የኬኒያው ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንዲያቆም አሳሰቡ!!!
ውብሸት ታዬ
* ኮሮና ቫይረስ ግስጋሴ ማሻቀቡን ቀጥሏል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮሮና ቫይረስ በተስፋፋበት
ወቅት ወደ ቻይና ጉዞ ማድረጉ ተገቢ እንዳልሆነ የኬኒያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬኒያታ ተናገሩ፡፡ አየር መንገዱ በዚህ ወቅት ወደ ቻይና መብረሩ ቫይረሱ አፍሪካን ወደ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል
ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ኬኒያታ‹‹ ጭንቀታችን ቻይና ቫይረሱን ትቆጣጠረዋለች የሚለው ሳይሆን የሚያሳስበን ደካማ የጤና ሥርዓት ባለን አገራት ውስጥ እንዳይገባ ነው›› ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በሚያደርገው የቀጥታ በረራ አምስት መዳረሻዎች ሲኖሩት ፤ ወደ ቤጂንግ፣ ሻንጋይ፣ ጉዋንዙ፣ ቼንጉዱ እና ሆንግ ኮንግ በረራዎቹን ማድረጉ ቫይረሱ ወደ አህጉሪቱ እንዳይገባ ስጋት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡አየር
መንገዱ አሁንም ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ አላቋረጠም፡፡
ትላንት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ተወልደ ገብረ ማርያም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ወደ ቻይና በረራ ማቆም ዋስትና አይሰጥም ብለዋል፡፡ባሳለፍነው
ሳምንት ኬኒያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ማቋረጣቸውም የሚታወስ ነው፡፡
ኮሮና ቫይረስ ግስጋሴ ማሻቀቡን ቀጥሏል!!
በአንድ ቀን ብቻ በቫይረሱ የተያዙት ቁጥር፦
ከ28,273 ወደ 31,481 ጨምሯል
የሞቱት ሰዎች ቁጥር፦
ከ565 ወደ 638 ጨምሯል
በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት ቁጥር
ከ3,859 ወደ 4,824 ጨምሯል
በቫይረሱ የተጠቁት አገራት ቁጥር፦
ከ25 ወደ 28 ጨምሯል
የቫይረሱ ሕመም ምልክት የሚያሳየው ከሁለት ሳምንት በኋላ በመሆኑና በሽታው ከተከሰተበት አገር የሚመጡ ተጠቂዎችን በአየር መንገዶች ለሁለት ሳምንታት እያቆዩ ማረጋገጥ የሚቻልበት መንገድ ስለሌለ ለዜጎቻቸው የሚያስቡ አገራት ወደ ቻይናም ሆነ ከቻይና የሚደረጉ በረራዎችን አግደዋል።
•የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዜጎቹን ሕይወት አስይዞ ለቻይና ያለውን ቁርጠኛ አጋርነት ማሳየቱን ቀጥሎበታል።
•የመከነ መከራከሪያ የሚያቀርቡ ግለሰቦች የአየር መንገዱን አቋም ለመደገፍ አንድም #የአፍሪካ አገር በረራ አላቆመም እያሉ ይሳለቃሉ !
•ቫይረሱ በአንድ ጊዜ ከአንድ ሰው ወደ አራት ሰው የመተላለፍ ፍጥነት አለው።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ !