>

በፓርላማ ስብሰባ ላይ የማይገኙ የህወሃት ተመራጮች ያለመከሰስ መብታቸው ሊነሳ ነው!!!  (ታምራት ሃይሉ)

በፓርላማ ስብሰባ ላይ የማይገኙ የህወሃት ተመራጮች ያለመከሰስ መብታቸው ሊነሳ ነው!!!

   ታምራት ሃይሉ 
    አምስተኛው ዙር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑና ከትግራይ ክልል ተመርጠው ፖርላማ የገቡ የህወሃት ተመራጮች ላለፉት 18 ወራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በፖርላማ ስብሰባ ላይ ባለመገኘታቸው ከፖርላማ የማንሳት ስራ ሊሰራ ስለመሆኑ ተሰማ፤አንድ የህዝብ ተመራጭ ያለ በቂ ምክንያት ከፖርላማ ስብሰባ ላይለተከታታይ ስድስት ወራት የሚቀር ከሆነ የመራጮችን መብት ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ የሚፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት የማገድ ስራ የሚሰራ ሲሆን በምክር ቤቱ የአራርና የአባላት የስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 መሰረት የመረጠውን ህዝብ ወክሎ በምክር ቤቱ የማይገኝ ተመራጭ የህዝብ አመኔታ እንዳጣ ተቆጥሮ ከምክር ቤቱ የማንሳት ስራ እንደሚሰራ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
    አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የምክር ቤት አባል እንደተናገሩት የምክር ቤት አባላት በመንግስታዊ የስራ ሀላፊነት ምክንያት ካልሆነ በቀር በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የመገኘት ግዴታ አለበት ብለዋል፡፡ ተመራጩ በስብሰባ ላይ የማይገኝበት በቂ ምክንያት ሲኖር ለአፈ ጉባኤው አልያም ለምክር ቤቱ ጽ/ቤት በፅሑፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ በመንግስታዊ ሀላፊነት ላይ የተመደቡ ተመራጮች ማለትም በሚኒስትር ደረጃ ከተሾመ ወይም በአምባሳደርነት ከተመደቡ አባላት ውጭ ማንኛውም የህዝብ ተመራጭ በመደበኛ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ መገኘት እንዳለበት የምክር ቤቱ ደንብ ያሳያል፡፡
    ያም ሆኖ ይላሉ እኝሁ የምክር ቤት አባል ማንኛውም የምክር ቤት አባል በማናቸውም መልኩ በሀገር ውስጥ እያለ ጠቅላይ ሚነስትሩ በምክር ቤቱ ተገኝተው የስራ ሪፖርት ሲያቀርቡና ማብራሪያ ሲሰጡ እንዲሁም የፌደራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች ለምክር ቤቱ ሪፖርት ሚያቀርቡበት ወቅት የግድ በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የመገኘት ግዴታ እንዳለባቸው በደንቡ ላይ ተመልክቷል፡፡ ያም ሆኖ ባለፉት 18 ወራት ከትግራይ ክልል የተመረጡና ፖርላማ የገቡ 38 የህወሃት ተመራጮች አብዛኛዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዓለ ሲመት በኋላ በፓርላማው ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንደማያውቁ ታውቋል፡፡
       ከእነዚህ የህወሃት የፖርላማው ተመራጮች መሀከል ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፤ አምባሳደር አዲስ ዓለም ባሌማ፤አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ወ/ሮ ሮማን ገ/ስላሴ፤ አቶ መብራቱ መለስ፤ አቶ አፅብሃ አረጋዊ፤ አቶ ታደለ አሰፋ፤ አቶ ካሳ ጉግሳ፤ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሐር፤ ወ/ሮ ማሚት ተስፋይ፤ ወ/ሮ አልማዝ በፖርላማ ስብሰባ ላይ የማይገኙ የህወሃት ተመራጮች ያለመከሰስ መብታቸው ሊነሳ ስለመሆኑ አርአያ፤ አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ፤አቶ አባይ ፀሀዬ፤ አቶ አድሃነ ሀይሌ፤ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ወዘተ ይገኙበታል ተብሏል፡፡
      እነዚህ የህወሃት አባል የሆኑ የምክር ቤት ተመራጮች በስብሰባ ላይ ተገኝተው የመረጣቸውን ህዝብ ድምፅ ባለማሰማታቸው እስከ ምክር ቤቱ የስራ ማጠናቀቂያ ሰኔ 30 2012 ድረስ እንደሚታደገዱና ያለመከሰስ መብታቸውም ሊነሳ እንደሚችል ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ይህ ሂደት ስልጣናቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ካስተላለፉ በኋላ ወደ ምክር ቤት መጥተው የማያውቁትን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ይመልክት አይመልከት የተባለ ነገር የለም፡፡
Filed in: Amharic