>

"ምርጫዉ ከአሁን መጭበርበር ጀምሯል!!!" ይላሉ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሀይሌ (ሸንቁጥ አየለ)

“ምርጫዉ ከአሁን መጭበርበር ጀምሯል!!!” ይላሉ ትሁቱ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሀይሌ

 

ሸንቁጥ አየለ
“እንዴት?” አልናቸዉ::
ምክንያታቸዉን እንደሚከተለዉ አስቀመጡ::
ምርጫ የሚጭበረበረዉ በተለያዬ ደረጃ ነዉ::ምርጫ የሚጭበረበረዉ ደረጃ በደረጃ ነዉ:-
1ኛ. አሁን የብልጽግና/ኢህአዴግ ፓርቲ መሪዎች የሚንቀሳቀሱት እና ደጋፊዎቻቸዉን የሚቀሰቅሱት በአዉሮፕላን እየሄዱ ነዉ::ወጭዉም ከመንግስት ካዝና ነዉ::ህዝቡንም ሰብስበዉ የዉሎ አበል የሚከፍሉት ከመንግስት ካዝና በሚወጣ ገንዘብ ነዉ::
  -የመንግስትን ገንዘብ እያባከነ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በጉብኝት መልስ እያሳበበ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ ነዉ::እንዲሁም ሌሎችም ሚኒስቴሮች የመንግስትን ገንዘብ በማባከን የፓርቲያቸዉን የብልጽግና/ኢህአዴግ ፕሮግራም እያራመዱ ቅስቀሳ እያደረጉ ነዉ::
2ኛ.የሀገሪቱን ሚዲያ ሙሉ ለሙሉ የሚጠቀሙት ለብልጽግና/ኢህአዴግ ፓርቲ ብቻ ነዉ::ለምሳሌ የባልደራስ-መኢአድ ጥምረት ሲመሰረት የምስረታዉ እለት እንኳን አንድም የመንግስት ሚዲያ ተገኝቶ አልዘገበም::
3.ሕግ የሚያወጡት የራሳቸዉን የብልጽግና/ኢህአዴግ ጥቅም የሚያስጠብቅ በሚሆን መልክ ሲሆን ተቃዋሚዎችን ግን በሚጎዳ መልክ ነዉ
4. የሀገሪቱን በጀት ለብልጽግና/ኢህአዴግ ካድሬዎች ማሰልጠኛ እያዋሉ ሲሆን ተቃዋሚዎች ግን እንዳይሰበሰቡ እና እንዳይነጋገሩ እንኳን ክልከላ እያደረጉ ነዉ::
“ምርጫዉ ከአሁን መጭበርበር ጀምሯል” ያልኩት ለዚህ ነዉ አሉ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሀይሌ በትህትና ፈገግ ብለዉ::
ከፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሀይሌ ባህሪ በጣም የሚገርመኝ ነገር በአንድ ነገር ላይ ጥልቅ እዉቀት ኖሯቸዉ ሳለ ሀሳባቸዉን የሚያካፍሉት ግን በትህትና እና በእርጋታ ነዉ::
ትሁቱ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሀይሌ የኢትዮጵያን ጉዳይ አንግበዉ እድሜአቸዉን ሁሉ ሳያሰልሱ ቢደክሙም አሁንም በ86 አመታቸዉ እጅግ የጋለ የሀገር ፍቅር ስሜት አላቸዉ::
Filed in: Amharic