>
5:13 pm - Tuesday April 18, 6389

አቤቱታ... ለጠ/ሚ/ዶኮ ዐቢይ አሕመድና  ለምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ዑማ  (ዘመድኩን በቀለ)

አቤቱታ… ለጠ/ሚ/ዶኮ ዐቢይ አሕመድና 

ለምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ዑማ 

 

            ዘመድኩን በቀለ
 ~ ጉዳዩ ፦ 
 
ሀ፥  የታሠሩ አባቶቻችን ትፈቱ ዘንድ 
ለ፥  ደማችን በፈሰሰበት ቦታ ቤተ መቅደሳችንን  እንሠራ እናንጽ ዘንድ ስለመጠየቅ 
•••
ክቡራን ሆይ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት ናት ብዬ ለእናንተ ላስረዳ ብዬ መቼም መከራዬን አላይም። 2ሺኛውን ዘመን አልፋ ሦስተኛውን ሺ ዘመን የጀመረች አረጋዊት ቤተ ክርስቲያን ናትም ብዬ አልነግራችሁም። ቤተ ክርስቲያኒቱ በየዘመናቱ በሚነሱ አላውያን፣ ከሃድያንና አረመኔዎች አማካኝነት ፍዳዋን ስታይ የኖረች መከራም የዕለት ምግቧ የሆነች ቤተ ክርስቲያን መሆናንም ታውቃላችሁ። በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአክሱም ካህናት ስህተት በዮዲት ጉዲት እሳት የተለበለበች፣ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ በግራኝ አህመድ ሰይፍ የታረደች፣ ጣልያንም፣ ደርቡሽም፣ ቱርክም ቢመጡ የሚያወድሟት እሷኑ መሆኑን ወይ አንብባችኋል ወይ ሲወራ ሰምታችኋል። በሀገር በቀሎቹ ደርግና ወያኔ ህወሓትና ኦነግም ጭምር በብዙ እንደተፈታተናት ታሪክ ምስክር ነው።
•••
አሁን ደግሞ ጭራሽ በእናንተ በጎረምሶቹ ጀማሪ ጴንጤዎች የሥልጣን ዘመን ይባስ ብሎ ልክ እንደ ውጭ ወራሪ ጠላት አክት እያደረጋችሁ ቤተ ክርስቲያንንና ምእመናኖቿን ማረድ፣ ማቃጠልን እንጀራችሁ እስኪመስል ድረስ እንደሥራ ቆጥራችሁ ተያይዛችሁታል። ይሄ አያዋጣም። እነ ግራኝ እንደ ወደሙት ትወድማላችሁ፣ እነ ዮዲት ጉዲት እንደጠፉት ትጠፋላችሁ፣ እነ ፋሽስት ኢጣልያ እሬቻቸውን እንደበሉት እሬቻችሁን ትበላላችሁ። እናም ቆም ብላችሁ አስቡ። ከዐለት ጋርም አትጋጩ። አያዋጣችሁም። አያዛልቃችሁምም።
•••
እኔ ዛሬ በትህትና እንደሌላው ጊዜ ይሄን ቂጣ የቀደደውን ክፍት አፌን ሳልከፍት ( በርገር ስለማልወድ ነው) የሐረሮችን የአነጋገር ዘይቤም፣ ጠባይና ልማድም ሳልከተል እንዲያው በጠባይ በጨዋ ደንብ እለምናችኋለሁ፣ እጠይቃችሁማለሁ። ጥያቄዬን ደጋግማችሁ አስቡበት። ከምር እውነቴን አስቡበት።
•••
ይኸውም ጥያቄዬ ምንድነው በአዲስ አበባ ከተማ፣ በ22 ሰፈር፣ በ24 ቀበሌ የመንግሥታችሁ ወታደሮችና የቦሌ ክፍለከተማ ያ ጨካኝ የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራራችሁ በሰጠው ትእዛዝ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የተፈጸመውን መቼም ታስታውሳላችሁ። እንዲህ በቀላሉ የሚረሳም ተነግሮም የሚያልቅ አይደለም። “አላህ ወአክበር፣ ኢየሱስ ጌታ ነው” እያሉ እየፎከሩ በፀረ ተዋሕዶ የሰከሩ የወሃቢይ እስላም ወታደሮችና የአክራሪ ጴንጤ ወታደሮችን ልካችሁ ያደረጋችሁትን ታውቃላችሁ።
•••
ያ እንደሌባ በሌሊት የላካችሁት ወታደር ቤተ ክርስቲያን አፍርሶ፣ ታቦት ጽላቱን ወስዶ፣ ህፃን፣ ሽማግሌ፣ ሴት፣ አረጋዊ ሳይል ቀጥቅጦ፣ አቁስሎ፣ ሁለቱንም ወጣቶች ገድሎ አርዶና ደማቸውን አፍስሶ እንዲሄድ አድርጋችኋል። ይሄም ተመዝግቧል። አድሎዊ ስለሆናችሁ ለእስላሞቹ 9000 ካሬ መሬት ኃይሌ ጋርመንት ጋር በጉልበት በፖሊስ ታጅበው ሲወስዱ ዝም ብላችሁ የእኛ ጊዜ ሲሆን እንደ ግራኝ፣ እንደ ጣሊያን አደረጋችሁ አረዳችሁን።
•••
አሁን በዚህ ጉዳይ ብዙ ተብሏል። ቅዱስ ሲኖዶስም መግለጫ አውጥቷል። ተሰብስበው አበው አረጋውያኑ አልቅሰዋል። አዝነውባችኋልም። ኦርቶዶክስ ሀገር ናት። ለዚህች ሀገር ለሆነች ቤተ ክርስቲያን ኩርማን መሬት ልትለምን አይገባትም። እናም ደም የፈሰሰበት ቦታ ነውና ይሄን ቦታ በአስቸኳይ ስጡን። ቤተ መቅደስ እንሥራበት፣ እንጸልይበት። እንደንስ፣ እንጨፍር አላልንም። እንጸልይበት።
•••
በዚህ ሰበብ የታሰሩትን አባቶችም በአስቸኳይ ፍቱልን። በሕጋዊ መንገድ የተንቀሳቀሱ አባቶችንና ምእመናንን ማሰር አግባብ አይደለምና ፍቱ። ልክ ዛሬ እንደፈታችኋቸው ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን አባቶቻችንንም በቶሎ ፍቱ። ፍቱልን።
•••
አይዋል፣ አይደር። በዓረቡ ዓለም፣ በአፍሪካ፣ በአውሮጳና በአሜሪካን መሬት በነፃ የሚሰጣት ቤተ ክርስቲያን በገዛ ምድሯ ላይ ታከለ ኡማና ዐቢይ አህመድ የተባሉ ጩጬዎችን ልትለምን፣ ልትለማመጥም አይገባትም። ዛሬ የምትመሩትን ሀገርና ከተማ ዕጣን እያጠነች፣ ትምህርት ሚኒስቴር ሆና እውቀት እየመገበች ያቆየችላችሁ ቤተ ክርስቲያን ናት እኮ። ዛሬ ጴንጤ ብትሆኑም መሠረታችሁን አትርሱ እንጂ።
•••
ከወጠጤው ዮናታን ጋርም አታወዳድሯት። ከአጭበርባሪዎቹ፣ ዪዲዲያ፣ ዳንሳና ጩፋ ጋርም አታወዳድሯት። ሞተው ቢነሱ፣ ቢጨፈለቁ እንደገና ቢሠሩ እንኳ እነሱ እሷን አይደለም መሆን መምሰልም አይችሉም። እደግመዋለሁ። ኦርቶዶክስ ሀገር ናት። ሀገር አትናቁ፣ ሀገር አታፍርሱ፣ ሀገር አትግደሉ። ግድየላችሁም ኦርቶዶክስን አትግፉ።
•••
ዐቢይ አህመድ አንተም ብትሆን በእናትህ ኦርቶዶክስ ነህ። በሚስትህም ዛሬ ጴንጤ ብትሆንም ኦርቶዶክስ ነህ። ታከለ ኡማ ዛሬ ጴንጤ መሆንህን አትይ። በወላጆችህ ኦርቶዶክስ ነህ። ሽመልስ አብዲሳ፣ አዲሱ አረጋ የዛሬን አትዩ። ለማ መገርሳ ዛሬ ጴንጤ መሆንህን አትመልከት። ትናንት ሊቀዲያቆን ሆነህ በመሰዊያው በመንበሩ በታቦቱ ፊት ቆመህ በወለጋ፣ በነቀምት ገብርኤል ከአረጋዊው አባት ከብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ጋር የቀደስክበትን፣ ተንሥኡ ለጸሎት ብለህ፣ ሃሌሉያም ብለህ ምስባኩን የሰበክበትን፣ ደጀ ሰላሙን፣ ሰዓታት ማኅሌቱን ኪዳኑን አስታውስ። ለዛሬ ማንነትህ የትናንቱን የቤተ ክርስቲያንን ውለታ አትዘንጋ። ሰምተሃል ኦቦ ለማ።  ታደሮችህ ታቦት ሲዘርፉ፣ ቤተ ክርስቲያን ሲያቃጥሉ ዝም አትበል። ህሊና ይኑርህ። ዛሬ ጴንጤ ብትሆንም ትናንት የነበርክበትን አትዘንጋ።
•••
እንደ ደመቀ መኮንን፣ እንደ ሙፈሪያት ካሚል አትጥሏት። እነሱ እንኳን እሺ የወሃቢይ እስላሞች ስለሆኑ ይጥሏት ይባል። እናንተ ምን እንሁን ብላችሁ ነው። እንደ ሶማሌው ፕሬዘዳንት እንደ ሙስጠፌ አክብሯት። እንድትከበሩ አክብሯት። እንድትፈርስም አትድከሙ። እንደ መለስ ዜናዊ፣ እንደ ስብሃት ነጋ፣ እንደ ህወሓት፣ እንደ አረብ አሽከሩ እንደ ኦነግ ጥርሳችሁን አትንከሱባት።
•••
ትግሬው ህወሓት ለሁለት የከፈላትን ቤተ ክርስቲያን አንድ ካደረጋችሁ በኋላ ታሪክ ሠርታችሁ ታሪኩ የተጻፈበት ቀለም ጠገግ ሳይል በዲቃላው በፀረ ኢትዮጵያው፣ በአባ ሜንጫ ጀዋር መሐመድ አማካኝነት የኦሮሞ ኦርቶዶክስ አማኝን ለሁለት ሲከፍል አትተባበሩ። አቡነ ሳዊሮስ ማለት ኦሮምኛ እንኳን የማይችሉ የመርሃቤቴ የመንዝ ዐማራ ናቸው። ከነ ስሙም አካለውለድ። ኦሮሞ የዋሕ ነው ብለው አናቱ ላይ ሊወጡ ሲጥሩ አትፍቀዱለት። ( ይሄን በሌላ ቀን በሰፊው እመጣበታለሁ። አካለወልድ እኔን አያድርገኝ። ጠብቀኝ። አቡነ ሳዊሮስም ይጠብቁኝ) ። በላይ መኮንን ጥሬ ካካውን እንዲዘፈዝፍብን አታድርጉ። ኋላ ትጸጸታላችሁ።
•••
እናም ጓዶች በምታመልኩት “ በጌታችሁ በየሱስ ስም” እለምናችኋለሁ።
• አንደኛ ቤተ ክርስቲያኑን መስሪያ ፍቀዱ።
• ሁለተኛ ያሰራችኋቸውን አባቶቻችንን ፍቱልን።
••• ገለቶማ። ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።
•••
#ማስታወሻ | ~ በሉ እናንት የተዋሕዶ ልጆች ደግሞ በያላችሁበት ተዘጋጁ። አርክቴክቸሮችም ግሩም የሆነ ዲዛይን አዘጋጁ። ሲሚንቶ፣ ቆርቆሮ፣ ድንጋይ፣ አሸዋና ብረቱም በልባችሁ አዘጋጁ። ኮሚቴዎችም የባንክ ቡክ ለመክፈት ተዘጋጁ። እኔ እንዲህ ይሰማኛል። እንዲህም አምናለሁ። ደግሞም ይደረጋል። ይፈጸማል። ቱ ! ምን አለ ዘመዴ በሉኝ። ይፈጸማል። ለምርጫ የሚወዳደር ፓርቲ ሀገር የሆነች ቤተ ክርስቲያንን አያስቀይምም። ተናግሬያለሁ።
•••
ሻሎም !     ሰላም ! 
ከራየን ወንዝ ማዶ
Filed in: Amharic