>
5:19 pm - Friday August 19, 2022

ኢህአዴግ /ብልፅግና ሌቦቹ ሲጠግቡ በሌላ የተራበ ለመተካት በአምባሳደርነት ከቦታው ገለል የሚያደግርህ አስከፊ ስርዓት ነው!!! (ስንታየሁ ቸኮል)

ኢህአዴግ /ብልፅግና ሌቦቹ ሲጠግቡ በሌላ የተራበ ለመተካት በአምባሳደርነት ከቦታው ገለል የሚያደርግህ አስከፊ ስርዓት ነው!!!

 

ስንታየሁ ቸኮል
የጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ከኃላፊነቱ መነሳቱን በዜና ሰማሁ እጅግ ነዉረኛ ተረኝነት ያነገበ ስግብግብ ሰዉ ነው። በሰኔ 15 ድራማ ሰዎችን ባሉዋሉበት በግፍ ለቅሞ ከማሰር በላይ ከእስር እንዲወጡ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቅ የነበረ ግለሰብ መሆኑ የአደባባይ ሃቅ ነው።
 ከመርማሪዎችና ከአቃቢ ህግ ጋር በሽርክና ብዙ ሰዎችን ሲበዘብዙ እንደነበር ከእነ ስማቸዉ ጥቂት መጥቀስ ይቻላል። አንድ ጀርመናዊ አዋሳ አካባቢ በኢንቨስትመንት የተሰማራ የዉጪ ባለሃብት 20 ሚሊዮን ብር ጠይቀውት ሳይከፍል ከእስር ቤት  አውጥተው በቀጥታ አገሩ ልከውታል። በተመሳሳይ በምን ምክንያት እንደታሰረ የማላቀው ሰዉ አቶ ቴውድሮስ የተባለ ሁለት ሚሊዮን ብር ተቀብለውት ጨምር በማለት ግለሰቡ ቂሊንጦ ይገኛል። ከሶስት እስከ አምስት መቶ ሺህ የሚበዘብዙት ሰዉ በየጊዜው ለጉድ ነው። አቶ ሰይድ የተባሉ ባለሃብት ሰዉ አሁንም እስር ቤት ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መጠየቃቸዉ እኔ በነበርኩበት ሰዓት ሰምቻለሁ።
ይህንን መንግስታዊ ውንብድና ሂሳብ ሳታወራርድ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ከስልጣ ተነሱ እና አምባሳደር ሆኑ ማለት ጉልቻ ቢቀያየር ነው ተረቱ..
ሰሞኑን የተፈታው አቶ ኤርሚያ አመልጋ ቀደም ሲል በርከት ያለ ሚሊዮን ብር ክፈለህ ውጣ መባለቻዉ ይታወቃል። ይሄን ተግባር የማይክዱት አቃቢ ህግ ስልጣንን መከታ በማድረግ በፈጸሙት ወንጀል ህግ ፊት ሳታቆም ስለህግ የበላይነት ማውራት ያሳፍራል። ጭራሽ አምባሳደር ስታደርገው ሞት ይሻላል። ኢህአዴግ በካርድ ማሰናበት የህልውና ጉዳይ የሚባለዉ በዚህ ነውረኛ ተግባሩ ነው። ይህ ቡድን ከዚህ ምርጫ አያልፍም።
Filed in: Amharic