>

የኮሮና ተጠርጣሪዎች በትግራይና በአዲስ አበባ !! (ዘመድኩን በቀለ)

የኮሮና ተጠርጣሪዎች በትግራይና በአዲስ አበባ !!

 

 

ዘመድኩን በቀለ
ሚኒሻም አያድንህም። ብልጠትም፣ ጉልበትም ቦታም ሥፍራም የላቸውም። መፍትሄው ንስሐ ገብቶ ተዘጋጅቶ የሚሆነውን መጠበቅ ብቻ ነው። እናም ንስሐ እንግባ። ሰምታችኋል። 
 የመታየታቸው ስጋትና የእግዚአብሔር እውነት!
•••
ወረርሽኝ በሽታው፣ የእርስ በእርስ ጦርነቱ፣ ረሃብና ጠኔው አንደዜ ከመጡ መጡ ነው። ዘር፣ ቀለምና ሃይማኖት የመምረጫ ጊዜም የላቸው። ደግሞም አያዳሉም። እኩል ይለክፉሃል። እኩል ይይዙሃል። እኩል ይጥሉሃል። እኩል ያስተኙሃል። እኩል ያጠፉሃል። ለዚህ ነው አሁን የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገብቶ 1 በትግራይ አክሱም 3 በአዲስ አበባ ከተማ ያዘ የተባለው። በኦሮሚያ ልዩ ዞን 2 ኢትዮጵያውያን እና አንድ ቻይናዊ በአጠቃላይ 7 በቫይረሱ የተለከፉ ተጠርጣሪዎች ላይ ኮሮና ታይቷል ተብሎም ሽር ብትን እየተባለ ያለው።
•••
“ በአሁኑ ወቅትም የበሽታው ምልክት ያሳዩ አራት ሰዎች(suspected cases ) ፤ አንድ ቻይናዊ እንዲሁም ሦስት ኢትዮጵያዋን፤  በሽታው እንሌለባቸው እስኪረጋገጥ ድረስ አንድ በአክሱም እና ሶስቱ በቦሌ ጨፌ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው እና በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን ናሙናቸው ተወስዶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጅት ተጠናቋል” ነው ያለው የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር፡፡
•••
ወዳጄ መለስ ዜናዊ ያደለውን መታወቂያ እያየ ዐማራን፣ የአንገት ማዕተብ እየለየም ኦርቶዶክስን ብቻ መርጠው እየለዩ አሳድደው የሚገድሉትና የሚያርዱት እነ አጅሬ ህወሓት፣ ኦነግ፣ ኦፒዲኦኦዲፒፒፒ እና ጽንፈኞቹ የወሀቢ እስላሞች ብቻ ናቸው። እነሱ ናቸው እየለዩ የሚያስሩህ፣ የሚገድሉህ፣ የሚያግቱህ፣ የሚያኮላሹህ። እነ ኮሮና፣ እነኮሌራና እነ ኢቦላ ግን ፍትሃዊ ናቸው። ገዳዮችንም ይገድላሉ። የሚያስራቸው፣ የሚያግታቸውም ኃይል የለም። ማንንም አይምሩም። ማንንም አይፈሩም፣ ማንንም አያፍሩምም።
•••
ወዳጄ የሚሊሻህና የልዩ ኃይልህ፣ የተዋጊህም ብዛት ለጊዜው ለስም ለማስፈራሪያና ለመፎከሮያ ይጠቅምህ እንደሆን እንጂ ከእግዚአብሔር ቁጣና መቅሰፍትም በፍጹም አያድንህም። አያስመልጥህምም። በፍፁም አልኩህ።
•••
