>
12:14 am - Thursday December 1, 2022

ዐብይ አህመድ፤ የማካካስ በሽተኛ (መስፍን አረጋ)

ዐብይ አህመድ፤ የማካካስ በሽተኛ

 

መስፍን አረጋ 

 

ከሰካራም አፍ ሚስቱ አትጠፋም

ሰካራም ባል ሚስቱን አመስግኖ እንደማይጠግብ የታወቀ ነው፡፡  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሚያወራው ስለሷ መልካምነት ነው፡፡ ይህን የሚያደርገው ደግሞ በሰካራምነቱ ሳቢያ በሚስቱ ላይ የሚደርሰው ዘርፈብዙ ጉስቁልና ሕሊናውን ስለሚሸነቁጠው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ባሕሪ ልቦናሲነኛወች (psychologists) ማካካስ (compensation) ይሉታል፡፡  ባጠቃላይ አነጋገር ማካካስ ማለት ያንድን ዘርፍ ደካማነት በሌላ ዘርፍ ጠንካራነት ለመዋጥ (ለመሸፋፈን ወይም ለማድበስበስ) ሲባል በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚደረግ ያላሰለሰ ጥረት ማለት ነው፡፡ 

የዐብይ አህመድ ድርጊቶች ሁሉም የሚጠቁሙት ግለሰቡ በሥርሰደድ (chronic) የማካካስ በሽታ በጽኑ የታመመ  የልቦናሲን (psychology) በሽተኛ ሳይሆን እንደማይቀር ነው፡፡  ዐብይ አህመድ የልቦናሲን በሽተኛ መሆኑን ለመጠርጠር ደግሞ ልቦናሲነኛ (psychologist) መሆን አያስፈልግም፡፡  አኳኋኑ ግልጽ ስለሆነ፣ ምንነቱን ለመረዳት ሕገ ልቦና (common sense) ብቻ በቂ ነው፡፡             

ስለ ሰላምና ስለ ፍቅር አውርቶ የማይታክተው ዐብይ አህመድ፣ የሰላምና የፍቅር ቀንደኛ ጠላት ስለሆነ ይሆናል፡፡  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ መግደል መሸነፍ ነው የሚለው፣  ማሸነፍ መግደል ነው በሚል መርሕ የሚመራ ደም ጠማሽ ስለሆነ ይሆናል፡፡  ሸካችነቱን (ፖለቲከኛነቱን) የዘነጋ ይመስል ኖላዊ (pastor) ለመምሰል የሚጣጣረው፣ በክርስትና የማያምን ኢሬቸኛ ስለሆነ ይሆናል፡፡  አባቱን ስማችውን ሳይጠቅስ እናቱን አለመጥን የሚያሞግሰው፣ በእናቱ ምንነትና ማንነት አለመጥን ስለሚያፍር ይልቁንም ደግሞ እንዲያፍር ስለተደረገ ይሆናል፡፡  እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የብቸነት ኑሮ ትገፋ የነበረቸውን እማወራ (single mother) ሚስቱን አለመጠን የሚክባት፣ በጓዳ የሚያዋርዳት የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ ስለሆነ ይሆናል፡፡ ጦቢያ፣ ጦቢያ በማለት የጦቢያ ብሔርተኛ ለመምሰል የሚጣጣረው ደግሞ የለየለት ፀረጦቢያ (ኦነጋዊ) በመሆኑ ይሆናል፡፡ 

በልጅነቱ ጫካ ገብቶ ሐይማኖትና ምግባር ከሌላቸው፣ በነውር ከተጨማለቁ፣ በጎጠኝነት ከታወሩ፣ በጥላቻ ካበዱ፣ በስቃይ ከሚደሰቱ፣ በደም ከሚታጠቡ ከወያኔ ጉምቱወች እግር ሥር ያደገ ግለሰብ በኣካልም ሆነ በመንፈስ ጤነኛ የመሆኑ ዕድል እጅግ የመነመነ ነው፡፡  ጤነኛ ካልሆነ ደግሞ ጤነኛ አለመሆኑን የሚያረጋግጡ መረጃወች ያላቸው ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በመረጃቸው እያስፈራሩት (black mail) አድርግ ያሉትን ሁሉ እንዲያደርግ ሊያስገድዱት ይችላሉ፡፡  

ዐብይ አህመድ ጃዋር ሙሐመድን አለቅጥ የሚፈራው፣ ለማ መገርሳን ደግሞ ‹‹ቀድሞ የይፋ አሁን የሕቡዕ አለቃየ›› እያለ አለቅጥ የሚሽቆጠቆጥለት ወዶ ሳይሆን ተገዶ ሊሆን ይችላል፡፡  ጃዋር ሙሐመድ ያገኘውን ክፍተት የሚበረግድ ወንበዴ ሲሆን፣ ለማ መገርሳ ደግሞ ባገኘው ቀዳዳ የሚገባ ሸለመጥማጥ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም፡፡  የወያኔው ጌታቸው ረዳ ደግሞ እናጋልጣለን እያለ ዘወትር የሚዝተው የያዘውን ቢይዝ ነው፡፡ እስካሁንም ያላጋለጠው መረጃው ዐብይ አህመድን ብቻ ሳይሆን ወያኔንም የሚያጋልጥ በመሆኑ ይሆናል፡፡     

