>

ኮሮና ቫይረስ ወዳገራችን እንዳይገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች ማቆም አለበት! (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ)

ኮሮና ቫይረስ ወዳገራችን እንዳይገባ አሁኑኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች ማቆም አለበት።

የሰው ህይወት በብር አይተመንም!!!

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ)

* ገንዘብ ከሞት አያድንም

ለብር ሲሉ በህዝብ ጤና አይቀልዱም!

ኮሮና ቫይረስ ወዳገራችን እንዳይገባ አሁኑኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች ማቆም አለበት።
አሁን በደረሰኝ መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚሄዱ የበረራ_ሰራተኞች የአፍ መሸፈኛ (Mask) እንኳን እንዳይጠቀሙ ተከልክለዋል።  በነገራችሁ ላይ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ምንም ዓይነት የህመም ምልክት ሳያሳይ ለ3ና ከዚያ በላይ ቀናት ሊቆይ ይችላል። በዚህ ግዜ ውስጥ ደግሞ በእያንዳንዱ ቀን በአማካይ ወደ ሌላ አንድ ሰው ቫይረሱን ሊያስተላልፍ ይችላል። እኔ በጣም ግርር…ም የሚለኝ ነገር እኮ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የትምህርት ውጤት ያመጡት ሰዎች ከሚቀጠሩባቸው መስሪያቤቶች ውስጥ ግንባር ቀደሙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።
በአንፃሩ ከየትኛውም የመንግስት መስሪያቤት በላይ ጥቂት የወያኔ ሰዎች ከላይ ተቀምጠው እንደ ፈረስ የሚጋልቧቸው እነዚሁን የተሻለ የሙያ ዕውቀት እና ደሞወዝ ያገኛሉ የሚባሉትን ነው። በዚህ ሰዓት ከ10ሺህ በላይ ሰራተኞች ባሉበት አንድ የረባ የሰራተኛ ማህበር መመስረት ያልተቻለው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ብቻ ነው።
ይባስ ብሎ አሁን ደግሞ ሌሎች አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ እየሰረዙ ባለበት ወቅት የእኛው ጉድ እንኳስ በረራ ሊያቌርጥ የበረራ ሰራተኞችን ምንም መከላከያ እንዳያደርጉ ይከለክላል።
 አየር መንገዱ ከቻይና ለሚያገኘው ገንዘብ እንጂ በቫይረሱ ለሚጠቁ ሰራተኞች ሆነ በሀገሪቱ ህዝብ ላይ ለሚደርሰው የጤና_ጠንቅ ደንታ እንደሌለው ለሰራተኞች በላከው የውስጥ መልዕክት (Internal Memo) እንደሚከተለው ገልጿል፦ <<The impact of #corona_virus epidemic severely affecting our business in china and other regions. china is the largest per country market for ET and the decline in business in #china will have significant negetive impact on our financial conditions.>>
…አየር መንገዱ ያሰላው ከቻይና የሚዝቀውን ረብጣ ዶላር ነው ግና ብር ከገዳይ በሽታ አያድንም። የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ቢገባ የሚሞተውን ሰው ህይወት በብር አንመልሰውም። በየለቱ አዳዲስ አገሮች የኮሮና ቫይረስን በዜጎቻቸው እያገኙ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ ወደ ቻይና መመላለሱ አሳዛኝም አሳፋሪም ነው። ከዚህ በረራ የሚገኘው ገቢ ሊያመጣብን ከሚችለው ጉዳት አንጻር ምንም ነው።
WHO ለኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ ተጋላጭነት ካላቸው አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ እንደሆነች ዛሬ መግለጫ አውጥቷል! አሁን ባለን የጤና ተቋማት አቅም ይህንን አይነት በሽታ መቆጣጠር ደግሞ አዳጋች እንደሚሆንብን መገመት አያዳግትም። ስለዚህ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ቻይና የሚደረገው በረራ ይቁም!
Filed in: Amharic