>

ባልተለወጠዉ ስርዓት የኢትዮጵያ እናቶች እንባ ዛሬም መቆሚያ አጥቷል!!! (ከባልደራስ የተሰጠ መግለጫ)

ባልተለወጠዉ ስርዓት የኢትዮጵያ እናቶች እንባ ዛሬም መቆሚያ አጥቷል!!!

 

 

ከ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ፤

* ይህ የሽብር ሰንሰለት መሪና ተመሪ ያለዉ በዉጪ ሃይል የሚደገፍ በመንግስት ውስጥ ባሉ ሴሎች እርዳታ የሚቸረዉ መሆኑ መንግስት ያሳየዉ ችለተኝነት ጥሩ ማሳያ ነዉ!

ዛሬ የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ስራ አስፈጻሚ ባደረገው ስብሰባ ከ2 ወር በላይ ታግተው  ስለሚገኙት የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በታጠቀ ሃይል ታፈነዉ እየደረሰባቸዉ ስላለዉ መከራና የቤተሰቦቻቸዉ መሪሪ ሐዘን በጉዳይ አሳሳቢነት አመራሩ ተወያይቶበታል።
 በሀገራችን በተደራጁ ሽብርተኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ የመጣዉ የመንጋ አስተሳሰብና ተረኝነት ዜጎች የደህንነት ዋስትና አደጋ ላይ መውደቁ  የደንቢዶሎ የተማሪዎች አፈና ጠቋሚ ነገር ነው።
የታገቱት ንጹሓን እህቶቻችን ከአጋቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸውን ተማሪዎች አፍኖ በመያዝ እና ሰይጣናዊ ተግባር በአካላቸዉ ላይ በመፈፀም የሚመለስ ጥያቄ ካለመኖሩም በላይ፣ ድርጊቱ የሽብር ተግባር በመሆኑ  ፓርቲያችን በፅኑ ያወግዘዋል።
ይህ የሽብር ሰንሰለት መሪና ተመሪ ያለዉ በዉጪ ሃይል የሚደገፍ በመንግስት ውስጥ ባሉ ሴሎች እርዳታ የሚቸረዉ መሆኑ መንግስት ያሳየዉ ችለተኝነት ጥሩ ማሳያ ነዉ።
መንግስት የህዝብን ጩኸት አዳምጦ ፈጣን መልስ ለዜጎች ከመስጠት ይልቅ ለጉዳዩ የሰጠዉ የትኩረት ማነስ ለታጋች ቤተሰብና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንቆቅልሽ አድርጎታል።
የፌደራል መንግስት የተማሪዎችን ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ፣  በቃል አቀባዮ በኩል የሰጠው የሀሰት መረጃ ኃላፊነት የጎደለው ከመሆኑም በላይ፣ የአጋቾች ተባባሪ ሆኖ በተጎጂዎች ማፌዝ  ያልተለወጠዉ ስርዓት ባህሪ ሆኖ አይተነዋል።
በተቃራኒው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከዳር እስከ ዳር አንድ ላይ በመቆም ድርጊቱን በማውገዝ እና መንግስት ላይ ያሳድረው ጫና በህዝባችን አንድነት እንድንኮራ አድርጎናል።
ስለሆነም፣ ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ መንግስት የተማሪዎቹን ሁኔታ ለህዝብ ሳይደብቅ እውነታውን እንዲያሳውቅ ፓርቲያችን ይጠይቃል።
በሌላ በኩል በመንግስት ላይ ህዝብ እያደረገ ያለውን ጫና ድርጅታችን የሚደግፈዉ ተግባር በመሆኑ ሁሉም የፓለቲካ ኃይሎች ድርጊቱን በመቃወም ከኢትዮጵያ እናቶች እንባ ከታገቱት ተማሪዎች ስቃይ ጎን እንዲሰለፍ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል።
ለታገቱት ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቸሩን ሁሉ እንዲያሰማን ፓርቲያችን ይመኛል።
  ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
 አዲስ አበባ
ጥር 18/2012 ዓ.ም
Filed in: Amharic