>
5:13 pm - Monday April 19, 8849

ሰውዬአችን ዓላማና ግቡ ፈፅሞ ግልፅ አይደለም- እንኳን ለእኛ ለራሱም!!! (ሰይፍአርድ አደጽዮን)

ሰውዬአችን ዓላማና ግቡ ፈፅሞ ግልፅ አይደለም!..እንኳን ለእኛ ለራሱም!

ሰይፍአርድ አደጽዮን
 
* ከልምድ እንዳየነው ሰውዬው ከዲስኩር በዘለለ በተለይም በአማርኛ የሚናገረውን ለማመን እጅግ የሚከብድ ነው!!
 
* የሚለውን ስለማድረጉ ወይም የሚናገረውን ስለመሆኑ ፈፅሞ ለማመን የሚቻል አይደለም!
 
* እዚጋ መልካም ሰራ ብለህ ስታደንቅ እዛጋ ክብሩን ያረክሳል!
 
* እዛጋ ሰበሰበ ስትል አጠገብህ መጥቶ ሲበትን ሲዝረከረክ ታየዋለህ!
 
* እዚጋ ሀቅና መልካም ተናገረ ስትል እዛጋ ሲቀባዥር ታየዋለህ!
 
* እዚጋ ህዝብን አንድ የሚያደርግ ነገር ሰራ ስትል እዘጋ ሔዶ ሰብረነዋል: አጥረነዋል: እኛ ካልፈቀድን እያለ ሲዘላብድ ለእሱ ታፍራለህ!
* እዚጋ የዩኒቨርስቲ ተማሪ በዘር አማራ በመሆናቸው ብቻ በሱ ነገድ ሲጠለፉ ከማንም በላይ በሽቆ የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ፍትሐዊነቱን ማሳየት ሲገባው ፓርላማ ላይ ቀርቦ ሲክድ ሲያምን ሲያስተባብል በአንድ እራስ ሁለት ምላስ ሆኖ ታገኘዋለህ:: ስለከበረ የሰው ልጅ ያውም የእናትና አባት ፍቅር ያልጠገቡ እድሜያቸው ከ19-21 አመት የሆኑ ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በራሱ ነገድ ተረኛ እና እብሪተኛ ወንበዴ መታገት እና የግፍ ሰለባ ስለመሆን ሲጠየቅ ስለአበባ መቀጠፍና የፀጥታ ሀይሉን በቤተመንግስት ሰብስቦ እራት እያበላ ውሃ ከ50 ጊዜ በላይ ስለማጠጣቱ ይደሰኩራል!
* ሰውዬው እጅግ ድብልቅ አንዴ ጭልጥ ያለ ኢትዮጵያዊ ነው ስትለው ተከርብቶ ግልፅ ዘረኛ እና የዘር እርካብ ናፋቂ ሆኖ የሰበሰበውን ህዝብ ሲበትን ታገኘዋለህ!
* ሰውዬው አሜሪካ ድረስ ሄዶ አንድ አድርጎ ወደሀገር ቤት በክብር ሰብስቦ ያስገባውን ሲኖዲዮስ ሀገር ቤት የሊቀሰይጣን ወያኔ የህይወት ዘመን አሽከር: የቤተክርስቲያን የቋንጃ እከክ የሆነው: የቤተክህነቱን አባቶች እና ኃይማኖታዊ ተቋሙን ሲሰልል እና ሲያደማ የኖረውን መስቀል ያዥ ካድሬ አይተ በላይን እረፍ ወይም አርፈህ ተቀመጥ የተዋህዶ ወገኖቼን አታሳዝን ህዝቤን አትከፋፍል ማለት ሲገባው የዛሬውን ኦቦ ካድሬ በላይ የተባለ ሰርጎገብ ወንበዴ ተጠቅሞ የዘመኑን የቤተክርስቲያን ችፍርግ ፈይሳ አዱኛ (ፈዋሽ ሀብት) እያለ ህዝበክርስቲያኑን በዘር ለመከፋፈልና ለመበተን ሲፍጨረጨር የሰው ህይወት ካስጠፋው: ከወንበዴው እና ከፀረ ኢትዮጵያዊዉ ጀዋር እና ጀዋራዊያን ጋር ቂጡን ገጥሞ በጠራራ ፀሀይ ህዝብን ሲያምስ አረንጏዴ መብራቱን ወደቀይ መብራት ሲቀይርበትና ስርዓት ሲያሲዝ አላየነውም!
* ለእናቴ ያለኝ ፍቅር ለሴት ያለኝ ክብር ከአለም አንደኛ ነው 50% ስልጣን ለሴቶች አካፈልኩ ይልህና 21 የአማራ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በራሱ ጎሳ ተጠልፈው ወላጆች ዓለም እያየ ሲያነቡ እሱ ሲያስመስል ወይም ንጉሱ ጥላሁን የተባለውን አፈቀላጤና አጋፋሪውን ተጠቅሞ ቲያትር ሲሰራ ወይም ሲክድ ወይም ስለአበባ መቀጠፍ ወይም መሰረቅ ደጋግሞ ሲዘባርቅ እጅከፍንጅ ትይዘዋለህ!
* ሰውዬው ዓላማና ግቡ ፈፅሞ ግልፅ አይደለም!
 የሚለውን ስለማድረጉ ወይም የሚናገረውን ስለመሆኑ ፈፅሞ ለማመን የሚቻል አይደለም!
* ለሰውዬው ሳይሆን የማዝነው እራሳቸውን የእሱ ፓሮት ላደረጉ በቀቀን ሀይሎች ነው:: ምክንያቱም እነሱ እዚህጋ ሲያደንቁ እሱ እዘጋ በዕጁ ያልተገባ ነገር ሲነካ ወይም በንግግሩ ዘባርቆ ታሪካዊ ስህተት ሰርቶ ያሳያቸዋል:: ያኔ አንተ ፊትህን ወደበቀቀኖቹ ስታዞር አንገታቸውን እንደ ሰአት ሰሪ በሀፍረት ሲደፉ እና መደበቂያ ሲያጡ ለዕሱ ሳይሆን ለበቀቀኖቹ ታፍራለህ!!
<> ይኼው ነው መናገርና መሆን ይለያያል!!!
Filed in: Amharic