ደግሞም አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ አውሮጳም ስላለህ ከእግዚአብሔር ቁጣ ታመልጣለህ ማለት አይደለም። ብዙ የጦር መሣሪያ በታጠቀችው ትግራይ፣ በባለ ጊዜዋ ኦሮሚያም ስላለህም ከእግዚአብሔር ቁጣ ታመልጣለህ ማለትም አይደለም። እንዲያውም ከኮረና ቫይረስ ብታመልጥ ከአራጁ አህመዲን ጀበልና ከጃዋር መሐመድ ሰይፍ ላታመልጥ ትችላለህ። እነሱም እኮ ያው አደገኛ ቫይረስ እኮ ናቸው። አራስ ሽማግሌ የማይመርጡ። በአንድ ቀን 86 ሰው አርደው የሚያድሩ ቫይረሶች እኮ ናቸው። ዐቢይ አሕመድ እንዲያውም በአንድ ቀን 100 ሺ ሰው ሊታረድ ይችላል ብሎ ነው በአንደበቱ የተናገረው። የአቢይ ቫይረስ እንዲያውም ከሁሉ በላይ ያሰጋል። በሐረርጌ ታየ የሚባለው የገጀራ መዓት ከኮሮና ቫይረስም የከፋ እኮ ነው።
•••
እናም ወዳጄ ልቤ ከእግዚአብሔር ቁጣም ሆነ ከእነ ጃዋርጀበሎ ሰይፍ የምታመልጠው አካሄድህን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረግህ ብቻ ነው። ከቅዱሳን ወገንና ኅብረትም ከተቀላቀልክ ብቻ ነው። እንዲያ ካደረግህ አስፈሪውን የኤርትራን ባህር ከፍለህ ትሻገራለህ። ከእግዚአብሔር ጋር ከሆንክ በእሳት ውስጥ ብትጣልም እንደ ምርጥ የመናፈሻ ስፍራ ኮራ ጀነን ብለህ ትመላለስበታለህ። በአህያ መንጋጋ ሺውን ፍልስጤማዊ የማሸነፍ ኃይልንም ታገኛለህ። በተራቡ አናብስት ጉድጓድ ብትጣልም እንኳ አናብስቱን እንደ ለማዳ ውሻና ድመት እግርህ ስር አንከባልሎ ጫማህንና የእግርህን ትቢያ እንዲልሱ ያስደርግልሃል። በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋር መሆን የትኛውንም ዓይነት ፈተና አሸናፊ እንድትሆን ያደርግሃል።
•••
ይሄ ሁሉ መርግ በሀገርም በዓለምም ላይ ተጭኖ እያየህ አንተ ግን አሁንም ዙርባ ጫት ገዝተህ በግብረ አህዛብ ልማድ ጫትን እየቃምክ እየተቃምክ ነው። ሃሺሽ፣ ሲጋራ፣ ጥንባሆ፣ ሺሻና ጋንጃ እያጨስክ ትጦዛለህ። የካቲካላና የአምቡላ በርሜል ሆነህ ገንዘብህንም ጤናህንም ትጨርሳለህ። አሁንም የጋለሞታ ጭን ታሻሻለህ፣ እንደውሻ ባገኘህበት በዝሙት ትጋደማለህ። አሁንም ገና ብዙ ታልማለህ። ወዳጄ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣበረቆና ተዘጋጅቶ፣ ንስሐም ገብቶ፣ ሥጋወደሙም ተቀብሎ መጠበቅ ግን ሲበዛ ብልህነት ነው። ደጋግመን ተናገሩ የተባልነውን ተናግረናል።
•••
እምነት፣ ጠበል፣ አሁን ለሚያምንባቸው ሥራቸውን ይሠሩለታል። የኪዳን ጸሎት፣ ጸሎተ ቅዳሴና ሰዓታት ማኅሌቱ ፍቱን መድኃኒት የሚሆኑበት ዘመን መጥቷል። ገዳማት በህዝብና አህዛብ ይጨናነቃሉ። ሰማዕትነትም ከደጃችን ነው። ከንጉሡ በፊት አስቀድሞ የሚመጣው ካህን ወንበሩም አልጋውም ተዘጋጅቶለታል። ወደ ምሥራቅ እያየየን በተስፋ የምንጠብቀው ንጉሣችን መንገድ ጀምሯል። የደፈረሰው ሁሉ ይጠራል። ኢትዮጵያና ኦርቶዶክሳዊነትም ያሸንፋሉ። ድንፋታውን እርሱት። እኛም መምጫችን መመለሻ ጊዜያችንም ቅርብ ነው።
•••
ሻሎም !    ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥር 26/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic