>

* የኔ ዜግነት ኢትዮጵያዊት ነው ተቀይሮ አያውቅም....!"  (ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ - ቪ.ኦ.ኤ)

“አሁን ዴሞክራሲ በተግባር!!!”

ቪ.ኦ.ኤ

የኔ ዜግነት ኢትዮጵያዊት ነው ተቀይሮ አያውቅም….!”

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
 
ኦፌኮ ቀነ ገደብ ያለው ሁለተኛ ማስጠንቀቂያ ከምርጫ ቦርድ ተልኮለታል!!!
 
•“ጉዳዩ በሕጉ መሠረት እልባት እንዲያገኝ እናደርጋለን” ብሏል ኦፌኮ
 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአቶ ጃዋር መሐመድን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሁኔታን እንዲያረጋግጥ ቀነ ገደብ የተቀመጠለት ሁለተኛ ደብዳቤ ለኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጻፈ። ኦፌኮ በበኩሉ ጃዋር መሐመድ ዜግነቱን ካልቀየረ እንሰርዘዋለን  ብሏል። (ዝርዝሩን ያዳምጡ።)
ቪኦኤ -“በማህበራዊ ድረ-ገጾች ወይዘሪት ብርቱካን ራሳቸው ኢትዮጵያዊ አይደሉም የውጭ ሀገር ዜግነት ነው ያላቸው” እየተባለ በስፋት ይናፈሳል። ለመሆኑ እርሶ ራስዎ ኢትዮጵያዊ ኖት ወይ?!
ወይዘሪት ብርቱካን – በእውነት ለዚህ ጥያቄ ምላሽ መስጠት በጣም ያሳዝናል። ምክኒያቱም ይህ ሀላፊነት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሳይኖር ሊወሰድ የሚችል ሀላፊነት አይደለም።
 በመጀመሪያም ለመንግስት በሰጠሁት መረጃ ኢትዮጵያዊ ዜግነቴን ያለቀቅኩ መሆኑን፣ ሳልወድ ተገድጄ ሀገሬን ለቅቄ በሄድኩበት ወቅትም በስደተኝነት (ጥገኛ) ሆኜ የቆየሁ መሆኑን አረጋግጬ ምዬ ነው ሀላፊነቱን የወሰድኩት።
እና እንዲህ ያለው ጥያቄ ተመልሶ ሲመጣ ትንሽ ያሳዝናል። ነገር ግን እንደኔ ላለ ሰው ተቃራኒውን መረጃ ሰጥቶ ይህን አይነት ሀላፊነት ከወሰደ ተራ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በወንጀልም ሊያስጠይቅ የሚገባ ነው።
እንደኔ አይነት በሙያውም በስልጠናም አልፎ እዝህ የደረሰ ሰው “ምንም ችግር የለውም” ብሎ ሊያደርገው የሚችለው ነገር አይደለም። የኔ ዜግነት ኢትዮጵያዊ ነው።ተቀይሮ አያውቅም!!!”
Filed in: Amharic