አያሌ አገር ወዳድ ጦቢያውያን የዐብይ አህመድ ወላጅ እናት አልኦሮሞ (non-oromo) መሆን የዐብይን የኦሮሞ ጎጠኝነት ስሜት ያለዝበዋል የሚል እምነት ነበራቸው፣ አላቸውም፡፡  ታሪክ የሚመሰክረው ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፡፡ ያንድ ብሔር አባል አለመሆኑ የሚጠረጠር ግለሰብ የዚያ ብሔር ጽንፈኛ ከሆነ፣ በብሔሩ አባልነቱ ሊጠረጠር እንደማይገባው በግልጽ ለማስመስከር የማያደርገው የለም፡፡  ሂትለር ይሁዳወችን ያለ ርኅራኄ የጨፈጨፈበት አንዱ ምክኒያት የይሁዳ ደም አለበት የሚባለውን ጭምጭምታ ለማስተባበል ነበር፡፡  ጌታቸው አሰፋ በላኤአማራ የሆነበት አንዱ ምክኒያት አባቱ አማራ ቢሆኑም ‹‹ከሙሉ ትግሬወች›› በላይ አማራጠል መሆኑን ለማስመስከር ነው፡፡  ዐብይ አህመድ ደግሞ ግማሽ አማራ ከመሆኑ በላይ ካማራ ጋር የተጋባና የተዋለደ በመሆኑ፣ ፀራማራ ልሁን ካለ ፀራማራነቱ ከጌታቸው አሰፋ ቢብስ እንጅ አያንስም፡፡  

በነገራችን ላይ አብዛኞቹ የኦነግ፣ የወያኔና የሻቢያ ፀራማሮች ካማራ ጋር የተጋቡና የተዋለዱ እና/ወይም ባንድም ሆነ በሌላ አማራነት ያለባቸው ናቸው፡፡  እነሱ ራሳቸው ከሚስቶቻቸው ጋር ባማረኛ ሲንሾካሾኩ እያደሩ ሌላውን አማረኛ አትናገር የሚሉ ተመጻዳቂወች፡፡   

ዐብይ አህመድ፣ ፀጋየ አራርሳና የመሳሰሉት ግማሽ አማራ የኦሮሞ ጎጠኞች በኦሮሞነታቸው ስለሚጠረጠሩ፣ ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቁና እያንዳንዷ ድርጊታቸው በጢኖፓይፋ (ባጉሊ መነጸር፣ microscope) እንደምትመረመር አሳምረው ያውቃሉ፡፡  ትንሽ ቢሳሳቱ ግዙፍ ውለታቸው መና ቀርቶ ከሃዲወች እንደሚባሉ ነጋሪ አያስፈልጋቸውም፡፡  እስከጣፈጡ ድረስ ተላምጠው የሚተፉ አገዳወች እንደሆኑ በደንብ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህም እነዚህ ግማሽ ኦሮሞወች ለኦሮሞ ጥቅም ሽንጣቸውን ገትረው የቆሙ መሆናቸው ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገባ ሲሉ ብቻ ‹‹ከሙሉ ኦሮሞወች›› እጅግ በባሰ ደረጃ የጸነፉ ጽንፈኞች መሆን አለባቸው፡፡  ከለማበት የተጋባበት፡፡  

ዐብይ አህመድ ለኦነግ ዓላማ መሳካት ሲል ማናቸውንም ጭራቃዊ ድርጊት ለማድረግ ቅንጣት እንደማያቅማማ በባሕርዳር ድርጊቱ በግልጽ ቢያስመሰክርም፣ ግማሽ ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ ኦነጋውያን መቸም ቢሆን በሙሉ ልብ አያምኑትም፡፡  ስለዚህም ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት ከፈለገ ትናንት ካደረገው የከፋ ዛሬ ማድረግ አለበት፡፡  ይህ ማለት ደግሞ በፀረ ኦነጋውያን ላይ (ማለትም ባገር ወዳድ ጦቢያውያን በተለይም ደግሞ ባማሮች ላይ) ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እያረመነ (አረመኔ እየሆነ) ይሄዳል ማለት ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ዐብይ አህመድ በማንነቱና በምንነቱ ምክኒያት እኩይ አዟሪት (vicious circle) ውስጥ የገባ  የኦነግ አውሬ ነው፡፡  ካዟሪቱ ነጻ የሚያወጣው ደግሞ ዳግም ምጽአት ብቻ ነው፡፡  

 

 መስፍን አረጋ  mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic