ራሳቸውን የረሱት ገርባዎች
አቻምየለህ ታምሩ
ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ለመሆን የሚውተረተሩ ገርባዎች ነገር ሁሌም ያስገርመኛል። ራሳቸው ኦሮሞ ሳይሆኑ አማራ ያገባን አፋተን እኛን እንዲያገባ እናደርጋለን ይሉናል። ይገርማል! ይህን የሚሉን ሰዎችኮ ራሳቸው ኦሮሞዎች አይደሉም። አማራ ያገባ አፋተን እኛ እናገባዋለን የሚሉን የኦፌኮ ደጋፊዎች በኦሮሞ ተወረው ማንነታቸው ከመጥፋታቸው በፊት ምናልባትም አማራ የነበሩ የማንነት ቀውስ ውስጥ የወደቁ ሰዎች ናቸው። በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ትክክለኞቹ ኦሮሞዎች ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ነበሩ። የተቀረው ኦሮምኛ የሚናገረው ሕዝቡ ኦሮሞ አልነበረም። ኦሮምኛ ግን በግድ እንዲናገር ተደርጓል። አባገዳዎች ይህን በወረራ ይዘው ጭሰኛ ያደረጉትን ነባር ሕዝብ ገርባ ወይም ገበሮ ይሉታል።
በኦሮሞዎች በራሳቸው አፈ ታሪክ መሰረት ኦሮሞው ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው። ዘጠኙ ገበሮ ወይም በወረራ የተያዘ ሕዝብ ነው። ይህንን እውነት ዛሬም በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። በቅርቡ የተጠና ጥናት እንደሚያሳየው የሰላሌና የአምቦ ሕዝብ የDNA ውጤት ዝምድናው ከምንጃርና ከጅሩ ሕዝብ ጋር እንጂ ከቦረና (እወነተኛው ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም። የአርሲ ሕዝብ ዝምድናው ከሐዲያ ጋር እንጂ ከቦረና (ከእውነተኛ ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም። በበርካምበር ጥናት መሰረት የአርሲ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሐድያ ነው።
የጅማ ሕዝብ ከየምና ከከፋ ሕዝብ እንጂ ከከቦረና (ከእውነተኛ ኦሮሞዎች) ጋር ምንም ዝምድና የለውም። ወለጋ እውነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስር አይሞሉም። የወለጋ ተወላጁ የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፌሰር ተሰማ ተአ እንደነገረን በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያየኔውን ቢዛሞን የአሁኑን ወለጋን ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጡት ቦረናዎች “ደገል ሰቂ” ይባላሉ። ትርጉሙም የመጀመሪያዎቹ ሰፋሪዎች ማለት ነው። እውነተኛ ኦሮሞዎቹ እነዚህ ለባሪያ ፍንገላ መጥተው እዚያው የቀሩት ደገል ሰቂሶች ብቻ ናቸው። የተቀረው ኦሮምኛ እንዲያወራ የተደረገው ሁሉ ኦሮሞ አይደለም።
ባጭሩ እስካሁን ድረስ በራሳቸው በኦሮሞ ብሔርተኞች የተደርጉ ጥናቶች ሁሉ እንደሚያሳዩት በየአካባቢው የሚገኘው ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ እዚያው አካባቢ ከሚገኝ ሌላ ቋንቋ ተናገሪ ጋር እንጂ ከእውነተኛ ኦሮሞዎቹ (ከቦረናዎች) ጋር ምንም አይነት ዝምድና የለውም። በኦፌኮ ስብሰባ ተገኝተው ከኦሮሞ ጋር የተጋባን አማራ እናፋታለን የሚሉ ራሳቸው ኦሮሞ ያልሆኑ ገበሮዎች ለሚሉት ነገር ታማኝ ከሆኑ ከሁሉ በፊት እነሱ ራሳቸው ዘራቸው ያልሆነን ማንነት ትተው፤ ዘራቸው ካልሆነ ኦሮሞ ጋር የመሰረቱትን ጋብቻ ፈትተው ከኦሮሞ የገዢ መደብ ወረራ በፊት ከነበረው የጥንት ማንነታቸውን ከሚጋሩ ሰዎች ጋር ተጋብተው የመርህ ሰዎች መሆናቸውን ያሳዩን።
ከታች የታተመው ገጽ በኦሮሞ ታሪክ ጥናት ጥርሱን የነቀለው አሌክሳንድሮ ትሪውልዚ “Boorana and Gabaro among the Macha Oromo in Western Ethiopia” በሚል ርዕስ ካሳተመው ድንቅ ምርምር የተወሰደ ነው። ጥናቱ ዛሬ ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮሞ እንዳልሆነ የኦሮሞ ባላባቶች ራሳቸው የሚሉትን የመዘገበበት የምርምር ውጤት ነው። አንብቡት!