>

እውነተኛው የትግል  እርሾ የተጣለው "  ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ!" ሲመሰረት ነው!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

እውነተኛው የትግል  እርሾ የተጣለው ”  ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ!” ሲመሰረት ነው!!!

 

አቻምየለህ ታምሩ

 

ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደር ላይ ከለኮሰው የአማራ ተጋድሎ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ  እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት እውነተኛው የትግል  እርሾ የተጣለው ዛሬ  ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ሲመሰረት ነው። የተቀረው  ሁሉ የተነሳበትን አላማ ረስቶ ወደ ጎጡ በመውረድ ሲገድሉን ለኖሩት የወያኔ እንደራሴዎች ውግንና በመቆም ሲተራመስና ልፊያ ሲያደርግ የሚውል እንጂ መርህ ያለው ትግል ውስጥ የለበትም። የኦሮሞ ብሔርተኞች ሁሉ የአዲስ አበባን ሕዝብ እንደ ጠላት የሚቆጥሩ፤ ሲገድሉትም ወገናቸውን እንደጎዱ  ሳይሆን  ኢትዮጵያውያን ፋሽስትና በተለያዩ ጊዜያት የወረሩንን የውጭ ኃይሎች አጥፍተን እንደሚሰማን አይነት ደስታ የሚሰማቸው፣ ወራሪ ጠላት ያጠፉ ያህል ነፍሳቸው ሀሴት የምታደርግ  ነፍሰ በላዎች ናቸው። ከእነዚህ የአዲስ አበባን ሕዝብ እንደ ወራሪ ጠላት ከሚቆጥሩና የአዲስ አበባን ሕዝብ አጥፍተው ከተማውን  ለመቀራመት ቀመር አውጥተው፤ የሚያጠቃ ኃይል አሰልጥነው ከሚጠባበቁ  አረመኔዎች መንጋጋ ለመላቀቅ ብቸኛው መንገድ አዲስ አበባን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ መዲና ለማድረግ የተቋቋመውን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ተቀላቅሎ የሚችሉትን ያህል አስተዋጽኦ ማድረግ ብቻ ነው።  ባልደራሶች  የትግላችሁን  የመጀመሪያ ፍሬ በማየታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ድል ለዲሞክራሲ!

Filed in: Amharic