>

ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው? ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ..(ገብረመድህን አርአያ - አውስትራሊያ ፐርዝ)

ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው?

ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ገብረመድህን አርአያ – /አውስትራሊያ ፐርዝ/ 
ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከኤርትራ መጥቶ ህወሓት መቀላቀሉ በአብዛኛው የወይኔ በተለይ ነባሩ ታጋይ የሚታውቀ ሃቅ ነው፤ እሱም ራሱ የሚናገረው ሃቅም ጭምር ነው። ደብረፅዮን ወደ ህወሓት የተቀላቀለው በመጨረሻው 1974 ዓም አካባቢ ነው። በወታደራዊ ማሰልጠኛ የክፍሉ ዋና መሪዎች በተለይ ሶስቱ መሪዎች የነበሩ ስማቸው አልጠቅስም ይህን አረጋግጠዉታል። ተወልዶ ያደገው ትምህርቱም የተማረው ኤርትራ ውስጥ ነው። ትግራይ ትውልድ ቦታዬ ነው ቢልም ይህም አሻሚ ነገር አይሆንም!!
የነገሩ ፍሬ ግን ኤርትራ አድጎ የጀብሃ ታጋይ የነበረው ትግራይና ህዝብዋን መምራት ይችላል ወይ? ነው፤የትግራይ ህዝብ ማንነት ፍፁም የማያውቅ ሰው!! ይህም የትግራይ ህዝብ ጥያቄ መሆን ያለበት ነው፤ ቀደም ሲልም በኤርትራውያን መሪዎች ትግራይ ስትመራ ቆይታለች፤
    ሃለቃ ፀጋይ በርሄ
    አባይ ወልዱ
    ክፉ አረመኔው የሃገርና የህዝብና ጠላት በሆነው “ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል አሁንም ትግራይ እየተገዛች ነው።
ትግራይ በራስዋ ልጆች ለምን አትመራም? የሚል ጥያቄ ከህዝቡ ቢነሳም በሕወሃት መሪዎች መልስ አያገኝም፤ ሾላ በድፍን። ከመቀሌ፣ ውቅሮ “ሁለት ዓውላዕሎ”፣ አጋሜ፣ ተምቤን፤ ዓድዋ፤ አክሱም፤ ሽሬ እንዳስላሴ፤ ማይጨው፤ የክልሉ ተውላጅ የመምራት ብቃት ያላቸው የሉምን? የሚል ጥያቄም ቢነሳም የሉም ሳይሆን የህወሓት ፖሊሲ በመሆኑ ብቻ ነው። ፖሊሲው ትነህግ (ህወሓት) የትግሉን የጀመረበት ዋናው የትግሉ መነሻው ትግራይን ከጨቋኙ የአማራው መንግሥት (ኢትዮጵያ) ተገንጥላ ታላቋን የትግራይ ሪፑብሊክ መንግሥት ስለምትመሰረት ድሮም ነፃ ሃገር የነበረችው ትግራይ፤ ወደ ውጭ ሃገር መውጫ በር፤ሰፊ የእርሻ መሬት ስለሚያስፈልጉ ከወሎ ከአለውሃ ምላሽ ራያ ድረስ፤ ከጎንደር ወልቃይት ጠለምት ጠገዴ ሁመር እስከ አርማጮህ መተማ ድረስ ጠቅልሎ የመውረር፤ ወራሪው ድርጅት ህወሓት ወደ ትግሉ ደደቢት በረሃ የወጣው ይህን ሁሉ በሚከተለው የትግሉ ፖሊሲ አዘጋጅቶ ነው ደደቢት የገባው።
በዚህ ወቅትም በብዛት የተቀላቀሉት ትውልደ ኤርትራውያን ናቸው። በአረጋዊ በርሄ የሚመራው ወያኔ ህወሓት እነዚህ ኤርትራውያን ለከፍተኛ የስልጣን ኮረቻ ካደረሳቸው እንዲያውም ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን የበቁ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው። ትግራይ በነዚህ ጠላቶች እጅ የወደቀችም መነሻው ከዚህ ነው። ትግራይ ክ/ሃገር ብቻ ሳይሆን በሃገር ደረጃ ኢትዮጵያም አሁን እየደረሳት ያለው ምስቅልቅልና ለክፉ የመበታተን አደጋ ሌሎች ችግር የዳረጋት ከዚሁ ተያይዞ የመጣም ነው።
እነ መለስ ዜዊም ኢትዮጵያን ለ27 ዓመት ገዝተዋል፣ መርተዋል። በወያኔ የመጡ ኤርትራውያን የባንዳ ልጆች ከመሆናቸው የተነሳ ኢትዮጵያን በመጥፎ ስሜትና ጥላቻን ኢትዮጵያን ያወግዛሉ አምርረው ይጠላሉ። ህወሓቶች በትግራይ ብቻ አይደለም ይህን የአገዛዝ ስርአት ያሰማሩት አማራም በስመ ብአዴን አማራ በራሱ ልጆች ሳይሆን በኤርትራውያንና በትግራይ መሪዎች በነ በረከት ስሞኦን፣ ታደሰ ካሳ፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ካሳ ተ/ብርሃን ወዘተ እየተመራ ለብዙ ችግርና ሞት፤ ስደት ተዳርጓል። በእጅ አዙር ባንዳዎች በትግራይ በኤርትራውያን የአማራ ገዝተውታል። ይህም የወያኔ ፖሊሲ ነው የአማራውን ኅልውናው ለማጥፋት በህወሓት መሪዎች ከትግሉ መነሻ ጀምሮ የወጣና የታቀደ ፖሊሲም ነው። የአማራው ኢትዮጵያዊ ባካሄደው ፀረ ህወሓት መራር ትግልና ከባድ መስዋእትነት ከ40 ዓመታት በላይ ከፍሎ፤ ባሁኑ ጊዜ ነፃ ነው፤ ባንዳ የባንዳ ልጅ ጠራርጎ በማባረርና በማሰር ነፃ ሆኖ በራሱ ልጆች እየተመራ ነው፤ ይህም ትልቅ እርምጃ ነው። በትግራይ ይህ የለም፤ ትግራይ በኤርትራውያን አገዛዝ አሁንም እንደወደቀች ናት።ለዚህም ተጠያቂውም ህወሓት ነው።
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በአስመራ ዩኒቨርሲት የኢጂነሪንግ ተማሪ ነበረ፤ ትምህርቱን አቋርጦ ተ.ሓ.ኤ. (ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ) ጀብሃ ተቀላቀለ። በዚህ ድርጅት ሰልጥኖ በአስመራ ውስጥ የጀብሃ ስዉር ፈዳያን (ፈዳያን የአረብኛ ቃል ነው ትርጉሙ ሽብርተኛ፤ ገዳይ፤ ነብስ አጥፊ ማለት ሲሆን በእንግሊዝኛው TERRORIST ማለት ነው) ሆኖ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሂወት የቀጠፈና ያጠፋ ሰው ነው። ይህም ከፍተኛ የህወሓት አመራር ስብሃት ነጋ፤ አባይ ፀሃይ መለስ ዜናዊ ወዘተ በማያሻማ ሁኔታ ያውቃሉ፤ ሌላ የደብረፅዮን ማንነት የሚያውቁ ብዙ ናቸው። የዛሬው “ሞኦ ወያኔ አይተ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ንጉሠ ዘትግራይ» ትግራይ እየገዛ ያለው ጀብሃ ታጋይ ነበር።
ጀብሃም ሆነ ደብረፅዮን በጀመሩት የትግል መንገድ ብዙ አልሄዱበትም፤ ሻዕብያና ጀብሃ ከመነሻው የትግል ጉዛቸው የከረረ ጠብ ስለ ነበራቸው ጀብሃ በሻዕብያ ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳና ጥቃት ያደርስበት ስለነበረ ለሻዕብያ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር። ሻዕብያም በዚሁ ችግር ትግሉን ለማካሄድ የማይችል መሆኑን ስለተገነዘብ ችግሩን ወደ የሚያልቅበት ወሳኝ የሆነ የስትራቴጂ መፍትሄ ሃሳብ ገባ። ስትራተጂካዊ ወታደራዊ ዝግጅቱም ነደፈ አጠናቀቀ። ከሕዳር ወር 1972ዓም አንስቶ ሻዕብያ ሙሉ ወታደራዊ ዝግጅቱን አጠናክሮ ሠራዊቱን በማሰለፍ በጀብሃ ላይ በማያዳግም የጥቃት ዘመቻው ከፈተ። ጀብሃ ተፈረካከሰ፤ በየቦታው በየውግያው ሽንፈቱን ፅዋዉን ተከናነበ። የጀብሃ ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ ተበታተነ፤ ወሳኝ ፍልምያ ጦርነቱ ታህሳስ ወር 1972 ዓ.ም. በሁለት ወር ውስጥ ተገባደደ፤ ጀብሃ ከኤርትራ ምድር ድምጥማጡ ጠፍቶ የትግሉ ሂወት አበቃ፤ ጀብሃ ሞተ። ብዙ የጀብሃ ታጋዮች ተማረኩ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምርኮኞቹ ወደ ምትፈልጉት ሃገር ሂዱ በማለት ሻዕብያ በነፃ አሰናበታቸው፤ የደብረፅዮን ገብረሚካኤል ሓቀኛ ታሪኩ ከዚሁ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ኤርትራ ገብቶ ለመኖር ስለማችል መጠግያ ፍለጋ ወደ ህወሓት ሸራሮ መጣ። እንዴት እንደተቀላቀለ ሚስጥሩን የሚያውቅ ተክሉ ሓዋዝ ብቻ ነው፤ እሱም ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየ ሚስጢሩ ማወቅ አይቻልም፤ ለሌላ አስቸጋሪ ቢሆንም እነ ስብሓት ነጋ ግን የደብረፅዮን ማንነት ያውቃሉ፤ ካለ እነዚህ የትግራይ መሳፍንቶች እውቅና ውጭ የሚድረግ የለም።
ተክሉ ሓዋዝ ወደ 02 ወታደራዊ ማሰልጠኛ ልኮት የአንድ ወር ስልጠና ወስዶ እንደጨረሰ በእንስሣት የጭነት ማጓጎዣ መደቡት። ቦታው ግን የሚመጥነው አልነበረም። የ02 አመራሮች አንስተዉት እንደነበርም ይናገሩ ነበር፤ ሚስጢሩ ግን ስብሓት ነጋ ከህወሓት ታጋይ በተለይ በክፍሎች ተመድበው ከሚሰሩ ታጋዮች ጥሩ ግንኙነት ፈጥሮ ትውውቁ እንዲያጠናክር ሆን ብሎ ያደረገው ሲሆን ከማጓጓዣው አውጥተዉም በብዙ የተለያዩ ክፍሎች እየተመደበ መስራቱ ይታወሳል። ደብረፅዮን የካድሬ ትምህርት የተማረው መለስተኛ ካድሬ ነው። ከዚህም አልዘለለም፤ ቢሆንም ግን የተማረ ሰው ነው፤ በጊዜው በህወሓት አመራር ታማኝነቱን አላረጋገጠም ነበር ማለቱ በቂ ነው። በመጨረሻ በ1979 ዓ.ም. ግንቦት ወር ደጀና ላይ የህወሓት ማሌሊት ኮንፈረንስ የ5ቀን የካድሬዎች ኮንፈረንስ ስብሰባ በሙሉ መሳተፉን አውቃለሁ። አብረን ነበርን ትውውቃችን ቀደም ያለ የነበር ቢሆንም፤ በዚሁ በስብሰባ መሳተፍ ግን ለደብረፅዮን የመጀመሪያው ጊዜ ናት። ጌታቸው አሰፋም ነበር፤ ለሱም የመጀመሪያው ስብሰባ ናት። እነዚህ ሁለቱ በዚሁ ኮንፈረንስ መሳተፍ ማለት በስብሓት ነጋና በመለስ ዜናዊ ሙሉ እውቅና ማግኘታቸው ያረጋገጠም በቂ ማስረጃ ነው። በተረፈ ደብረፅዮን በዝቅተኛ ሥራ ተመድቦ መኖሩ ሁሉ ታጋዩ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፤ ደብረፅዮን እጅግ በጣም ተንኮለኛ መርዘኛ እባብ ነው፤ ደብረፅዮን ቁጡና ገልፍተኛ ባህሪ አለው፤ ተሳዳቢም ነው፤ ቂመኛ ሰውን የማጥቃት ቂሙና በቀሉን ለመበቀል ፍላጎትና ምኞቱ እቅዱን በድብቅ የሚያከናውን፤ በማር የተለወሰው መርዙ በአስመሳይ ባህሪው የማወናበድ ዘዴው የተካነ ነው።
ለምሳሌ አሁን እየተጠቀመበት ያለውን ማየት በቂ ነው፤ ለአብነት ያህል፤ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ፍላጎቱ አለው በግልፅ እየተናገረ ነው፤ ብሎ በሬድዮና በቴሌቭዥን ደብረፅዮን የተናገረውን እናስታውስ፤ ትግራዋይ በመሆናቸው ብቻ እየተለዩ እየታሰሩ ናቸው፤ ትግራዋይ በመሆናቸው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ቦታዎች እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፤ ሃብት ንብረታቸው ወድመዋል፤ ብዙ ትግሬዎችም ተገድለዋል ወዘተ በማለት አደገኛ የውሸት ፈጠራው ወደ ትግራይ ህዝብ በማሰራጨት ንፁሁን ህዝብ የሚያስጨንቅ፤ ከወንድሙ በሰላም በፍቅር ከኖረበት ኢትዮጵያ ሃገሩ እየለየ አንተን ሊያጠፉህ ኤርትራና አማራው ተንኮል እያሴሩብህ ነው፤ እያለ የትግራይን ህዝብ እያስጨነቀ የሚገዛው ያለው በዚሁ ዘዴው በኢትዮጵያ ህዝብ ግጭት ለመፍጠርም ነው ይህም የወያኔ መርዎች እቅድም ነው። የትግራይ በሰላም እንዳይኖር ከኢትዮጵያዊ ወገኑ ለማለያይት ያልቻለው የትግራይ ህዝብ ህወሓት ከተፈጠረባት እለት አንስቶ በባርነት በመያዣ የታሰረ ህዝብ ከኤርትራ የመጡ የባንዳ ልጆች በስመ ታጋይ ህወሓት የሚገዛና የሚመራ፤ ለችግርና መከራ የተዳረገ ኢትዮጵያዊ ህዝብ የትግራይ ህዝብ ነው። የሚመራው የትግራይ ሰው የለም ማለት ነው? ወይስ መሪ የመሆን ብቃትና ችሎታ በትግራይ ተፈልጎ ስለታጣ ነው? ይህን የሚመልሱት ሻንጣ ተሸካሚው የህወሓት ማእከላይ/ኮሚቴውና የህወሓት ፍርፋሪ ለቃሚ ካድሬዎች፤አባላቶቹና ደጋፊዎቹ ብቻ ናቸው። የትግራይ ህዝብ ለሰቆቃና መከራ የዳረጉትም እነዚህ አጋሥስ ማ/ኮሚቴና ካድሬዎቹ ከተጠያቂነትም አያመልጡም።
የትግራይ ነፃ ህዝብ ከኤርትራ በመጡ የማፍያ ስብስብ ወንጀለኞች ተከቦ የተያዘ ነው። አሁንም ለወደፊትም የትግራይ ህዝብም እንዲህ ሆኖ መኖርም ስለማይቻል ካሳለፍከው የ45 ዓመታት ስቃይና የሰቆቃ የወያኔ የባርነት አገዛዝ በስምህ እየነገዱ ባንተ ስም እየዘረፉ ኢትዮጵያን ያፈረሱ የስንቱን ኢትዮጵያዊ ህዝብ ሂወት የገደሉ ያጠፉ የህወሓት/ወያኔ የወረበላ ወንጀለኞች ስብስብ ዛሬ ይብቃኝ ብልህ መነሳትና እነዚህ ማፍያዎች ማስወገድ በኢትዮጵያዊነት ሃላፊነትም የታሪክ ግዴታ አለብህ።
በአሁኑ ጊዜ ትግራይ ኢትዮጵያን ያደሙ ኢትዮጵያ በዝርፍያና በሙስና ሌብነት አጥንት ብቻ ያቀርዋት ህዝብዋን ጭምር የገደሉ ያጠፉ፣ በህዝባዊ ሃይል ከስልጣናቸው የተወገዱ የወያኔ ማፍያ ስብስብ ምሽግ ሆናለች፤ አሳዛኝ ነው። ይህች የጀግኖች የአርበኞች የኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር ሰፈር ምን ጉድ ወረደባት።
ደብረፅዮን በቀን 7 ጊዜ ይዋሻል፤ አስመሳይ ውሸታም ነው፤ ይህም የሚጠቀምበት ዘዴውም ህዝብ ለህዝብ ለማጋጨት ነው። በመቀሌ በህዝብ ፊት የዋሸው ሽሬ ሂዶ በህዝብ ፊት ቁሞ ይክዳል፤ 7 ጊዜ ይዋሻል 7 ጊዜም ይክዳል፤ ከሃዲ ውሸታም ባህሪ የተጠናወተው፤ በተለይ ህዝብ ለህዝብ የማጋጨት ድብቅ የተንኮሉ ሤራው ነው። ደብረፅዮን በህዝብ ላይ ይሳለቃል፤ ህዝብን ይሳደባል በትግሉ ጊዜ ከገበሬዎች ለስራ አህዮች ለመሰብሰብ ወደ ገበሬዎቹ ሲሄድ ስዎቹን እየተሳደበ እየመታ በጉልበቱ የፈለገውን ይዞ ይሄዳል፤ ገበሬዎቹም ያማረሩበት ጊዜ ነበር። ለሰው ልጅ ክብር አይሰጥም ከባለጌነቱ የተነሳ ለምሳሌ ባለፉት ጥቂት ቀናት በድምፅ ወይኔ የተናገረው አሳፋሪ ንግግር ለሰባዓ እንደርታ ለዓጋሜ ህዝብ፤ ለተምቤን ህዝብ በአንድ ደምሮ ባንዳና ባንዳዎች ናችሁ፤ ብሎ ህዝቡን መሳደቡን እናስታውሳለን። በትግርኛ አንድ ተረት አለ “ዘመን ያ ግርምቢጥስ ማይ ንዓቅብ” ይህም “ዘመን ሲገላበጥ ውሃ ወድ ሽቅብ ይፈሳል” ማለት ነው።
የትግራይ ህዝብ ባንዳ አይደለም ፤ በኢትዮጵያዊነቱ በጀግንነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ያስመሰከር ጀግና ህዝብ ነው። ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነፃነት አንድነት ሲል ከጠላት ባእድን ወራሪዎች ለእናት ሃገሩ ኢትዮጵያ የሞተና አጥንቱ የከሰከሰ በኢትዮጵያ ታሪክ ያስመሰከረ ኩሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ነው።የወያኔ መሪዎች የትግራይ ህዝብ ታሪክ አያውቁምና። ባንዳ ማለት እሱ ራሱና የወያኔ መሪዎች መቀሌ ውስጥ በምሽግ ተደብቀው ያሉት በራሱና በስብሓት ነጋ የሚመሩ ናቸው። ዘር ከዘራቸው ባንዳዎች እንጂ የትግራይ ህዝብ በዚሁ አይታማም። ትግራይ ዛሬ በባንዳዎች እጅ ወድቃለች፤ በአፈ ሹም ባንዳ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የምትመራ ከኢትዮጵያ አፈንግጣ ከኢትዮጵያ ግዛት ውጭ ሁናለች ለማለት እንችላለን፤ ረእሰ መሪዋ የኢትዮጵያ ትእዛዝና መሪነት አይቀበልም። ትግራይ የሌቦች፤ የወንጀለኞች፤ ሃገር ያፈረሱ ህዝብ የገደሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ንብረት የዘረፉ ሌቦች መኖሪያ ምሽግ ሆናለች። በመሳፍንቱ የወያኔ መሪዎች እጅ ወድቃለች።
በባድመ በተነሳው ግጭት ኤርትራና ኢትዮጵያ መሃከል የስንቱን ሂወት የቀጠፈው ስንት ሃብት ንብረት የወደመበት አስከፊ አሳዛኝ ጦርነት ወቅት በሁለቱ በደም በሥጋ በታሪካቸው የተሳሰሩ ህዝብ ይህን መከሰቱ ታሪክ ይቅር የማይለው የማይረሳው ነው። የህወሓት ወያኔው መንግሥት በኢትዮጵያ ህዝብ የ27 አመት የጨለማ የሲኦልና ሶቆቃ ዘረኛ አገዛዙ በህዝባዊ ትግል ብርታትና መስዋእትነት ወያኔ ከሥልጣኑ ተወግዶ ሲጣል፤ በወቅቱ የመጡ ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ ተቀባይነትና ድጋፍ በማግኘት በኢትዮጵያ ሙሉ ባለሥልጣን ሆኖውም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኖው ተሾሙ። ወያኔ እንደ ለመደው ሲሸነፍ መሸሽ ልማዱ ነውና ወደ መቀሌ ጓዙን ሸክፎ የፈረጠጠው እዚያውም ወደ ምሽጉ ገብቶ ተቸንክሮ ቀረ። አረመኒያዊ ስርአቱም አብሮት በምሽግ ጉድጓዱ ተቸነከረ። በዚህ ጊዜ ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስተር ሆነው እንደተሾሙ የወያኔው የ27 ከፉ የጨለማ ዘመን አገዛዝ አከተመ። ዶ/ር አብይ አህመድ ሥልጣኑ እንደተረከቡም የመጀመሪያ የሰላም እጃቸው የዘረጉት ወደ ኤርትራ ነው። እቅዳቸውም ወደ መተግበር ገቡ፤ ብዙ ችግር የነበረበት ባድመ በተፈጠረው ግጭት በሁለቱ ወንድማዊ ህዝብ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ሊከሰት የማገባው ደም አፋሳሽ የተካሄደው ጦርነት የስንቱን ሂወት የቀጠፈ ስንት ሃብትና ንብረት ያወደመ ለ20 ዓመታት ሙሉ በህዝቡ መሃከል ስጋትና ፍርሃት የነገሰበት አስቸጋሪ ውጥረት ለማጥፋት የኢትዮጵያው መሪ ዶ/ር አብይ ከኤርትራ መሪ ፕሬዚዳንት ኢሳያሳ አፈወርቅ የሰላም የፍቅር የወንድሟሞች ውይይት ተካሂዶ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ተጨምሮበት በሁለቱ ሃገራትና በህዝብ ዘላቂ ሠላም ወረደ። ኤርትራም የኢትዮጵያዊያን ቤት ማረፊያ ሆነች ኢትዮጵያም የኤርትራውያን ማረፊያ ቤት ሆነች ሁለቱ ወንድማዊ ህዝብ በሰላምና በፍቅር ተቃቅፈው ዛሬ ይገኛሉ።
ስብሓት ነጋ
ለወያኔ ግን ይህ የሰላም የፍቅር መንገድ አልተዋጠለትም። የኤርትራ ህዝብ የኢትዮጵያ በተለይ ኩታ ገጠም ድንበር ያላቸው አማራና ትግራይ በእልልታና ደስታ ሲያከብሩት፤ መቀሌ የመሸገው የወያኔ ፀረ ህዝብ ቡድን አእምሯቸው የዛለ በድን መሳፍንት እነ ስብሓት ነጋ የእነዚህም አፈ ሹም ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለተፈጠረውና ለመጣው እርቀ ሰላም አደባባይ ወጥተው አወገዙት፤ በሁለት አምባገነን መሪዎች የሚፈጠር ስላም አይገኝም አሉት። ከነዚሁ ያልተለየ ውግዘት የሰነዘረው የTAND (ታንድ) ም/ሊቀ መንበር ግደይ ዘርአፅዮን በLTV ቴሌቭዥ ጣብያ የተገኘው ሰላም አውግዞ በሁለት አምባገነን መሪዎች ሰላምና ስምምነት አይፈጠርም፤ ሰላም አይገኝም በማለት አወገዘው። ኮተታሙ ግደይ ዘራፅዮን ውግዘት ለወያኔ መሳፍንቱ ለነ ስብሓት ነጋ አስደስቶ ፍርፋሪውን ለመልቀም ያቋመጠ ነው። ቂመኛው ደብረፅዮን ግን የራሱ ቂም በቀሉን መወጣጫ አደርገዋለሁ ለሚለውን የትግራይ ህዝብ ሰላም እንዳያገኝ ሻዕብያ መጣብህ ሊያጠፋህ ነው እያለ የትግራይ ህዝብ ሰላምና ኡፈይታ አግኝቶ አርሶ ሰርቶ ሰላማዊው ኑሮው እንዳይኖር በትግራይ ህዝብ ከባድ ጫና በመፍጠር ማለቅያ የሌለበት ጦርነት ሊማግደው ስለሚፈልግ ሻዕብያ በጀብሃ ያደረሰው ጥቃት በትግራይ ህዝብ ደም ብቀላውን ሊወጣ ፍላጎቱ ግልፅ እየሆነ ነው ።
በዚህ ብቻ ደብረፅዮን አልተወሰነም በትግራይ ክልል ድንበር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ወንድሞቹ በደምና በሥጋ ዝምድና የተሳሰሩ ህዝብ አካሉ የሆኑት የአማራ ክልል በጎንደርና በወሎ በአፋር ክልል ወዘተ የመሬት ወረራ በትግራይ ስም እየፈፀመ፤ ህዝብ ለህዝብ እያጋጨ ያለው ይህ ከኤርትራ የመጣ የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚ የጀብሃ ታጋይ የነበረው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ነው። የትግራይ ህዝብ ከወንድሞቹ እያጋጩ ችግር እየፈጠረ፤ ችግሩን እየሎኮስ የእሳት ጭድ የሚያቀጣጥለው ያለ የትግራይ መሪ ተብየው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዋና ተጠያቂም ነው። ከኤርትራ ከጎንደር ከወሎ ከአፋር ከሸዋ ከጎጃም ወዘተ የትግራይን ህዝብ እያጣላ ጥላቻም እየፈጠረ እያራራቀ የህዝብ እልቂት እንዲከሰት የውሸት ዲስኩሩ እያስፋፋ ይገኛል። ይህም ዋናው የወያኔ የእለት ሥራና ተግባር ሆነ በየቀኑ የሚታይ ሓቅ ነው።
የትግራይ ህዝብ ሰላምና እፎይታ ካጣ እንሆ ዛሬ 45 አመቱን ሞልቶታል፤ በወያኔ የባርነት ሰንሰለት ከወደቀ የአንድ ትውልድ ዘመን ሆኖታል። የትግራይ ህዝብ ኩሩ ኢትዮጵያዊ የሃገሩን ዳር ድንበር አስከባሪ ኢትዮጵያዊ ጀግና በዚህ የወያኔ አሰቃቂ ኑሮ ነፃነቱ የተቀማ ህዝብ በወያኔ ተገድሎ ተረሽኖ ያለቀ የትግራይ ህዝብ ነው። ይህ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ጀግና ትግራዋይ ዛሬ በወያኔ የባርነት ሸንሸል ታስሮ አንገቱን ቀና አርጎ መሄድ የማይችል ቀናም ካለ አንተ ባንዳ እየተባለ እየተሰደበ ስቃይና መከራ በወያኔዎች እየደረሰበት ይገኛል። ደብረፅዮን የግሉ ቂም በሻዕብያ የቋጠረው በትግራይ ህዝብ ስም ኤርትራውያን ሊበቀል ሊበቀል ይፈልጋል፤ የትግራይ ህዝብ በሻዕብያና በጀብሃ የተከሰተው ነገር ምንም አያውቀም፤ የተከሰተው በኤርትራ ውስጥ በሁለት ኤርትራውያን ወንድማሞች መሃከል ነው፤ ለምን ደብረፅዮን የትግራይ ህዝብ ወደ ማያውቀው የማይመለከተው የጦርነት እሳት ትግራይን ሊማግድ ፈለገ? ህዝብ ፍርድህን ስጥ!!
ከትግራይ አጎራባች ክልሎች ከጎንደር፤ ከወሎ፤ ከአፋር ወንድማዊ ህዝብ ደም እያቃባው ይገኛል።ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ለምን ትውልድ ሃገሩ ኤርትራ ሂዶ ሜዳው ፈረሱ ካገኘ አይበጠብጥም (ዓዲያ ዘይብሉስ ዓደይ ዓድዋ ይብል) “ትውልድ ቦታውን የደበቀ ተውልዴ ዓድዋ ነው ይላል”። ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዓድዋ የምትባላው አውራጃ አያውቃትም፤ የትግራይ አውራጃዎች ጨምሮ ምክንያቱም አላደገበትም ሽሬ ሸራሮ ያወቃትም፤ ያያትም በ1974 ዓም ነው። በወያኔ የተሰጠው ምርቃት ነው የትግራይ መሪ የሆነው ኤርትራዊ በመሆኑም እሱ ብቻ አይደለም ብዙ ናቸው፤ ለምሳሌ እንውሰድ መለስ ዜናዊ፤ ሙሉ ሓጎስ፤ ተክሌ መሓሪ፤ “ሙሴ” ብርሃነ ገ/ክርስቶስ፤ ግደይ ዘራርአፅዮን፤ ቴድሮስ ሓጎስ፤ ስብሓት ነጋ፤ ሥዩም መስፍን፤ ፃድቃን ገብረተንሳይ፤ ሃለቃ ፀጋይ በርሄ፤ ቴድሮስ አድሓኖም ኣረ ስንቱን የትግራይ ትውልድ የሌላቸው ከወያኔ ተቀላቅለው ከ1967ዓም እስከ አሁንዋ ሰአት ትግራይን እየመርዋት ያሉት። ከሚያሳዝነው ነገር ዋናውናም የትግራይ ክልል ብሎ ህወሓት ወያኔ ከጠራት ከ1985ዓም ለመጀመሪያ ጊዜ የግል ንብረታቸው በመያዝ የምትመራውም፤ የትግራይ ፕሬዚዳንት አንድ ኢትዮጵያዊ የትግራይ የእንደርታው መቀሌ ተወላጅ አቶ ገብሩ አስራት በርእሰ መሪነት ነበር፤ በ1993 ዓም እሱን ከድርጅቱ አባርረው የሚፈልጉትና ሲመኙት የነበሩቱን ትግራይ በራስዋ ልጆች መመራት የለባትም በሚለው በወያኔው በፖሊሳቸው መሰረት ከኤርትራ በተሰባሰቡ ባንዳ የባንዳ ልጆች እንድትመራ በመለስ ዜናዊና በስብሓት ነጋ ተወሰነ። በዚሁ መሰረት ተከታትለው የመጡ ትውልደ ኤርትራውያን የትግራይ ክልል ርእሰ መሪዎች ሆኑ። ለአብነት እንመልከት! …
    ሃለቃ ፀጋይ በርሄ፤
    ዓባይ ወልዱ
    ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ተሾመ። 
ትግራይና ህዝብዋን እንደፈለገው እያሸማቀቁ ወያኒያዊ የባርነት አገዛዙን በማጠናከር ህዝብ ለስደትና ርሃብ በሽታ እየዳረጉት የመጡትም ከሃለቃ ፀጋይ በርሄ ንግሥና ጀምሮ ሲሆን በፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት የሚታወቀው ባንዳው መሪው ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ለከፋ ደረጃ የትግራይ ህዝብ ተዳርጎ ይገኛል። የደብረፅዮን ገ/ሚካአኤል እውነተኛ የሂወት ታሪኩ ይህ ነው።
ህወሓትና የኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት
ዘረኛውና ጠባቡ ህወሓት ፀረ ኢትዮጵያ ሏሉአላዊነት ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት መሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አጠናቅቆ የሚያውቀው ሓቅ ነው። በሃገርና በህዝብ የሚነግድ ወረበላ ማፍያ ነጋዴ ሓፍረት ቢስ ፀረ ኢትዮጵያና ህዝብዋ ህወሓት ወያኔ መሆኑ መላው የኢትዮጵያ በሚገባ ያውቃል ስለሆነም ህዝብ እናት ሃገሩ ኢትዮጵያና የራሱን አንድነት ይጠብቅ። ወያኔ ደደቢት በረሃ የገባው 1ኛ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ለማፍረስ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ለመናድና ለመበታተ፤ 2ኛ የኢትዮጵያን ታሪክ መሉ አሻራው አጥፍቶ የራሱን ዝና ለመፍጠር የወያኔን ታሪክ ለመፍጠር እና ለመፃፍ፤ 3ኛ አማራ ህዝብ የአማራው ጨቋኝ ገዢ ስርአት እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ጨምረህ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት መደምሰስ አለብኝ ብሎ እቅድና ፖሊሲ አዘጋጅቶ ይህ ተግባራዊ በማድረግ “ታላቅዋ የትግራይ ዲሞክራሲያዊት ሪፑብሊክ” ስርአት መፍጠርና ትግራይን ከኢትዮጵያ ተገንጥለው ነፃ ሃገር ትግራይ መመስረት ነው በማለት የወያኔ የትግል መርሆ ከዋና አላማው አንዱ ይህ ነው።
ህወሓት እና የ2010 ዓም ለውጥ!!
የህወሓት መሪዎች ደርግን አሸንፈን ኢትዮጵያና ህዝብዋ ተቆጣጥረን እጃችን ውስጥ አስገብተን እንገዛለን የሚል ሃሳብ ፍፁም አልነበራቸውም። የነሱ ትልቁና ዋነኛው ዓላማቸው ትግራይ ከደርግ ተዋግተን ትግራይ ነፃ እናወጣለን፤ ትግራያም ከኢትዮጵያ ገንጥለን የራስዋ የሆነ ነፃ መንግሥትም ትመሰርታለች ነበር የህወሓት ዋናው ዓላማ። የትግላቸው ፖሊሲም አላማው ይህ ነው። ይህን ፖሊሲና የትግል አቋማቸው ተከትለው የካቲት 11 ቀን 1967ዓ.ም “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት” (ትህነአድ)ተብሎ በይፋ ተመሰረተ። በየካቲት ወር 1968 ዓ.ም. በዲማ ጉባኤ በድርጅቱ ሊቀ መንበር አረጋዊ በርሄ የትግሉ ማኒፈስቶ ‹መትከል› በእነሱ አጠራር ይህ ማለትም የትግሉ ፖሊሲ አቋም፤ ድርጅቱም አዲስ ስም እንዲሰጠው በነበሩት ጥቂት ታጋዮች ውይይት ከተደረገ ማኒፈስቶው ፀደቀ። የድርጅቱ ስምም “ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ” (ተሓህት) ተባለ፤ ይህ ማለትም ህወሓት ቀጥሎም ማሌሊት ተመልሶም ህወሓት ስሙን እየለዋወጠ የመጣ አጭበርባሪው ድርጅት ህወሓት ነው። ይህ ድርጅት ሲፈጠር ከመነሻው ፋሽሽት ድርጅትም ነው፤ መሪዎቹ ከኛ በላይ አዋቂ በዚች ዓለም አልተፈጠረም፣ አይገኝም፤ የሚሉ የዕውቀት ድሆች ናቸው፤ ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጥና በውይይት ነገር መፍታተ እንደሚቻል ፍፁም አያውቁም፤ አእምሯቸው የአለት ድንጋይ፤ ፍፁም በዚች ምድር የድንጋይ ዘመን ቅሪቶች ይፈለጉ ቢባል የህወሓት መሪዎችና አባሎቻቸው ብቻ ናቸው።
በኢትዮጵያ በ2010 ዓም የተፈጠረው ለውጥ ህወሓት/ወያኔ ግንቦት ወር 1983 ኢትዮጵያን በመውረር ሃገርና ህዝብ ከተቆጣጠረ ለ27 አመታት በፋሽሽታዊ ስርአቱ ሃገርና ህዝብ ያጠፋ ፀር ድርጀት የኢትዮጵያ ህዝብ ህፃን ወጣት ሽማግሌ ሴት ወንድ ሳይለይ ለ27 አመታት በምሬት ታግሎ ከባድ መስዋእትነት ከፍሎ ከመንበር ሥልጣኑ ከምኒሊክ ቤተ መንግሥት ወያኔን ንቅሎ ያባረረው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ነው። ወያኔ በ27 ዓመቱ የስልጣን ዘመኑ የፈፀማቸው ወንጀሎች ዘግናኝ አሰቃቂ ድርጊቶች የፈፀመ መንግሥት አረመኔ ስርአት ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ያፈረሰ፤ ኢትዮጵያን ያዳከመ በዘር በቋንቋ ኢትዮጵያን የሸነሸነ በአንድነት የቆየ ህዝብዋን አንድነቱ ያወደመ ህ፣ወ.ሓ.ት.ነው፤መሬት የመንግሥት ብሎ መሬቱን ከኢትዮጵያ ህዝብ በመንጠቅ የድርጅቱ አባላትና ካድሬዎቹ ሰፋፊ መሬት በመስጠት ለውጭ ሃገር ባለ ሃብት ሰዎች በመሸጥ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለችግርና ረሃብ የዳረገ ወያኔ ነው። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተቋማት በወያኔ ተወርሰው የመንግሥት ነው በሚል ሽፋን እንደ ብሄራዊ ባንክ ንግድ ባንክ ሌሎች ባንኮች የመድን ኢንሹራንሶች፤ መብራት ሃይል ማእድኖች ሆስፒታሎች ትልልቅ ሆቴሎች ፓርኮች ወዘተ በመንግሥት ሽፋን በህወሓት/ወያኔ ተወርሰው 27 ዓመታት ሙሉ በጥቂት የህወሓት መሪዎቸና ካድሬዎቻቸው ሙሉ በሙሉን ተዘርፈዋል። ሃገር ደህይታ ህዝብ ለችጋር ለመከራ ድህነት ለበሽታ ርሃብ ስለተጋለጠ ከዚህ ባገኝ ብሎ ለስደት የተዳረገው ኢትዮጵያዊ በዛም የውሃ ሽታ ሆኖ የቀረው የኢትዮጵያ አምላክ ይቁጠረው።
በወያኔ የ27 ዓመት ስርአት ኢትዮጵያና ህዝብዋ በወያኔ ህወሓት የአገዛዝ ዘመን ወድመዋል ጠፍተዋል። ኢትዮጵያ ወደ ግላጭ ድህነት ወደቀች ህዝቧም እንኳንስ የሚበላ እህል የሚጠጣ ውሃ ያጣበት በዚሁ የወያኔ የ27 ዓመት አገዛዝ ዘመን ብቻ ነው። ኢትዮጵያ በወያኔ ህወሓት ተዘርፋለች። ዝርፍያው በዚህ የተወሰነ አልነበረም። ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ወያኔ ባስቀመጠው በትግል ፖሊሲው ማኒፈስቶው ታላቅዋን የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ለመመስረት ከወሎ ጠ/ግዛት ከአለውሃ ምላሽ እስከ ራያ ድረስ፤ ከጎንደር ጠ/ግዛት ሰሜን ጎንደር በሙሉ እንዳለ ወደ ትግራይ መጠቅለል አለበት። በማለት በማኒፌስቶው በማስገባት በጉልበትና በጠመንጃ ሃይል መሬቱን ወረው ተቆጣጠሩት የሰሜን ጎንደር ህዝብ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ከፍተኛ ቁጥር በክፉ መልኩ ታህሳስ ወር 1972 ዓ.ም ወያኔ ሃይሉ ሰብስቦ 1ኛ ታጋዩ 2ኛ ወየንቲ (ምልሻው) 3ኛ ክርቢት(ክራቢት) ክርቢት ወያኔ በልዩ ታክቲክ አሰልጥኖ ሽብርና ግድያ የሚፈፅሙ ናቸው። ሰሜን ጎንደር በተለያዩ አቅጣጫ በማሰማራት በንፁህ ህዝብ የሲኦል ነበልባል ወረደ ህዝብ ሞተ፤ ተገደለ፤ ሂወት በመሬቱ እንደቅጠል አረገፉት፤ ሃብቱ ንብረቱ ሁሉ በህወሓት ውርስ እየተባለ ተዘረፈ፤ ሂወቱን ይዞ ያመለጠ ደግሞ ለስደትና ለእንግልት ተዳረገ።
ወያኔ በጉልበቱ ሥልጣን ከጨበጠም ኢትዮጵያን ክልል ብሎ በመከፋፈል ለዕድሜው ማራዘሚያ የተጠቀመብት ዘዴ በሌላም በኩል የትግራይን ግዛት በበለጠ ለማስፋፋት ይጠቅመኛል በሚል እሳቤ የተቀናጀ ነው። ለምሳሌ ላይ አርማጮህና፤ ታች አርማጮህ፤ መተከል፤ የትግራይ ግዛት ናቸው ተብለው ወያኔ እንደልማዱ ለመቀማት በትግራይ ካርታ አካቶ ካርታውን እያሰራጨ እንደነበር ሁላችን ያየነው እውነት ነው። ህወሓት ከልደተ ጥምቀቱ ሲፈጠር ፀረ ኢትዮጵያ ነው፤ ህወሓት ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ነው። ህወሓት ከወራሪው የሞቃድሾ መንግሥት ሳይድ ባሬ በ1969ዓም በመተባበር ኢትዮጵያን የወጋና ያቆሰለ የለየለት ከሃዲ ድርጅት ነው። ህወሓት የኢትዮጵያን ግዛት አሳልፎ ለሱዳን መንግሥት የሸጠ ከሃዲ ድርጅት የጠላት መሳሪያ ነው፤ ህወሓት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ነው፤ በተለይ በአማራው ላይ የፈፀመውና እየፈፀመው ያለውን ህወሓት ወራሪና ተስፋፊ ድርጅት ነው፤ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ኢሰብዓዊ በሆነው መንገድ የትግራይ ህዝብ አጥፍቶታል፣ ገድሎታ፣ ታርደዋል። ህወሓት በፈፀመው ኢሰብዓዊ ድርጊቶች ተጠያቂ ወንጀለኛ ስለሆነ በሕግ መጠየቅ አለበት። የተከበርከው የትግራይ ህዝብ በዚሁ ወንጀለኛ ድርጅት ህወሓት የስቃይ መክራ ሲኦል ከወረደብህ ከየካቲት ወር 1967 ዓም እስከ ዛሬዋ እለት 2012 ዓም 45 አመታት ሙሉ በባርነት ተይዘህ ወያኔ በስምህ ነግዶብሃ፤ ባንተ ስም ያልፈፀመው ወንጀል የለም፤ አሁንም እየተጠቀመብት። ተነስ ከዚሁ የወያኔ የባርነት አገዛዝ ራስህን ነፃ አውጣ ወያኔ የነጠቀህን ክብርህን መልሰው በቃኝ በል የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ካንተ ጋር ነው ያለው።ለተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ መልእክቴን ማተላለፍ የምፈልገው በህወሓት ወሳኝ እርምጃ ካልወሰድክ ወያኔ ካለ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላምና ተባብሮ መኖር እፎይታም ማግኘት በፍፁም አይቻልም አይታሰብም።
Filed in: Amharic