>

“ነውረኛው ሐውልት!”(አቻምየለህ ታምሩ)

“ነውረኛው ሐውልት!”

 

አቻምየለህ ታምሩ

 

የምትመለከቱት ሐውልት የየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ለተሰውት ሰማዕታት እና በሀገር ፍቅር ስሜት ለተቃጠሉ አርበኞች መታሰቢያ የቆመ ሐውልት እንዳይመስላችሁ። ሐውልቱ የአማራው ጉድ ብአዴን ባሕር ዳር ቀበሌ 11 ባስገነባው እና «የሰማዕታት ሐውልት» ብሎ በሚጠራው ቅጥር ግቢ ውስጥ አቁሞት የሚገኝው በሀገር ፍቅር ስሜት የተቃጠሉ ነፍጠኞችን በትግሉ አንገታቸውን ማስደፋቱን ለማሳየት ያቆመው ነውረኛ ሐውልት ነው። ጥንት ድርብ ካባ ለብሶ፣ ነፍጡን አዘቅዝቆና አንገቱን ደፍቶ በሐውልቱ ላይ የምታዩት ሰው ወያኔዎች በትግላቸው ነፍጡን እንዲዘቀዝቅ፣ አንገቱን እንዲደፋ አድርገን አከርካሪውን በመስበር ትክሻውን ለእስክስታ ብቻ አስቀርተን ገድለን ቀብረነዋል ብለው ያሉትን ነፍጠኛን ወይም በነሱ እሳቤ አማራን የሚወክል ነው። የሕወሓት እንደራሴው ብአዴን ያካሄደውን ትግል የሚወክለው ይህ ሐውልት፤ ነውረኛው ድርጅት አማራን ነፍጡን እና አንገቱን ወደ መሬት አስደፍቶ ነፍጡን ከናስዘቀዘቀበት ነውረኛ ሐውልቱ ተነቃቅሎ እስካልተጣለ ድረስ የአዲሶቹን ጌቶቹን ፍላጎት ያለገደብ ለማስፈጸም ሲላላክ ያምናዎቹን ጌቶቹን ሲያገለግል ነፍጡን እና አንገቱን ወደ መሬት አስደፍቶ ሐውልት ያቆመለትን አማራ አንገቱንም ነፍጡንም ቀና ለማድረግ በሚታገሉ ልጆቹ ላይ ዘንድሮም የማይፈጽመው ጥቃት የለም።

Filed in: Amharic