>

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ……… !! (ይድነቃቸው ከበደ)

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ……… !!

ይድነቃቸው ከበደ
☞ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን፣
☞ አባ ገብረ ማርያም፣
☞”ዲያቆን” ኃይለ ሚካኤል ታደሰ
☞ቄስ በዳሳ ቶላ
፩) ከዚህ በኋላ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን አይፈጽሙም። ቀድሰው አያቆርቡም፣ መስቀል አያሳልሙም፣ አይባርኩም፣ ንስሐ አይሰጡም፣ አይናዝዙም።
፪) በስመ ማእረጉ አይጠሩበትም። ሁሉም ማእረገ ሥልጣናቸው በመያዙ ሁሉም “አቶ” ሆነው ይቆያሉ።
፫) የክህነት ምልክቶችን አይጠቀሙም። የመባረኪያ መስቀል አይዙም። የስብከተ ወንጌል ቀሚስ አይለብሱም።
☞ ከዚህ ውሳኔ ተላልፈው ቢገኙ ግን ቅጣቱ ወደውግዘት ከፍ ይላል። ቅጣታቸው ወደ ውግዘት ከፍ ካለ ደግሞ የሚያዝባቸው ሥልጣነ ክህነታቸው ብቻ ሳይሆን ከምእመናን አንድነት እና ከቤተክርስቲያን ኅብረትም ይለያሉ።
☞ ከውግዘት በፊት ተመክረው እና ወደልቡናቸው ተመልሰው ለጥፋታቸው ይቅርታ ጠይቀው የበደሏትን ቤተክርስቲያን ክሰው ለመመለስ ፈቃደኛ ከሆኑ ግን የተያዘው ሥልጣነ ክህነታቸው ይመለስላቸዋል። እስከዚያው ግን ከምእመናን እንደ አንዱ ሆነው “አቶ” ሆነው ይቆያሉ።
ከየካቲት 11 ቀን ጀምሮ በጥፋታቸው ተጸጽተው ከተግባራቸው በይቅርታ እስኪመለሱ ድረስ ሥልጣነ ክህነታቸው እንዲያዝ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ልዩነት በሌለው ሙሉ ድምፅ ወስኗል፤ (በስብሰባው ለኃይለሚካኤል ዲቁና “እኔ ነኝ የሰጠሁት” የሚል ጳጳስ አልተገኘም)
Filed in: Amharic