>
12:38 pm - Sunday December 4, 2022

አይ ማጣራት ድንቄም  ማጣራት!!! (ግርማ ታደሰ)

አይ ማጣራት ድንቄም  ማጣራት!!!

 

ግርማ ታደሰ
ለአብይ የድጋፍ ሰልፍ ቦንብ ፈነዳ አጣርተን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን፣ ኢንጂነር ስመኘዉ በግፍ ተገደለ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተጣርቶ ህዝብ እንዲያዉቀዉ ይደረጋል፣ 20 ምናምን ባንክ ተዘረፈ ክትትል ይደረጋል ይጣራል፣ በቡራዩ ህዝብ ተጨፈጨፈ ወንጀለኞቹ ላይ ማጣራት ተደርጎ ለፍርድ ይቀርባሉ፣ ቤንሻንጉል በሰዎች ላይ አረመኔያዊ ድርጊት ተፈጸመባቸዉ በአስቸኳይ እንዲጣራ መመርያ ተላልፏል
በጋምቤላ ሰዎች በቀስት ተገደሉ እየተጣራ ነው የቅማንት ማንነት ኮሚቴ አማራዎችን ገደሉ ሐብት ንብረታቸዉን አወደሙ የፌደራል መንግስት ከክልሉ መንግስት ጋር በመሆን እያጣራ ነዉ፣ 
በከበቡሽ ምክንያት በኦሮምያ በተለያ ዞኖች ቤተ ክርስትያናት ጋዩ ክርስትያኖች በሜንጫ ተጨፈጨፉ በድንጋይ ተወገሩ አጣርተን ዉጤቱን በምድያ ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን
በድሬደዋ ሰዉ በቄሮ አለቀ አጥፊዎቹን በቁጥጥር ስር አዉለን እየተጣራ ነዉ
በጎንደር የጥምቀት በአልን ለማሸበር ሲሉ የፌዴራል እና የክልሉ የፀጥታ ሀይሎች አሸባሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉለናል በአፋጣኝ አጣርተን ዉጤቱን በሳምንት ዉስጥ ለህዝባችን እናሳዉቃለን፣
በቀደም ማክሰኞ ደግሞ በአዲስ አበባ በዉድቅት ለሊት ፖሊሶች ሁለት ኦርቶዶክሳዊያንን ገደሉ ትዕዛዝ እና መመርያ የሰጡትን አካላት ይዘን እናጣራለን እናጣራለን እናጣራለን እናጣራለን ዉይ እናጣራለን………….
… አስቲ መንግስትየ እባክህን ሌላ ቃል እንኳን ተጠቀም ዉሸቱን እንኳን ለምደነዋል።
Filed in: Amharic