመድኩን በቀለ) 

እሜቴ አብዮት ውድ ልጆቿን ምን ልታደርግ ይሆን ??

ዘመድኩን በቀለ 
[ በዚህ ሁሉ ግርግር መሃል ግን የእንግሊዙ የስለላ ድርጅት ቅጥረኛ እንደሆነ የሚነገርለት አቶ ደመቀ መኮንን ሀገር ተተራምሶ ሌላ መንግሥት ቢመጣም ምክትልነቱን አይንካበት እንጂ ዴንታው አይደለም … ]  
 
••• 
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከሀገር ወጥቷል። ኤርትራም ገብቷል!
••• 
የሐገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ሀገር ውስጥ የሉም!!
•••
የኦነጉ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳም ወደ  ጀርመን አቅንቷል
—–
የሀገሪቱ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳም ከሀገር ወጥቷል። ለማ ከዐቢይ ተኳርፏል ይባላል። በወለጋ ልጆቹን ያሳገተው የለማ ቡድን እንደሆነ በሰፊው እየተነገረ ነው። አጋቹ ቡድን ቀደም ሲል በዘመነ ህወሓት ለተለየ የሽብር ስልት በዐቢይና በለማ በህቡዕ እንደተቋቋመ የሚነገርለት አባ ቶርቤ የሚሉት የቄሮ ክንፍ እንደሆነ ሲነገር አሁን ይሄ ቡድን ዐቢይን ዲቃላ በማላት ፊቱን ከለማ ጋር አዙሮ መተኛቱ ነው የሚነገረው። ወለጋ የለማ የትውልድ ሀገር ነው። አሁን በወለጋ የስልክ አገልግሎት ባለመኖሩ ኦቦ ለማ ለቤተሰቦቻቸው እንኳ መደወል አይችሉም። የእነ ጃወር መረራ በቀለ ገርባ ቡድንም የለማን ፖስተር አሰርቶ በአደባባይ መታየት መጀመሩ የሆነ ነገርማ አለ የሚሉ እንዲበዙ አድርጓል።
•••
በሌላ ዜና ደግሞ የወለጋው ነፃ አውጪ የኦነግ ሸኔው መሪ የጃል መሮ ሚስት እንደሆነች የሚነግርላት ጫልቱ ታከለ ከ 8 ወር ልጇ ጋር ተይዛ ወደ ወኅኒ ወርዳለች ተብሏል። ወለጋ ጭፍጨፋ ላይ ነው የሚሉም አሉ። ኔትወርክ ሲለቀቅ የሚታየው ጉድ ዘግናኝ ይሆናልም እየተባለ ነው።
•••
የኦነጉ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳም ወደ ራየን ወንዝ ማዶ እኔ ወዳለሁበት ሀገረ ጀርመን መጥቷል። አምልጥ ነው መሰለኝ ነገሩ። የጃል መሮ ሚስት የጫልቱን መያዝ እንደሰማ ነው ሼባው ወደ ጀርመን የነካው ነው የሚሉኝ የሰላሌ ልጆች። አብዮት ልጆቿን መብላት ሳትጀምር አልቀረችም።
•••
አባ ሜንጫ ጃዋር መሐመድም የፌስቡክ ገጹን በማጽዳት ሥራ ተጠምዷል። የሚያጸዳው ከእኛ ዕይታ ነው እንጂ ከዋናው ከፌስቡክ ተቋም ከቋቱ ግን ማጥፋት አይቻለውም።
•••
በዐማራ ክልል የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎችን መብት ለማስጠበቅ “ የተለየ የትግል ስልት”  መከተል አለብን በማለት መርዙን ሲረጭ የከረመው የኦፌኮው ጃዋር መሐመድ ያ “ የተለየ የትግል ስልት” ብሎ የሰየመው የትግል ስልት በደንቢዶሎ የዐማራ ተማሪዎችን በማገት ከተጠናቀቀ በኋላ እንደ አውሮጳውያኑ የዘመን አቆጣጠር ከሰብቴምበር 29/2019 ዓም እስከ ኖቬምበር 30/2012 ዓም ድረስ ለአንድ ወር ሙሉ የፖሰታቸውን መርዛማ መልዕክቶች ሙሉ በሙሉ አጽድቷቸዋል።
•••
የታገቱት ልጆች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ባለማዕተብ ክርስቲያን የተዋሕዶ ልጆች ናቸው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ልጆች ናቸው። አብዛኛዎቹ ደግሞ ከ4 ወንዶች በቀር በአብዛኛው ህጻናትና ሴቶች ናቸው። በነገድም የዚያ የፈረደበት የዐማራው ነገድ አባላትም ናቸው። የጃዋርና የአህመዲን ጀበል ሜንጫ፣ የለማ መገርሳና የዐቢይ አህመድ እርግጫ እነዚያን እምቦቀቅላዎች ከምን አድርሷቸው ይሆን?
•••
ሻሎም !    ሰላም !
ጥር 18/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic