>
4:53 pm - Monday May 25, 1181

ነፃነት በላብና በደም እንጂ በልመና አይገኝም! (ቴዎድሮስ ሀይለማርያም)

ነፃነት በላብና በደም እንጂ በልመና አይገኝም! 

   ቴዎድሮስ ሀይለማርያም
        የአማራ ህዝብ ላለፉት 29 ዓመታት የደረሰበት ግልፅ መንግሥታዊና መዋቅራዊ ጥቃት  ህልውናውን ቢፈታተነውም ፣ እስከዛሬ  በጊዜያዊ መፍትሄዎች እያስታገሰ ቆይቷል። ይህ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ጠላቶቹን እያበረታ ፣ ወዳጆቹን ተስፋ እያስቆረጠና ወገን  እያስለወጠ እዚህ አድርሶናል። አሁን በምንገኝበት ወሳኝ የታሪክ መስቀልያ ላይ ከወያኔ ያልተናነሰ እየደረሰብን ነው። ምን እናድርግ?
—-
    1: አጎብዳጅነትን እንጠየፍ !
      አጎብዳጅነት የንፍር ውሃ ቢወርድብን በፀጥታ  ተቀብለን ፣ ተዋርደን ወርደን እንኑር የሚል ጠላት ተከል መርህ ነው። አንዳች መስዋእትነት የማይሻ ፣ ከአማራ ተፈጥሮ የተጣላ ስልት ነው።  እጅግ አፀያፊ ነው።
     አጎብዳጅነት ለ29 ዓመታት በተለያዩ ካባዎች ተጀቡኖ ቀርቧል። ፈሪ/አስፈራሪ ከክልሉ ውጭ ያለው አማራ ያልቃል ፣  የሰኔ 15ቱ እልቂት ይደገማል ይለናል።  “ቅቤ አንጓች”  ሰባት ጊዜ ሰባ ሰባት ካልተጠፈጠፍን   “አማራ ከከፍታው ይወርዳል” ወይም   “ክልላችን የሰላም ማእከል በመሆን ያገኘውን የኤኮኖሚ ተጠቃሚነት ያጣል” የሚል  ጭንብል ይዞ ይመጣል።
     በአማራ ብሂል  የጅል ተምሳሌት የሆነው የ”ዝምበሉ እግሬን ይብላኝ” (hash hash)  መርህ  በዘመናችን  እንደ ብልህነት ሲቀርብ ያሳፍራል። ለአጎብዳጅነት  የጉማሬው  ትክለኛ ድርጅት ጀርባ በቂ ነው።  ክርንህን ላስ እንበለው!
    2: ምሽጋችንን እናጠናክር !
     አሁን የአማራ ብሄርተኝነት በራስ መከላከል ትግል ላይ ይገኛል።  መከላከል በተቻለ መጠን የሚደርስብንን  አደጋ የመቀነስና ከቁጥጥር እንዳይወጣ የመጣጣር ስልት ነው። ሀገር በእብድ ዘረኞች ጥፍር ባትወድቅ ኖሮ  ለሁላችንም አዋጭ የሆነ አመዛዛኝ   አመክንዮ አለው።
     መከላከል ለአማራ ህዝብ ፣ አልፎም ለሀገራቸው ለኢትዮጵያ የሚቆረቆሩ ቡድኖች የተሰለፉበት አማካይ መስመር ነው። እውነት ነው ካበደው ማበድ ፣ ካረደው ማረድ የለብንም። ትእግስትና ፍቅር በብዛት ያስፈልገናል። ነገር ግን ስልታችን በእኛ ፍላጎት ብቻ አይወሰንም።
    ግራችንን ከመቱን ቀኛችንን እንዳይደግሙን እንጠብቅ የሚለው  መስመር ከጠላት በሚሰነዘር  ጥቃት ላይ በመመስረቱ ከእሳት አጥፊነት  ተራምዶ ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ  አይችልም። ስለዚህ አስፈላጊ መሸጋገሪያ  እንጂ በቂ የመታገያ  ስልት አይደለም። ለማይቀረው ፍልሚያ እንዘጋጅ!
     3: የጠላትን ምሽግ እንስበር! 
     አሁን የአማራው ህዝብ የራሱንም የሀገሩንም አጣፈንታ ለመወሰን ከእርድ የወጣ መልሶ ማጥቃት የግድ ይለዋል።   የማህበረሰባችንንና የሀገራችንን ጠላቶች በሁሉም መስክ በቆራጥነት ፣ ያለይሉኝታና ያለርህራሄ መፋለም አለብን።
    አጥቂነት “offence is the best defence”  የሚል  ጊዜው የደረሰ ስልት ነው። ፍልሚያው ወደጠላቶቻችን ወረዳ መዝለቅ ፣ የጫሩት እሳት መፋጀቱን ማሳየት አለበት። ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎትና  ኪሳራ አይገኝም። በሁለት ወገን ኪሳራ ቢያንስ ትምህርት ይገኛል።
     አጥቂነት   ገና በቅጡ ያልያዝነው አቋም ይሁን እንጂ ለአማራው ህዝብ በዘላቂነት እንደሚበጅ አያጠራጥርም።  ከሁሉም በላይ አማራው ሲቆርጥ የሚያሳየው ተፈጥሯዊ  የፍልሚያ ባህሪው   ስለሆነ ጠላቶቹን ያንዘፈዝፋቸዋል።  ስለዚህ ወገን  ትመርር እንደሆን ምረር እንደ ቅል !!
Filed in: Amharic