>

ባለ ዘውድ ንጉሥ ይነግሳል! (ማህበረ ቅዱሳን)

ባለ ዘውድ ንጉሥ ይነግሳል! 

በዚያን ዘመን እንኳን ጠማማ ሰው ጠማማ እንጨት አይኖርም!!!
ማህበረ ቅዱሳን
√ እስከዚያ ግን ክፉ ጊዜ ፣ ከባድ ዘመን መከራ ሰማዕትነት ይኖራልና በተቃዋሚዎች አትደንግጡ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ ።
√ እንዲህ ባለ መከራ ጊዜ የበረኽኞች ገዳማውያን አበውን ትንቢት አስተውሉ:-
√ በዚያን ጊዜ የሚቆመው የአህዛብ መንግስት ለአለም መንግስታት ሳይቀር አስቸጋሪ ይሆናል
ለኢትዮጵያውያን ለመፍረድ እስከያስቸግራቸው ድረስ ምክንያቱም ሰላም ሳይኖረው ስለሰላም ያወራል ፣ ሰላማዊ ይመስላል ፣ እምነት የሌለው ጉንግማንጉግ ድሃ የሚበድል ፍርድ የሚያጓድል ይሆናልና።
√ ብዙዎች ሰማዕት ይሆናሉ በመሃል ሀገርም በዳር ሀገርም ፣ ነገር ግን ሞታቸው መስዋዕት መሆናቸው ልክ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ቅዱስ ቂርቆስ ፍጹም ሰማዕትነት ይቆጠርላቸዋል።
የበቁት ገዳማውያን አበው ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ ምን ትንቢት ተነበዩ
በ፲፪ ፲፪ ዓ.ም ጀርመን የሚገኘው ብራና መጽሐፍ ነፍሳቸውን ይማረው እና አለቃ ታምሩ በኢትዮጵያ ከሠሩት ታላቅ ሥራ አንዱ ፣ ትንቢት – ዘኢትዮጵያ በ፲፪ ፲፪ በግዕዝ የተፃፈውን ወደ አማርኛ በ፲፱ ፬፱ ዓ.ም ተርጉመው አሳትመውታል ::
፩ኛ )ጣሊያን የተባለ ወራሪ ተነስቶ ኢትዮጵያ ና ህዝቧን ሊወጋ ይነሳል ፣ በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስ በፈረስ ሆኖ አድዋ ላይ ይዋጋል።
እውን ሆኗል
፪ኛ) በቋራ አንበሳ ተነሳ ይልና የአፄ ቴድሮስን መምጣት ቀድሞ በትንቢቱ ተናግሯል ::
፫ኛ) ዘመነ ጎንደር እያለቀ ንግሥናው ወደ ሸዋ ሊመጣ ሲል ፋሲል ግቢ የሸረሪት ድር ያደራበታል ፣የቁራ ማደሪያም ይሆናል።
እውን ሆኗል ::
፬ኛ) ስለ ንጉሥ አጼ ኃይሌ ሥላሴ ደግሞ ፈረሳቸው ሳይቀር ይከዳቸዋል ይላል ::
፭ኛ) ልጅ ኢያሱን ያወሳል:-ኢያሱን ላለመካድ መኳንንቶች ተማምለው ነበር በኋላ ግን ኢያሱን ክደው የጣይቱን ወንድም ብጡለን ራስ ጉግሳን ገድለው በዛ የተነሳ መኳንንቱና እና ተፈሪ መኮንን ጥቁር ውሻ ይወልዳሉ ይላል ::
√የመግስቱ ኃይለማርያምን መምጣት ቀደም ብሎ ተነግሮአል:- ተኩላ ይመጣል ንጉሡን ይገድላል ሃይማኖት የለውም ጉግማንጉግ ሆኖ በክፉ ይበረታል።
በዚያን ዘመን ወላድ እናት ደረቷን ትመታለች ይላል፣ በቀይ ሽብርና በብሔራዊ ውትድርና ፣”ተኩላ ይመጣል ጠቦቶችን ይበላል” የተባለው ትቢንት ተፈፀመ::
√፮ኛ) ትንቢት ፳፯ ዓመት ስለገዙት ወያኔዎች ጉንዳን ከሰሜን ይመጣል የኢትዮጵያን መዓዛ ይመጣል፣ ይህ ጉንዳን እንደ ጢስ ተኖ እንደ አመድም ብን ብሎ ይጠፋል ብዙዎቹም ጉንዳኖች ያግዛሉ ያጋግዛሉ ነገር ግን ሀብታቸውን እንኳን የትም ይዘው ለመሄድ እድሉን አያገኙም :: ወየው የሚሉበት ጊዜ ይመጣል። ከዚያ በኋላ ተመልሰው ለመምጣት ብዙ ይጥራሉ መከራም ያደርሳሉ ግን አይመለሱም። ከሰሜን መረብ ከተሻገሩ በኋላ ዝም በሏቸው አባይን ተከዜን ከተሻገሩ በኋላ እርስ በእርሳቸው ይተላለቃሉ።
√ኤርትራውያንም ኢትዮጵያ ውስጥ እህል ውሃ አላቸው :: በዚያን ዘመን ደግ የሠሩ ሠዎች ምነው ብለው እስኪፀፀቱ ድረስ ፍዳቸውን ይቀበላሉ ::
√ ትንቢት ከጉንዳኖች (ወያኔዎች) ውድቀት በኋላ እሳት ይመጣል፣ በዚያን ጊዜ የአህዛብ ንጉሥ ይነግሣል ለቤተክርስቲያን እና ለክርስቲያኖችም መልካም ያልሆነ ጌዜ ይሆናል !! ብዙዎች ድንገት እንደ ወጡ ይቀራሉ ፣ ፍትህን አያገኙም።
√ በዚያን ዘመን አብዛኛዎች በዳር ሀገር ያሉ ክርስቲያኖች መከራ ያገኛቸዋል ደም ይፈሳል ሠማዕትነትን ይቀበላሉ ትልቅ ክብር ያገኛሉ ።ከሠማዕትነት ይቆጠርላቸዋል ብዙዎች ወጣቶችም ይህንን ክብር ይቋደሳሉ !!
√ እንደ ቅዱስ መርቆሪዎስ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሠማዕትነት ይቆጠርላቸዋል ::
√ የኑሮ ውድነት ርሃብ ቸነፈር የከፋ ይሆናል ::የኤድስ በሽታም የሚመሰገንበት ጊዜ ይመጣል ::ምክንያቱም የኤድስ በሽታ ለንስሃ ጊዜ ይሰጣል ከዚያ በኋላ የሚመጣው መቅሰፍት ድንገተኛ ነው ። ለንሰሃ ጊዜ
የማይሰጥ አጣድፎ የሚገል በሽታ ሳይሆን አይቀርም ::
√ የሚቆመው የአህዛብ መግስት ለዓለም መግስታት ያስቸገረ ይሆናል :: ሰላም ሳይኖር ስለ ሰላም የሚያወራ ፍርድ የሚያጓድል ደሃ የሚበድል ፍቅር ሳይኖር ስለ ፍቅር የሚሰብክ አንደበተ ለስላሳ የውጭ አልጋ የቤት ቀጋ የሆነ ይሆናል። ነገር ግን ስለ ተመረጡት ቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ዕድሜው አጭር ይሆናል ::

ትንቢት ስለ ንጉሥ ቴዎድሮስ:-

=
ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር ደገኛ ንጉሥ ይነግሣል።
ኢትዮጵያ ን በዘንግና በነጭ መነሳንስ አርባ ዘመን(ዓመት) የሚገዛ ንጉሥ (ቴዎድሮስ ይሉታል )ይነግሣል ።
የሚነሳውም ከምስራቅ ኢትዮጵያ ከኤረር ተራራ እንደሆነ ይነገራል። በእርሱ ዘመን ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል ።
በዚያን ዘመን የአንድ ላም ወተት የአንድ በሬ ጉልበት በቂ ነው ፤ አህያና ጅብ በአንድ ላይ ይውላሉ በአንድ ላይ ያድራሉ።
አንድ እንጀራ ለአገር ሰው ያጠግባል ፤ በእርሱ ዘመን እንኳን የሰው የእንጨት ጠማማ አይኖርም።
በዚያን ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት ይሰፋል ኤርትራም ወደ እናት ሀገሯ ትመለሳለች ፍቅር እና አንድነት ይሆናል ። ኢትዮጵያ እጅግ ታላቅ ሀገር ትሆናለች ። በእርሱ ዘመን የሚነሱት ፖትሪያክ እጅግ የበቁ እና ገቢረ ተአምር የሚያደርጉ ይሆናሉ።በዚህ ሰው ንግሥና ዘመን በኢትዮጵያ ፍፁም ሠላም ይሆናል በሀገሪቱም በረከት ይሆናል ከሌላው ሀገር ተለይታም የጥጋብ እና የበረከት ሀገር ትሆናለች ።
√ የበርካታ ሀገር ስደተኞችንም የምታስተናግድ የስደተኞች መጠለያ እና ማረፊያ ትሆናለች ።
√ለዘመናት ደም ሲቃቡ የነበሩት ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያዊንም አንድ ይሆናሉ። ሁለቱም ወንድማማች ህዝብ ወንድማማችነታቸውን አድሰው በሰላም በፍቅር ይኖራሉ ። በዚያን ዘመን የሚሾሙት ፖትሪያክ ህዝቡን ከአምላኩ ከእግዚአብሔር የሚያስታርቁ ሀገርን የሚጠብቁ ተአምር የማድረግ ፀጋ የተሰጣቸው ትልቅ አባት ናቸው።
አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ ሆይ ይህን ዘመን አሳየን ::
Filed in: Amharic