>
5:33 pm - Sunday December 6, 3626

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት የፓለቲካ ድርጅቶች በይፋ ተዋሀዱ!!! (ኤልያስ ገብሩ)

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት የፓለቲካ ድርጅቶች በይፋ ተዋሀዱ!!!

ኤልያስ ገብሩ
ዛሬ የተቀናጁት ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት የፓለቲካ ድርጅቶች ናቸው። ባልደራስ ከአብን ጋር በሀሰት ሲከሰስ ነበር የከረመው። ባልደራስና አብን ዛሬ የታሉ? የታሉ? እውነቱ ግን የተባለው አልነበረው። ስንቱን በፈገግታ ጭምር ታዘብነው ….አለፍን።
 ለወደፊቱ ለፍረጃ መቸኮል መልካም አይደለም፣ ያስገምታል። በቅንነት የመነጨ ምክር መልካም ነው። ምክር ያንጻል። ነገር ግን በጥላቻ ስሜት ተነሳስቶ መፈረጅ፣ መፈራረጅ  ግን ረብ የለውም። ጥላቻ በቅድሚያ የሚጎዳው በጥላቻ ውስጥ ያለውን ነው። …..
ለግንዛቤ ያህል፣ [መረጃ ለሌላቸው፣ መረጃ ያላቸውና እውነቱን የሚያውቁት አውቆ እንዳላወቀ ሊሆኑ ይችላሉ] መኢአድ፣ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ አንጋፋ ሲሆን በ1997 ዓ.ም ቅንጅትን ከመሰረቱት አራት ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። የያኔው ሰፊ ህዝባዊ ቅቡልነትን ያገኘው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር፣ የመኢአድ ሊቀ መንበር የነበሩት ሃይሉ ሻውል (ኢ/ር) ነበሩ። ቅንጅት በአዲስ አበባ 23ቱንም ወንበር አሸንፏል። ህወሃት/ኢህአዴግም በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ መሸነፏን ይመነበት ክስተት  አሁን በህይወት የሌሉት የመኢአዱና የቅንጅት ሊቀ መንበርም ሃይሉ ሻውል (ኢ/ር) በተወዳደሩበት ወረዳ ማሸነፋቸውም ይታወሳል።
 ህዝባዊ ማዕበል የተባለለትና በህዝብ ዘንድ ውዳሴ የተቸረው የምርጫ 97ቱ ቅንጅት፣ አንዱ ታሪኩ ህብረ- ብሄራዊ ከተባለው መኢአድ ጋር ነው። መካድ አይቻልም ነገር ….
የአሁኑ የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ማሙሸት አማረም በቅንጅትም ጊዜ ከአመራሮች ጋር ታስሮ የተፈታ ሲሆን ከጥቂት ዓመታት በፊትም በሽብር ወንጀል ተከስሶ እስር ቤት የከረመ ነው።
የሆኖ ሆኖ፣ የተስማሙ ፓርቲዎች በአንድ መስመር ይሂዱ፣ ያልተስማሙም ደግሞ በሚያዋጣቸው መስመር ይሂዱ። ምርጫው ሲመጣ ህዝብ ያመነበትን ይምረጥ። አንዱ የዴሞክራሲ መገለጫ ይሄ ሲሆን ህዝብ የመረጠውን ያድርግ። ኢትዮጵያ ለዘመናት ያጣችው አንዱና ቀዳሚው ይሄ ነው #ዴሞክራሲያዊ ምርጫ።
Filed in: Amharic