>

እኛና እነሱ !! (ዘመድኩን በቀለ)

እኛና እነሱ !!

 

ዘመድኩን በቀለ
 
• የሟቾቹ የሰማዕታቱ ወጣቶች በረከታቸው ይደርብን። አሜን  !!  
 
• ሰማዕትነቱ ከሶማሌም ከከሚሴም አልፎ መሃል አዲስ አበባ ደርሷል። 
 
 በዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ዘመነ መንግሥት ኦርቶዶክስንና ዐማራን መሰባበሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል
•••
ይሄን የምጽፍላችሁ ወጣት ሚሊዮንና ወጣት ሚኪ ከተገደሉ በኋላ፣ ብልቱን በጥይት የበተኑበት ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ በሞትና በሕይወት መካከል ሆስፒታል ተኝቶ እያጣጣረ ነፍስ ውጪ፣ ነፍስ ግቢ እያለ ባለበት ሁኔታ፣ ከአስራ ስድስት በላይ የሆኑ የተዋሕዶ ልጆች በኦሮሚያ ፖሊስ በጥይት ቆስለው ሆስፒታል ተኝተው ባሉበት ሁኔታ፣ ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የተዋሕዶ ልጆች “ አላህ ወአክበር፥ ኢየሱስ ጌታ ነው ” በሚሉ ነፍሰበላ ወታደሮች እየተወገሩ ታፍሰው መታሰራቸውን ከሰማሁ በኋላ ነው።
•••
ያለፈው ሳምንት እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ የወሀቢ እስላሞቹ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በቀበሌ 01 በመኖሪያ ቤቶቹ መሃል ያለውን ክፍት ቦታ በአንድ ቀን ወርረው፣ ቦታውን አጥረው የማንንም ፈቃድ ሳይጠይቁ በግማሽ ቀን መስጊድ ሠርተው ጨረሱ። ለአገልግሎትም አበቁ።
•••
ፖሊስ መጣ፣ ሕገወጦቹ ወራሪዎች በኦሮሚኛ ስለሚያወሩ አከበራቸው። መስጊዱን ሠርተው እስኪጨርሱም የተጠናከረ ጥበቃ አደረገላቸው። ያውም ውኃና ምግብ እየቀረበለት። ሥራውን ሲጨርስ አላሁ ወአክበር እያሉ የታከለ ኡማ፣ የሽመልስ አብዲሳ፣ የለማ መገርሳ፣ ሠራዊት የኦሮሚያን ባንዲራ በመስጊዱ ግቢ ውስጥ ሰቅሎ እየጨፈረ በሰላም ወደቤቱ ሄደ።
•••
አባቴ ዛሬ በ22 አካባቢ ቤተ ክርስቲያን መተከሉን የዐቢይ መንግሥት የታከለ ኡማ አስተዳደር፣ የለማ መገርሳ ሠራዊት ሰማልሃ። ሰምቶመች ቀረ፣ በሶማሊያ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በሲዳማ፣ በአርሲ፣ በጅማ፣ በባሌ፣ ያደርግ እንደነበረው ተቆጣ፣ አበደ። እናም የተመረጡ የኦነግ ወታደሮችን በምሽት፣ በውድቅት ሌሊት ወደ ሥፍራው ላከ። ከዚያ ምን ይጠየቃል በመትረየስ አጨደዋ፣ አላሁ ወአክበር የሚል ወታደር ቤተ ክርስቲያኗን እሳት ለቀቀባት። የሚገድለውንም ገደለ።
•••
ካቻምና የለገጣፎዋ ከንቲባ ወሀቢስቷ ጫልቱ ሳኒ አዲስ አበባ አፍንጫህ ስር የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅን ቤተ ክርስቲያን አፍርሳ፣ ታቦቱን በመኪና ጭና፣ ንዋያተ ቅዱሳኑን በሽንት ቤት አጠገብ ስታስቀምጠው፣ አረጋዊውን ሊቀጳጳስ ደም እምባ ስታስለቅስ በዐይንህ አይተሃል። እናም ትናንት ለገጣፎ የነበረው አሁን ካዛንችስ ደርሶልሃል። አራት ኪሎ ቅድስተ ማርያም ብዙ ሩቅ አይደለም።
•••
በእጄ የሚገጀውን የሚዘገንን የሰማዕታቱን ምስል እንዳላወጣ ፌስቡክ ይከለክለኛል። በቴፒ ሚዛን ኦርቶዶክሳውያን እየታረዱ ነው። ከአንድ ቤት ሁለት ሦስት ሰው እየታረደ ነው። በቤንሻንጉል ዐማሮች እየታረዱ ኩላሊታቸው እየተበላ ነው። ቪድዮ ነው ያየሁት።
•••
የታከለ ኡማ አስተዳደር፣ የዐቢይ አህመድ መንግሥት፣ የለማ መገርሳ ሠራዊት የማይገድለው “ አላህ ወአክበር ” እያልክ መሬት ስትወር። መስጊድ ስትሠራ። አይነካህም። 200 ካሬ መሬት ውረር ይልህና 4000 ካሬ ይሰጥሃል። ኦቦሌሶ መስጊድ በግማሽ ቀን በፈለከው ቦታ ገንብተህ ከጨረስክ በኋላ የኦሮሚያን ባንዲራ መስቀል፣ ማውለብልብንም እንዳትረሱ።
•••
ጊዜው የኦሮሞ ወሀቢይ እስላሞች ስለሆነ ፖሊስ ሕገወጥነትን ያበረታታል። ይደግፋልም። ይጠብቃቸዋልም። ኦርቶዶክስ ከሆንክ የዐቢይ አህመድ መንግሥት ይበላሃል። የሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ይሰብርሃል። የለማ መገርሳ የኦነግ ሠራዊት አናት አናትህን ይበጠርቅህሃል።
•••
በአዲስ አበባ የአዲስ አበባን ልጆች ለመግደል የኦሮሚያ ወታደር በጭለማ ይላክብሃል። ወዳጄ ጊዜው የእነሱ ነው። መሞት የእኛ፣ መታሰር የእኛ፣ መታረድ የእኛ ዕጣ ፈንታችን እንዲሆን ከተፈረደብን ቆየ። ጊዜው የአራጆች ነው። ጊዜው ዐማራ በብሔሩ እና ኦርቶዶክስ የሆነ በሃይማኖቱ ምክንያት የሚታረድበት ዘመን ነው።
•••
አሁን በእኛ በኩል ሰብሳቢ የለንም። ሊቀጳጳስም የለንም። ማኅበራት የሉንም። እናም በሕጋዊ አግባብ የተደራጀ ሕጋዊ አካል የለንም። ሆዳም ይበዛዋል። የጥምቀት በዓል አሰማምሮ ወደ ቤቱ የሚመለስ እንጂ በቀጣይ ምን እንሥራ ብሎ በሕጋዊ መንገድ የተደራጀ ሕጋዊ አካል የለንም። ብንለፈልፍ፣ ብንለፈልፍም እንደ እብድ ከመቆጠር በቀር ሰሚ ስለሌለ የሚሆነውን ከመጠበቅ በቀር ምንም ማድረግ አይታሰብም።
•••
ወሀቢዮቹና ፕሮዎቹ ለጊዜው ጫጉላ ሽርሽር ላይ ናቸው። ሀገረ መንግሥቱ በእነሱ እጅ ነው። መስጊድ ወስጥ ቅስቀሳ፣ በአደባባይ ማርሻል አርት ስልጠና ከጀመሩ ቆይተዋል። ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ገጀራ በሀረር ከተማ መራገፉም ተሰምቷል። ሰማዕትነት በደጃችን እንደሆነ አስቀድሞም ተነግሯል። የእነ መምህር ምህረተ አብ የማንቂያ ደወል ወጣቱን እያነቃው መሆኑ ታይቷል። ቢያንስ ጳጳሳቱ ተኝተው ሰማዕትነትን የሚቀበሉ ወጣቶች ብቅ ብቅ ብለው ታይተዋል። ሰማዕትነቱ ይቀጥላል።
•••
ምስል 1፦ ክርስቲያኑ የፈረሰ መቅደሱና የልጆቹን አስከሬ ታቅፎ ያለቅሳል፤
ምስል 2፦  የወሀቢያ ሙስሊሞች በወርራ ባጠሩት መሬት ላይ መስጊዳቸውን ሰርተው ይጨፍራሉ
ሻሎም !     ሰላም !
ጥር 27/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic