>

የባህርዳር ህዝብ እምባውን እያፈሰሰ ድምጹን አሰምቷል! ሰብዓዊነትን መቀለጃ ያደረጉ ባለስልጣናት ፍትህ ካለ ለህግ ይቅረቡ!


ሰብዓዊነትን መቀለጃ ያደረጉ ባለስልጣናት ፍትህ ካለ ለህግ ይቅረቡ!!!

ታደለ ጥበቡ
 

* የባህርዳር ህዝብ እምባውን እያፈሰሰ ድምጹን አሰምቷል፦

” ተማሪዎቹ ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ ተደብቀው ከሆነም እያጣራን ነው!” 
የፌደራል ፖሊስ ምልትል ኮምሽነር መላኩ ፈንታ
የታገቱ ተማሪዎችን አስመልክተው የፖሊስ ባለስልጣን የሆነ ግለሰብ ለተጠየቀው ጥያቄ ተዘባብቷል። በወላጆች እምባ ላይ ቀልዷል። ከሕዝብ በተሰበሰበ ግብር ደምወዝ እንደሚከፈለው ዘንግቷል።ነገ ማእረግና የደምወዝ ጭማሪ ለማግኘት ራስን ለሐሰት መሸጥ ነውር ነው። ፖሊሱም፣ ደሕንነቱም፣ መከላከያውም፣ የመንግስት ባለስልጣን ሁሉ የታገቱ ተማሪዎችን የውሸት ትርክት ማወራረጃ አድርገዋቸዋል።
አስነዋሪው የመንግስት ወንበዴዎች ቃላቶቻቸው አፀያፊዎች ናቸው
– ተማሪዎቹ ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ ተደብቀው ከሆነም እያጣራን ነው።
– የታገቱት ሰዎች ወላጆች እኛ ቢሮ መጥተው ስላልነገሩን ስንት ተማሪ እንደጠፋ መረጃ የለንም፣ላንች እንደነገሩሽ ለእኛም መንገር ነበረባቸው።ብለዋል የፖሊሱ ባለስልጣን ! መላኩ ፈንታ የተባለው የፌደራል ፖሊስ ምልትል ኮምሽነር ባለስልጣን ነው።በቪ ኦ ኤ በታገቱት እህቶቻችን ላይ ቀለደ። አጋቹ ማን እንደሆነ ግልፅ እየሆነ ነው።
መንግስት የዜጎችን ደሕንነትና ሰላም ከመጠበቅ ይልቅ ከዜጎች በሚሰበስበው ግብር ሕዝብን እያጋጨ መግዛትን መርጧል። ባለስልጣናት የመንግስትን ገበና የደበቁ እየመሰላቸው መንግስትን እያጋለጡት መሆናቸውን ሊያውቁ ይገባል።
ባህርዳር እንዲህ ድምጻቸውን እያሰሙ ናቸው፦
1.ተማሪዎች የታገቱት በጥፋታቸው ሳይሆን በአማራነታቸው ነውና በአስቸኳይ ይለቀቁልን!!
2.በለፋበት ሀገር የሚንገላታ ህዝብ አማራ!!
3.ከ54 ሺህ በላይ የተፈናቀሉ የአማራ ተማሪዎች መልስ ይሰጠን!!
4.የአማራ ተማሪዎችን ማሳደድ ይቁም!!
5.የምንሳደደው በአማራነታችን ስለቆምን ብቻ ነው!!
6.መንግሥት አለ ወይ?
7…ዘግይተን ሳይሆን ቀድመን እንደርሳለን ያለከነሰ የት አለህ?  (ለደመቀ መኮነን)
8.እህቶቻችን የውሸት ትርክት ማወራሪጃ አይሆኑም!
9.54 ቀናት ዝምታ የዋጠው መንግስት ሊመራ አይችልም!!
10.የአማራ ስቃይ ቸል የተባለው ተረኛ ፖለቲከኞች ባላቸው ጥላቻ መሆኑ ግልፅ ነው!
11.ለታፈኑት ተማሪዎች መቆም የብሔርና የሃይማኖት ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው!
12.አማራነት በፈተናዎች ሁሉ የሚያጎነብስ ሳይሆን ቀና የሚል ነው!!
13.በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በማንነታቸው የሚሳደዱ የአማራ ተማሪዎች ጥያቄ ይመለስ!!
14.የህወሓት የበላይነት በኦነግ የበላይነት እንዲተካ አንፈልግም!!
15.where are our boys and girls
16.ተለቀቁ ያልካቸው የአማራ ተማሪዎች የት አሉ? (ለንጉሡ ጥላሁን)
Filed in: Amharic